ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ በሰፊው ለክርስቲያን በብዙ ቦታዎች ተጽፎል፡፡
ለነዲዳትና ለመሰሎቹ በመልስና በመረጃ መልክ ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ በአጭሩ ተገልጧል፡፡
እሱም በመጀመሪያ የኦሪትን ከዚያ የቁርአንን ስለአዳም መውደቅ ታሪክ መነሻ አድርጎ ታትቷል፡፡
(ዘፍ 2፡7) ከዚህ በኋላ
እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት አፈር ወስዶ፣ ሰውን ከአፈር አበጀው፣ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፡፡ ሰውም ሕይወት
ያለው ፍጡር ሆነ፡፡
(ዘፍ 2፡15)ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር
አምላክ ሰውን በኤደን የአትክልት ቦታ አኖረው፤ይህንም ያደረገው ሰው የአትክልቱን ቦታ እንዲያለማውና እንዲኩተኩተው ነው፤ እግዚአብሔር
አምላክ ሰውን በአትክልቱ ቦታ ከሚገኙት ዛፎች ሁሉ ፍሬ ብላ፤ ነገር ግን ደጉን ከክፉ ለመለየት የሚያስችል ዕውቀት ከሚሰጠው ዛፍ
ፍሬ አትብ፤ ምክንያቱም ከዚህ ፍሬ በበላህበት ቀን በርግጥ ትሞታለህ ብሎ አዘዘው፡፡
(ዘፍ 2፡18) እግዚአብሔር አምላክም
አለ፤ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፡፡ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት፡፡
(ዘፍ 2፡20) ----- ፤ እግዚአብሔር
አምላክም በአዳም ከባድ እንቅለፍን ጣለበት አንቀላፋም፣ ከጎድኑም አንዲት አጥንት ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ሞላው፤ እግዚአብሔር አምላክም
ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት፣ አዳምም ይህች አጥንት ካጥንቴ፣ ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ
ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል፡፡ ስለዚህ ሰው አባትና እናቱን ይተዋል፣ ከምሽቱም ይጣበቃል፤ ሁሉም አንድ ሥጋ ይሆናሉ፡፡ አዳምና
ምሽቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፡፡ አይተፋፈሩምም ነበር፡፡
(ዘፍ.3፡1……፣)አዳምና ሔዋንም
በዚህ ሁኔታ በገነት መካከል የፍጥረታት ሁሉ ገዥዎች ሁነው ሲኖሩ ሰይጣን ቀናና በእባብ ተመስሎ የተከለከለችውን ዕፅ እንዲበሉ በማድረጉ
የአምላካቸውን ትእዛዝ በመተላለፋቸው ተረግመው ከገነት ወጡ፡፡
ይህ ታሪክ በቁርአን ደግሞ
እንዲህ ነው፤ (ላሟ ምዕራፍ ፡2፡34-38) መላእክትንም ለአዳም ስገዱ ባልነ ጊዜ ከዲያብሎስ በቀር ሁሉም ስገዱ፣ እሱ ግን እምቢ
አለ፣ ኮራም በዚህም ከከሐዲዎች ተቆጠረ አዳም ሆይ !አንተ ከነምሽትህ በገነት ተቀመጥ፤ ከርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ፣
ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፤ ከበደለኞች ትሆናላችሁና አልነም፡፡ ከርሷም ሰይጣን አዳልጦ (አሳስቶ) በውስጡ ከነበሩበት ድሎት አወጣቸው፡፡
አንዱ ለሌላው ጠላት ሁናችሁ ውረዱ፣ ለእናተም በምድር ላይ እስከ ጊዜያችሁ ድረስ መጠለያና ሥንቅ አለላችሁ፡፡ በኦሪትም ሆነ በቁርአን
እግዚአብሔር ትእዛዙ በመጣሱ አዝኖ አዳምና ሔዋንን ከገነት እንዳስወጣቸው ቁልጭ ተደርጎ ተጽፏል፡፡ ቁርአን ከዚህ በኋላ ስለመታረቅና
ድኅነት የሚናገረው የለም፣ ከአሕዛብ ልማድ ከመጣው መሥዋዕተ እንስሳ በቀር፡፡ ኦሪትና ወንጌል ግን በትንቢትና በፍጻሜ አምላክ ዓለምን
የታረቀው በልጁ ደም መሆኑን አብራርተው፣ ነግረው ደምድመዋል እዳም የፈጣሪውን ትእዛዝ በመተላለፍ ከገነት ወጥቶ፣ እሱ ብቻ ሳይሆን
በመላ ዘሩም በምድረ ፋይድ ሲኖር በሦስት አካላት ሲመሰገን የሚኖር እግዚአብሔር በዳዩን አዳምን ይቅር ለማለት ወሰነ፡፡(ዘፍ.3፡1-4)
ለዚህም መታረቂያ መሥዋዕት አስፈለገ፡፡ በደሉም ግዙፍ ስለሆነ ለመሥዋዕቱ የሰውና የእንሰሳ ደም የማይበቃ ሆነ፡፡ የስላሙ የመሐመዱ፣
የቁርአኑ አምላክ ቢሆን ኑሮ ያፍርድ እንደ ዐጤ ስለሚሰራ ምሬሃለሁ ቢል ይበቃ ነበር፡፡ የአብርሃም አምላክ ግን እውነተኛ ዳኛም
መሓሪም ስለሆነ፣ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው ልጁ ሥጋ ለብሶ እንዲሠዋ ወሰነና ላከው፡፡ (ዘፍ.3፡15) በአንተና በሴቲቱ መካከል፣
በዘርህና በዘርዋ መካከል ጠላትነትን አኖራለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል
አንተም ሰኮናውን ትቀጠቅጣለህ ባለው መሠረት፣ በዳይም ተበዳይም ልጅ ልጃቸውን አዋጡና የአምላክ ልጅ እግዚአብሔር ወልድ፣ ኢየሱስ
ክርስቶስ ፣ሥጋ ለብሶ፣ ትስብአርትን ተዋሕዶ የሰውን ልጅ ጠላት ሰይጣንን ድል ነሥቶ ፣ ከዲያብሎስ ባርነት ከሲኦልና ከገሃነም ሥቃይና
ኩነኔ አዳነ፡፡ የተበዳይና የበዳይ ልጅ (ዘር) በተዋሕዶ ሥጋ ተሰቅሎ ዓለምን አዳነ፡፡ ከሦስቱ ሥላሴ፣ ከሠለስቱ አካላት አንዱ
በተለየ አካሉ እግዚአብሔር ወልድ ሥጋ ለብሶ፣ ተሠቃይቶ፣ ተገፎ፣ ተገርፎ፣ ተሰቅሎ ዓለምን እንዲያድንና ከአባቱም ከራሱም ከመንፈስ
ቅዱስም ጋራ እንደያስታርቅ እንዴት እንደ ተወሰነ በሥሉስነት ሲመሰገን ከሚኖረው ከገናናውና ከረቂቁ አምላክ አንዱ እግዚአብሔር በቀር
ማንም አያውቅ፡፡ ተበዳዩ አምላክ በዳዩን ሰውን ይቅር የሚልበት ጊዜ ሲደርስ፣ በመበሠሩ በቅዱስ ገብርኤል አማካይነት፣ የቅድስት
ድንግል ማርያምን ይሁን ይደረግልኝ ፈቃድ ብኋላ፣ አንድያ፣ ተቀዳሚ፣ ተከታይ የሌለው ልጁን ሥጋ እንዲዋሃድ እንዲለብስ ወደ ቅድስት
ድንግል ማርያም ላከ፡፡
በልደት ሦስቱም፤ አብ፣
ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ተስማምተዋል፣ ተባብረዋል፡፡ አብ መርጧል፣አጽንቷል፤ መንፈስ ቅዱስ በላያዋ ላይ አድሮ ወላዲተ አምላክ ማኅደረ
መለኮት እንድትሆን አመቻችቷል፣ አዘጋጅቷታል፡፡ እግዚአብሔር ወልድም ከነፍሷ ነፍስ ከሥጋዋ ሥጋ ነሥቶ ፍጹም ሰው ሁኗል፡፡ ስለዚህም
በአንድ አካል የተዋሐደ ሰውና አምላክ ይባላል፡፡ ስለዚህም በአንድ እረኛ አንድ መንጋ በተሰጠው ውሳኔ አንድ መለትስ ይባላል፤
(መለትስም ሰውና አምላክ ወይም መለኮትና ትሰብእት ማለት ነው) በመለኮቱ
የአብ ልጅ፣ በትስብእቱ (ሥጋው) የማርያም ልጅ ይሉሃል ይህ ነው፡፡ በግዕዙም ወልደ አብ በመለኮቱ ወልደ ማርያም በትስብእቱ ይላል
ውሳኔው፡፡ ሰው አምላክ፣ አምላክ ሰው ሆነ የሚያሰኘውም ይህ ነው፡፡ በመለኮቱ አምላክ አማልክት፣ ፈጣሬ ዓለማት ሲሆን፣ በትስብእቱ
ደግሞ ንጉሠ ነገሥት፣ ሊቀ ካህናት፣ ሊቀ ሰማዕት፣ ሊቀ ነቢያት ነው፡፡ እንደ ሰውነቱ፣ ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ትንሽ በትንሽ አድጓል፣
እንደ ሕፃናት አልቅሷል፣ደክሟል፣ ተርቧል፣ ተጠምቷል፣ ምራቅ፣ ደም ወጥቶታል፣ ሙቷል፡፡ አምላክ እንደ መሆኑ፣ አምክነቱን ለማጠየቅ
(ለማስረዳት) በድንግልና ተወልዷል፣ በተዘጋ ቤት ገብቷል፣ በባሕር ላይ ያለ ጀልባ ሂዷል፤ ከሞተና ከተቀበረ በኋላ መቃብር ክፈቱልኝ
መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ተነሥቷል፤ በዚህም አንደ መለትስነቱን እነረዳለን፡፡መለትስ መሆኑን ያልተረዱ ብዙ ሰዎች ትስብእትን ሲያይ
የተነገሩትን ቃላት፣ ጥቅሶች፣ ዐረፍተ ነገሮች፣ ባነበቡ ቁጥር ለማረም ወይንም ለማጣመም ይሞክራሉ፡፡ ይህ ግን ካለማወቅ የመጣ ነው፤
ልኩ መለኮቱነ ሲያዩ የተነገሩትን ለመለኮቱ ሰጥቶ በመለኮት ባሕርይ መተርጎም፣ በትስብእት፣ ለትስብእት የተነገሩትን ደግሞ ለትስብእት
ሰጥቶ ከነበቡ በኋላ አንድ አካል አንድ መለትስ ብሎ አስታርቆ አስማምቶ
መፍታት ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ወልድ የአብና የማርያም ልጅ፣ በአንድ መለትስ መሆኑን ለመረዳት በሰፊው የሚፈልግ
ሁሉ ወደ ፊት በሌሎች ክፍሎች የምናየው ይሆናል፡፡ ከዚህ ግን ፍጽም አምላክ እና ፍጹም ሰው በአንድ አካል እንድመለትስ መሆኑን ለማስረዳት የሚከተሉት ተጠቅሰዋል፤ (ዮሐ.1፡1-14)
3፡1618፤ መዝ.2፡68፤ 109፡4፤ ሉቃ.23፡34፤ ዮሐ.10፡30፤14፡6፤20፡17፤ ኢሳ.61፡13፤ ሉቃ.418-19፤53፡11-12፤
ዮሐ.14፡28፤31፤ መዝ. 21፡1፤ ማቴ.27፡46፤ ሉቃ.13፡32፤ 2ቆሮ.1፡3፤11፡31፤ ኤፌ.1 ኢሳ.3፤17፤ ፊል.2፡6፣10፤
1ጴጥ.1፡3፤ 2ጴጥ 1፡17-18፤ ግብ.ሐዋ 2፡24፤ ራእ.1፡6፤3፡12 ዮሐ.6፡37-39፤7፡29፤ 1፡36፤8፡42፤9፡4፤ ሉቃ.4፡43፤
ገላ.4፡4፤ ዮሐ.4፡9) ከቅዱሳት መጻሕፍት አምላክና ሰው መሆኑን ለመግለጥ የተጻፈ ለቁጥር የሚዳግቱ ብዙ ጥቅሶች አሉ፡፡ቁርአንም
የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ያምናል፤ ይህንም