Monday, August 13, 2012

ፅንሰታ ለማርያም

ቅዱስ ያሬድማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ:- ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች"      አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ:- ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም ፤በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ"
 በኢየሩሳሌም አገር የሚኖሩ ኢያቄምና ሃና የተባሉ በጣም ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ አንድ ልጅ እንኳ ስላልነበራቸው እጅግ ያዝኑ ነበር፡፡ ወደ ቤተ መቅደስ እየሄዱ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ አጥብቀው ይለምኑት ነበር፡፡

Saturday, August 11, 2012

በገዳማት ላይ እየተከሰተ ባለው ጥቃት በተመለከተ ስብሰባ ተጠራ


 እንደሚታወቃው በኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ገዳማትና አድባራት ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን ነው የማይባል በደልና ግፍ እየደረሰ መሆኑን ይታወቃል፡፡ ይህች ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ታሪክ ማሕበራዊና ስነጥበባዊ እድገት ያበረከተችው አስተዋጽኦ ከኢትዮጵያ አልፎ በመላው አለም የሚታወቅ እውነታ ነው፡፡ Read in PDF

ቤተክርስቲያናችን ባላት ታሪክና መንፈሳዊ ሐብት ለበርካታ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ትልቁን ድርሻ የምትይዝ ሲሆን ለዚህም መንግስትና የተላያዩ ተቋማትን በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃሚ እያደረገች ስትገኝ፣ ወደኦትዮጵያ የሚመጡ ቱሪስቶችም በዋነኛነት የቤተክርስትያን ጥንታዊያን ገዳማት አድባራት እና እንደጥምቀት ፤ መስቀል(ደማራ)እና ልደት የመሳሰሉ ታላላቅ በዓላትን መንፈሳዊ አከባበርን ለመመልከት እንደመጡ ዘወትር የሚመሰክሩነው፡፡
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ኢኮኖሚያው እና ስነጥበባዊ የአበረከተችውን አስተዋጽኦ በየትኛውም ዘመን የነበረና ወደፊትም የሚኖር እንደሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሚመሰክረው እውነታ ነው፡፡ 

Wednesday, August 8, 2012

የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚታሰብበት ወቅት ፆመ ፍልሰታ


ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ፤ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት” /መዝ.1318/
ተንሥኢ ወንዒ ቅርብትየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ ውስተ ጽላሎተ ኰኲሕ ቅሩበ ጥቅም፡፡ አቅራቢያዬ መልካሟ ርግብየ ተነሽ፤ ነዪ፤ በግንቡ አጠገብ ወዳለው ወደ ዋሻው ጥላ፡፡” /መኃ.210-14/ 
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መቅደሱ፥ ታቦቱ፣ ማደሪያው፣ መንበሩ እናቱ አድርጎ መረጣት፡፡ ስለዚህ ምክንያት አብ ጠበቃት ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን ከርሷ ተዋሐደ መንፈስ ቅዱስ አጸናት፡፡ እመቤታችን በዚህ ኃላፊ ዓለም 64 ዓመት ቆይታለች፡
በሕይወተ ሥጋ ሳለን ካልጾምንና ካልጸለይን ነፍሳችን ልትለመልም አትችልም፡፡ በጾም በጸሎት ዲያብሎስን፣ ዓለምንና ፍትወታት እኩያትን ድል መንሣት ይቻላል፡፡ እንደዚሁም በጾም አማካኝነት መንፈሳዊ ሕይወትን ማሳደግ ይቻላል፡፡

Tuesday, August 7, 2012

አባ ሕርያቆስ በትምህርቱ መናፍቃንን ተከራክሮ ይመልሳልና ብለው ግብረ ገብም ከሆነ ይሾም ብለዋል:በጸሎቱ ይጠብቃል..


ሕርያቆስ ማለት ህሩይ ማለት ነው : ለሹመት መርጠውታልና: አንድም ረቂቅ ማለት ነው ምሥጢረ ሥላሴን ይናገራልና : ከሊቃውንትስ ምሥጢረ ሥላሴን የማይናገር የለም ብሎ ከሁሉ ይልቅ እሱ አምልቶ አስፍቶ አጉልቶ ይናገራልና አንድም ፀሐይ ማለት ነው: አብ ፀሐይ ወልድ ፀሐይ መንፈስቅዱስ ፀሐይ ብሎ ጽፏልና : አንድም ብርሃን ማለት ነው: የምዕመናንን ልቦና በትምህርቱ ብሩህ ያደርጋልና : ዘአብርሃ መንበረ ማርቆስ በብርሃን እንዲል :አንድም ንብ ማለት ነው: ንብ የማይቀምሰው አበባ የለም እሱም የማይጠቅሰው ሊቅ የለም:ይህም እንደምን ነው ቢሉ:ሐዋርያት የተማረ ግብረ ገብ ይሾም ብለው ሥራት ሰርተዋል: ይህስ አይደለም ሁለቱን አስተባብሮ የያዘ አይገኝም ብሎ የተማረ ከሆነ ይሾም ብለዋል::በትምህርቱ መናፍቃንን ተከራክሮ ይመልሳልና

Monday, August 6, 2012

ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ጀርባ


መናፍቅ ማለት ከፍሎ የሚያምን ሙሉ እምነት የሌለው ማለት ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ የማያምን ሰው መናፍቅ አይባልም። ከሀዲ ወይም አህዛብ ይባላል እንጅ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ አምናለሁ ብሎ ነገር ግን ሙሉ የክርስቶስንና የአባቶች ውሳኔዎችን የማይቀበል አካል መናፍቅ ይባላል። መጸሐፍ ቅዱስ እና አዋልድ መጻሕፍት ስለአምላክ ማንነት የሚናገረውን የማይቀበል፡ የአምላክን ፈቃዳትና ትእዛዛት በተዛባ መልኩ የሚያስተምር መናፍቅ ይባላል።
 
ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት በተሃድሶ መናፍቃን ዙሪያ የተለያዩ ስልት በመጠቀም ቤተ ክርስቲያኒቷን ለመከፋፈል ብዙ ብዙ ጥረት ማድረጋቸውን አስነብበናችኋል ዛሬስ የሚጠቀሙበት ስልት አላዋጣ ሲል ምን እየሰሩ ይገኛሉ? ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሁለት ሺሕ ዓመት ታሪክ ያላት ጥንታዊት ቤተ ክርሰቲያን ትሁን እንጂ መንበሯን ከሊቀ ጵጵስና ወደ ፕትርክና ለማሳደግ አንድ ሺሕ ስድስት መቶ መራራ ዓመታትን ገፍታለች፡፡

Friday, July 27, 2012

ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ታላቅ ሰማዕት


 1875 .. በሰሜን ሸዋ አገረ ስብከት ሰላሌ አውራጃ ፍቼ ከተማ ተወለዱ። ወላጆቻቸው ዕድሜያቸው ገና በወግ ለትምህርት ሳይደርስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመውሰድ ባሕታዊ ተድላ ለተባሉ መምህር አደራ ሰጧቸው። በዚያው ገዳም የንባብ ቤቱንና የዜማውን የትምህርት ደረጃዎች በሚያስገርም ሁኔታ በአጭር ጊዜ አቀላጥፈው በመጨረስ ገና በልጅነት የዕድሜ ደረጃቸው ሦስተኛውን የቅኔ ትምህርት ጀምረው በአጭር ጊዜ ሙሉ ቤት ተቀኙ። ይህንኑ የቅኔ ትምህርት ለማስፋፋት በምዕራብ ጎጃም አገረ ስብከት ወደሚገኘው የቅኔ ትምህርት ማዕከል ዋሸራ ተሻግረው ለመምህርነት የሚያበቃውን ትምህርት ፈጽመው አስመሰከሩ።