Monday, March 26, 2012

የለገዳዲ የቅ/ኪዳነ ምህረት ተአምር




የካቲት 16/2004 ዓ.ም  የቃል ኪዳኗ ታቦት ለእመቤታችን ቃል ኪዳን በተገባበት ቀን ለማክበር  ከህናት ወደ ዋሻው ገብተው ታቦቷን ተሸክመው ወደ  ድንኳን መጡ፡፡ እልልታው ቀለጠ ግማሹ በደስታ የለቅሳል ቀድሞ የፈረሰው የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን  ጋር የተጣለው ድንኳን ደረሱ ታቦት ተሸካሚው ካህን ምልክት አሳዩ ታቦትን መሸከም አልቻልኩም አቃጠለኝ ካህን ይቀየርልኝ አሉ፡፡ በሌላ ካህን ተቀየሩ ሕዝቡም እንዲረጋጋ ተነገረው፡፡ ወረብ ስብከት ወደፊት ለሚሰራው መቃኞ ቤተ ክርስቲያን እርዳታ ተሰበሰበ ስርዓት ቅዳሴ በድንኳን ውስጥ ተከነወነ፡፡ ከዚያም ታቦተ ቅድስት ኪዳነምህረትን ይዘው ከድንኳን ጉዞ ተጀመረ፡፡ ለወንጌል መስፋፋት ዘወትር የሚደክሙት ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉት የለገዳዲ ወጣቶች ቀይ ቲሸርት ለብሰው ቀይ ምንጣፍ የሚያነጥፉ ተቦቷን ወደ መጣችበት ዋሻ ለመመለስ ይዘምራሉ፡፡ ድንገት ድምፅ ተሰማ አልቅሱ ምዕመናን አልቅሱ እግዚአብሔር እንዲታረቀን አልቅሱ የሚል  በሞንታርቦ ድምጽ ተሰማ  ምዕመናን ሁሉ ተደናገጡ ታቦተ ኪዳነ ምህረትን የተሸከሙትን ሁለኛው ካህን እያለቀሱ ድምጽ አሰሙ፡፡ ተቃጠልኩ አንሱልኝ አልቻኩም እግዚኦ በሉ ብለው በወደቁበት ይጮኃሉ ግን ማን ታቦቷን ያንሳላቸው፡፡ እሳትን ማን ይደፍራል፡፡ ጩኽቱ ምህላው ለቅሶው እግዚኦታው ቀጠለ ግን ማንም ታቦቷን ማንሳት አልቻለም ሕዝበ ክርስቲያን እንደ ሻሽ ተነጥፈው አለቀሱ መነኮሳት እና ካህናት አነቡ በብዙ ለቅሶና እግዚኦታ ቆሞሱ አባታችን በወደቁበት ቦታ ሆነው ወደ ዋሻ አትመልሱኝ ክብሬ መገለጫው ደርሷል ወደ ድንኳን አስገቡኝ ብላለች ሲሉ በቀላሉ ብድግ አለችና ወደ ድንኳን ገባች፡፡ ሁለተኛው ታቦት ተሸካሚው ካህን ከወደቁበት ለማንሳት ተሞከረ እራሳቸውን ስተው በሕይወትና በሞት መካከል ሳሉ ወጣቶች ካህኑን ከካህን ጋር ይዘው ወደ ፀበሉ ሮጡ ታቦት ተሸካሚው ካህን ሲጠመቁ በእሳት የጋለ ብረት ምጣድ ውሃ ሲፈስበት የሚያወጣውን ድምጽ እና ጭስ እሰቸውም ላይ ታየ ከብዙ ሰዓታት ቆይተ በኋላ እራሳቸውን አወቁ፡፡ ካህናቱ የወደቁት ኃጢያተኛ ስለሆኑ ሳይሆን የቅድስት ኪዳነ ምህረት ዕለት ወደ ዋሻ አልገባም ብላ በተዓምቷ ቦታውን ስአስከበረች ነው፡፡ የወረዳው ምክር ቤት ፍልፍል ቤተክስቲያን ኃይማኖታዊ እና ታሪከዊ ቦታነቱን የታቦቷን ሃያልነት አምነው ተቀበሉ፡፡ ግን ቦታውን እስካሁን ለቤተክስቲያኗ አልሰጡም  ጠንካራው  የለገዳዲ ምዕመናን ግን በጥቂት ቀን ውስጥ መቃኞ ቤተክስቲያን ስርቶ አጠናቆ እሁድ መጋቢት 16/2004 ዓ.ም ፅላቷን ከድንኳን ወደ መቃኞ በሰላም ገብታለች ሕዝበ ክርስቲያኑም ከተለያየ ቦታ እየመጡ እየተፈወሱ ናቸው  በቀጣይ የተሸለ ቤተ ክርስቲያን ሰርቶ በቅርብ ማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው ሁላችንም የራሳችንን ድርሻ እንድንወጣ ይገባል መልክታችን ነው ፡፡
አምላክ ቤተክርስቲያናችንን ከጠላት ይጠብቅልን


No comments:

Post a Comment