Thursday, March 1, 2012

አገልግሎት


አገልግሎት  በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ኤር.48:10 የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚያደግ ርጉም ይሁን፥ ሰይፉንም ከደም የሚከለክል ርጉም ይሁን

  

 

Wednesday, February 29, 2012

ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ማን ናቸው?


 ለማታውቋቸው

የራሳቸውን የእምነት ድርጅት አቋቁመው የነበሩ፣ በፊርማቸው ከፕሮቴስታንት እምነት የመግባት ፍላጎት እንዳለው የጻፉ፤ ሽጉጥ ታጥቀው የሚሄዱ፣ ባላቸው የፖለቲካ ቀረቤታ ብዙ ግፍ የሚያስፈጽሙ፣ ምእመናን ለአቤቱታ ወደ አባቶቻቸው ዘንድ ሲመጡ በጎን በፖሊስ ምእመናንን ያሳገቱ ወዘተ ወዘተ። ለማንኛውም እርሳቸውን በተመለከተ ያሉትን መረጃዎች በሙሉ ከዚህ በታች በሰፊው አቅርበናል። ቅዱስ ፓትርያርኩ ከዚህ ሰው ወግነው ይህንን ሁሉ ምእመን ማሳዘን አለባቸውን?


                                                    
ቀን፡- 05/02/2002

ለአባ ሠረቀ ብርሃን
ለሰንበት ት/ቤቶች መምሪያ ሐላፊ፤

          የማክበር ሰላምታዬን እያቀረብኹ፣ እንደሚታወቀው ባለፈው በተነጋገርነው መሠረት ጉዳዩን እየሄድኹበት እገኛለኹ፡፡

እንደሚታወቀው አንዳንድ የአቡነ ሳሙኤል ደጋፊዎች የግል ማኅደሬን ለማበላሸት የፓትርያሪኩን ሕጋዊ ወኪልነቴን ለመሻር ደብዳቤ ጽፈውብኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን ሐሳባቸውን አክሽፌባቸዋለኹ፡፡ በመኾኑም አቡነ ይስሐቅ እንድነሣ ሊያደርጉኝ ቢያስቡም በአቡነ ገሪማ ጸሐፊነት ደብዳቤው እንዲመለስልኝ ተደርጓል፡፡ ምክንያቱም ጋዜጣ ላይ የጻፍኹት ራሴን ለማስተዋወቅ አይደለም፡፡ የፀረ ሰላም ኀይሎችን ምስጢር ነው ያወጣሁት፡፡ አባ ሠረቀ ብርሃን በእርስዎ በኩል ይጠበቅብዎታል፣ ምክንያቱም በርካታ ሰንበት ት/ቤቶችን በመምሪያው ሥር ማግኘት ስለምትችሉ፣ ቤተ ክርስቲያንን በወጣት ኀይል ነውና ማደስ የሚቻለው ጠንክረን መሥራት እንችላለን፡፡
እኛ ሣራ ወለደችን በመኾኑ እናታችንን ከኋላ ቀር አሠራር እና ባህል አላቀን፣ ወጣቱን በተሐድሶአውያን ኅብረት አዲስ ጥምቀት በማድረግ ‹‹ቅን ልቦና የመንፈሳዊ የፈውስ አገልግሎት›› ሥር ልንሰበስባቸው እንችላለን፡፡

የካናቴራ አልባሳት ማሠርያ ለማሠራት በጎ ፈቃደኞችን እየጠቆሙኝ ነው፡፡ ስለዚህ እኔም የማጥመቅ ሥራ በየቤቱ እየዞርኹኝ እያጠናከርኩኝ ነው፡፡ እርስዎም ይህን መንገድ በተሻለ መንገድ አጠናክረው ሊቀጥሉበት ይገባል፤ ስለ ገንዘቡ ሊጨነቁ አይገባም፡፡ 170 ሺሕ የሚያወጣ ሐውልት በእኛ ደብር ስለምናሠራ ከዚያ ላይ በሚገኘው ገንዘብ ልናጠናክረው እንችላለን፡፡ በዙሪያው ያሉ የአቡነ ሳሙኤል ደጋፊዎች ይህን ሐሳባችንን ሊያደናቅፉ ቢችሉ እንኳን ተቋቁመን ልንጥላቸው ይገባል፡፡

በመጨረሻም የሙሉ ወንጌል አማኞች ወላጅ ለሌላቸው ሕፃናት የገንዘብ እና የልብስ ድጋፍ ስለሚያደርጉልን ሕፃናትን መመዝገብ አለብን፡፡ በዚህ እኔ ባለሁበት ደብር አባ ገብረ ሥላሴ የተባሉት በስማቸው የመሠረቱት የሕፃናት ማሳደጊያ በርካታ ልጆች ስላሉ፣ በዚህ ማሳደጊያ ስም ልናገኝ እንችላለን፡፡ ስለዚህ በገንዘቡ በኩል በእንዲህ ዐይነት ኹኔታ ላይ ስለሆንን እርስዎ ወጣቱን በማነሣሣት ትልቅ ሥራ ሊሠሩ ይገባል፡፡ በተረፈ አዳዲስ ነገር ሲኖር በስልክ በመደዋወል እንጨርሰዋለን፡፡

                                      

 ‹‹ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋራ››
ስል ወድምፅ ማስረጃዎች


                                    

ጌታቸው ዶኒ እንደገና ወደ ዜና ብቅ ሲል

(ምንጭ፡- የካቲት 21/2004 ዓ.ም ከአማናዊቷ ደጀ ሰላም)

  • ዳግመኛ በተሾመበት ደብር የተቀሰቀሰው የምእመናን ተቃውሞ ተጠናክሯል።
  • የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እስርና ማስፈራሪያ እየተፈጸመባቸው ነው።
 በግንቦት 2003 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ራሳቸውን “ወንጌላውያን” ብለው ከሚጠሩ የፕሮቴስንታት አብያተ እምነት ጋር ያለው የዓላማ ግንኙነት በማስረጃ የተረጋገጠበት፣ በሕገ ወጥ የማጥመቅ ሥርዐትና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ጉልሕ ሃይማኖታዊ ሕጸጽ የፈጸመው ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ቀደም ሲል በአበው ካህናት እና ምእመናን ከፍተኛ ተቃውሞ ወደተባረረበት የቃሊቲ ደብረ ገነት ቁስቋም ማርያም እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተመልሶ አጥቢያውን እንዲያስተዳደር በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ መሾሙ ተሰምቷል፡፡
ጌታቸው ዶኒ ከሁለት ዓመት በፊት በተባረረበት ደብር የቀድሞውን የአለቅነት ሥልጣኑን ይዞ እንዲመለስ የተደረገው ከታኅሣሥ ወር 2004 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን የሥፍራው ምንጮች በጽሑፍ ያደረሱን መረጃ ያመለክታል። ሊቀ ካህናት ጌታቸው በድጋሚ መመደቡ ከተነገረበት ጊዜ ጀምሮም በአጥቢያው ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ዘንድ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከዕለት ወደ ዕለት በመጠናከር ላይ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
ጥር 6 ቀን 2004 ዓ.ም የሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒን ወደ ደብሩ መመለስ የሚቃወም ጽሑፍ /ትራክት/ ለምእመናን ተሰራጭቷል፡፡ የአቃቂ ቃሊቲ ፖሊስ አንዳንድ የአጥቢያውን ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በመጥራት “አካባቢውን ሰላም ነስታችኋል” በማለት ቢያስጠነቅቅም ተቃውሞው እንዳልቆመ ነው ምንጮቹ የተናገሩት፡፡
በተለይም በበዓለ ጥምቀት በተከናወነው ጸሎተ ቅዳሴ፣ ሥርዐቱ ከተጀመረ በኋላ ቅዳሴውን የሚመሩት ካህን የለበሱትን ልብሰ ተክህኖ አስወልቆ በመልበስ ቅዳሴውን ለመምራት መሞከሩ ካህናቱንና ምእመናኑን አስደንግጧል፡፡ ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ የተፈጸመው ይኸው የጌታቸው ዶኒ ድፍረት ውስጥ ለውስጥ ተሰምቶ ጥር 12 ቀን 2004 ዓ.ም ታቦታቱ ወደ መንበራቸው ለመመለስ በዐውደ ምሕረቱ በቆሙበት ወቅት ‹ምክር እና ቡራኬ እሰጣለሁ› ብሎ በተነሣበት ወቅት ምእመናኑ በከፍተኛ ድምፅ ዝማሬና እልልታ በማሰማት ከመናገር እና ከመደመጥ ተከላክለውታል፡፡
በበዓሉ አከባበር ወቅት በርካታ የፖሊስ ኀይል በሥፍራው መታየቱ ውጥረት ፈጥሮ የነበረ ሲሆን ‹ሊቀ ካህናት› ጌታቸው ዶኒ ወጣቶቹን በዐመፅ ቀስቃሽነት በመክሰስ ፖሊስ እንዲያስታግሣቸው ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አለማግኘቱ ተገልጧል፡፡
ቁጥራቸው ከ400 በላይ የኾኑ ምእመናን ጌታቸው ዶኒ ቀደም ሲል የደብሩን አገልጋይ ካህናት በጎጥ (ተወላጅነት) በመከፋፈል እንዳይግባቡ ማድረጉን፣ ከጠበልተኞች ብጽዓት እና በአጥቢያው በሚፈጸመው ተኣምር የተነሣ ከሩቅም ከቅርብም ከሚሰበሰቡ ምእመናን የሚገኘውን ሀብት በአስተዳደራዊ መንገድ ለሙስና በማመቻቸት ሀብቱን ለምዝበራ ማጋለጡን፣ ምእመኑን ለማስተማርና አባታዊ ሓላፊነትን ለመወጣት ያለበትን ውስንነት በመጥቀስ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት አቤቱታቸውን አቅርበዋል፤ በግልባጭም በክፍለ ከተማ እና ወረዳ ደረጃ ለሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት አካላት አሳውቀዋል፡፡
ይሁንና የምእመናኑና የሰንበት ት/ቤቱ አቤቱታ በግልባጭ የደረሰው ፖሊስ የካቲት አንድ ቀን 2004 ዓ.ም ሁለት የሰንበት ት/ቤቱን የሥራ አመራር አባላትንና ሦስት ምእመናንን ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ በማለት ጠርቶ በማሰሩ የተፈጠረው ተቃውሞ እንዲባባስ አድርጓል፡፡ ጉዳዩ ያሳሰበው የወረዳው (05) አስተዳደር ጽ/ቤትም የካቲት ሁለት ቀን 2004 ዓ.ም የአጥቢያውን ምእመን በጽ/ቤት በመጥራት ምእመናኑ ጉዳዩን ኮሚቴ በማዋቀር እንዲከታተሉ፣ የክፍለ ከተማው ፖሊስ በምእመናኑ ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ ከመፈጸም እንዲቆጠብ በማግባባት ሁኔታውን ለማረጋጋት ጥረት ተደርጓል፡፡ የታሰሩት ምእመናንም የካቲት ሁለት ጠዋት ፍ/ቤት ቀርበው እያንዳንዳቸው የብር 350 ዋስ ጠርተው እንዲፈቱ ተደርጓል፤ ከወረዳው አስተዳደር ጋር በተደረሰበት መግባባት መሠረትም ጉዳዩን የሚከታተሉ ስምንት አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡
ይህም ሆኖ በማናለብኝ ድርጊቱ የቀጠለው ጌታቸው ዶኒ በምእመኑ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑትን የደብሩን ስብከተ ወንጌል ሓላፊ እንዲታሰሩ አልታቀበም - ቆይቶ የስብከተ ወንጌል ሓላፊው በዋስ ቢለቀቁም፡፡
በፈውስ ተኣምራትና ሌሎች ድንቅ ሥራዎችን በመሥራት የሚታወቀው የቃሊቲ ደብረ ገነት ቁስቋምና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተ ስምንት ዓመት ያህል አስቆጥሯል፡፡ ሥፍራው ከአዲስ አበባ ወጣ ያለና የአጥቢያው ምእመናን ቁጥርም አነስተኛ ነው፡፡ በ2001 ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበር ወቅት ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው በሚያድሩበት ቦታ የደብረ ገነት ቁስቋም ማርያም ታቦት ከቦታው ባለመነሣቷ እዚያው ቦታ ላይ ማደርያ እንደተሠራላት፣ በጠበሏ እና እምነቷ ፈዋሽነት የተነሣም በርካታ ምእመናን ከየማእዝናቱ እየመጡ መሻታቸው እንደሚፈጸምላቸው ተዘግቧል፡፡
ጌታቸው ዶኒ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጭ የሲዳሞ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ በፓትርያርኩ ከተሾመበት ሥልጣኑ ምእመናን ባቀረቧቸው ማስረጃዎችና ተቃውሞዎች መነሻነት እንዲወገድ ከተደረገ በኋላ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ምክትል ሓላፊ ሆኖ ተመድቦ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል፡፡
በአሁኑ ወቅት የደብረ ገነት ቁስቋም ማርያምን ጨምሮ በደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል፣ በማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም፣ በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና በአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት ተመሳሳይ አስተዳደራዊ ችግር የታየ ሲሆን አለመግባባቱ አስቸኳይ እልባት እንዳያገኝ አስተዳደሮቹ ከሀ/ስብከቱ አንዳንድ ሓላፊዎች እና በፓትርያርኩ ዙሪያ የፈጠሩት የጥቅም ግንኙነት ዕንቅፋት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

Monday, February 27, 2012

ፆም አያስፈልግም?

ፆም  አያስፈልግም?
 ክርስቶስ ፆሞልኗልና አንፆም ?
ፆም በዛ ?
ፆም ማለት ምን ማለት ነው ?
ፆም የታዘዘበት ምክነያቱ ምንድን ነው ?
 ቀሲስ ከፍያለው  ጥላሁንቀሲስ ከፍያለው  ጥላሁን
ፆም የዳቢሎስ ድል መንሻ ነው ያድምጡት በጥቂቱ



ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል



"ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥
 እንዲህ ሲል። በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች። ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ። ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥ ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ ጌታም አለ። ዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን? ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፥0 እንዲህ ሲል ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ። እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጦማለሁ፥ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት አወጣለሁ አለ ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን። አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።" ሉቃ18:1-14
"ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም"  ማቴ. ፬፡፬

Friday, February 24, 2012

ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ

ከበለስ በታች  ሳለህ  አየሁህ ዮሐ. 1፡-44 በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ዮሐ.1:44-52 "በነገው ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊወጣ ወደደ፥ ፊልጶስንም አገኘና ተከተለኝ አለው  ፊልጶስም ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበረ ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ። ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው ናትናኤልም ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? አለው። ፊልጶስ። መጥተህ እይ አለው ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ። ተንኰል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው እነሆ አለ ናትናኤልም ከወዴት ታውቀኛለህ? አለው ኢየሱስም መልሶ። ፊልጶስ ሳይጠራህ፥ ከበለስ በታች ሳለህ፥ አየሁህ አለው ናትናኤልም መልሶ። መምህር ሆይ፥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ አለው ኢየሱስም መልሶ ከበለስ በታች አየሁህ ስላልሁህ አመንህን? ከዚህ የሚበልጥ ነገር ታያለህ አለው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ አለው።"

Tuesday, February 21, 2012

አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ አብሳዲ አረፉ።


በ1912 የተወለዱ አና በኢትዮጵያ እና በኤርትራ በክህነታቸው ቤተ ክርስቲያንን ያገለገሉት ብፁእነታቸው ዲቁናን  ከብፁዕ አቡነ ይስሃቅ እንዲሁም ቅስናን ከኤርትራው ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል  ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ረዳት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል እንዲሁም ከግብፅ ከፍሊስጤም እና ከሊባኖስ ያለውን የቤተ ክርስቲያን ፈተና በማቀለል ከፍተኛ አገልግሎትን ፈፅመዋል ብፁእነታቸው የዕብራየስጢኛ እና የአረቢኛ ቋንቋም ተምረዋል ፡፡
ላለፉት 60 ዓመታት በኢየሩሳሌም ገዳማት የኖሩትና በእግራቸው ከኢትዮጵያ ወደ ቅድስት አገር ጓዙት  ጥንታዊ ትውፊት ከፈፀሙት አበው መካከል የነበሩት ብፁዕነታቸው በሕመም እና በእርግና ምክንያት  በተወለዱ በ 92 ዓመታቸው የካቲት 10 ለሊት ባደረባቸው ሕመም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል የአባታችንን ነፍስ አምላክ በገነት ያሳርፍልን::