(ደቂቀ
ናቡቴ መስከረም 15/2005) “የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።”ያዕ.5:16 በዋልደባ
ገዳም መንግስት በጀመረው የስኳር ፋብሪካ ብዙ በጣም ብዙ በደሎች በመነኮሳቱ ደርሷል እየደረሰም ነው፡፡ እስከአሁንም ችግሩ እልባት
ሳያገኝ በመነኮሳቱ ላይ ደብደባ እንግልት እና ከገዳሙ እንዲሰደዱ እየተደረገ ነው ፡፡

" ካልጠፋ ገላ ዓይን ጥንቆላ "
የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ እርስ በርሱ፣ በሀሳብና በድርጊቱ መካከል
አለመግባባት ይፈጠራል፡፡ለዚህም የአዳምን ልጆች የአቤልንና የቃዬልን ህይወት ማንሳት የሰው ልጅ በተፈጠረ ማግስት አለመግባባትና
የጥቅም እንደራሴነት አንደተጀመረ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ በዘመናችን ከጉንጭ አልፋ ክርክርና ንትርክ አስከ ከፋ ግጭትና ሞት የሚያበቁ
አለመግባባቶች የሚከሰቱት አንድም በስልጣን ወይም በጥቅም ይገባኛል የተነሳ ነው፡፡በነዚህ የግጭት ሰበቦች የተነሳ አለማችን ብዙ
ሚለዮን ሰወችንና ብዙ ሀብትን አላግባብ አጣለች፡፡ ምናልባት የሰው ልጅ የአስተሳስብ አድማሱ እየጨመረ በመጣ ቁጥር ግን ልዩነቶችን
ሰላማዊ በሆነ መንገድ የመፍታት ሂደቱ እየጨመረ መምጣቱ ለመጭዋ ዓለም አበረታች ተስፋ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከሶስት ነገሮች ጋር ሊጣላ
ይችላል፡፡