ፀሎተ ምህላ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
፩ዱ አምላክ አሜን።
“አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረን፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፋችንን ደምስስ። ከበደላችንም ፈጽሞ እጠበን፥ ከኃጢአታችንንም አንጻን፤ እኛ መተላለፋችንን አናውቃለንና፥ ኃጢአታችንም ሁልጊዜ በፊታችን ነውና። አንተን ብቻ በደልን፥ በፊትህም ክፋትን አደረግን፥ በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ።” መዝ.50/51፡1-4
†♥†♥♥♥†♥† የይቅርታ አምልክ አቤቱ
ማረን የቸርነት አምላክ አቤቱ ይቅር በለን፤ ልጅህን ልከህ ያዳንከን አቤቱ ተመልከተን ጨለማ ሕይወታችንን ወደ ብርሃን የለወጥክ
አቤቱ ታደገን።
†♥†♥♥♥†♥† በዚህ ክፉ ዘመን የገጠመንን
መከራና ችግር ታርቅልን ዘንድ በአማኑኤል ስምህ በድንግል እናትህ እንለምንሃለን።
†♥†♥♥♥†♥† በጨለማ ለነበሩት አህዛብ እንደ ነጋሪት ጮኸውመወለድህንና
መምጣትህን ስላስተማሩ ነብያትህ ብለህ ከመዓት ሰውረን።
†♥†♥♥♥†♥† የአህዛብን ምድር በመስቅልህ እርፍ አርሰው የቃልህን
መዝገብ በዓለም ዳርቻ ሁሉ ስለ ዘሩ ስለ ቅዱሳን ሐዋርያት ብለህ ከክፉ መከራ አድነን።
†♥†♥♥♥†♥† ድል ስለነሱ፣ አምነው ንጹህ ስለሆኑ ስለ ሰማዕታት
ተኩላዎች ስለበሏቸው ስለመንጋህ ብለህ ይቅር በለን።