በስመ ሥላሴ
ሁሉን ቻይ ታላቅ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ በቀንና በሌሊት የአንተን መኖር አስታውስና፣ አንተን ሁል ጊዜ በፊቴ አደርግህ ዘንድ ልቤን ምራልኝ፤ በኪሩቤል ላይ የምትኖር የቀለያትንም (ጥልቅ ባሕርንም) ጥልቀት የምትመለከት ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ፤ አቤቱ ምስጢርን ግለጽልኝ፤ ቃልህንም እናገር ዘንድ፣ ያለመሰልቸት ስለ አንተ እንድመሰክር አንተ አንደበት ሁነኝ አሜን።”
ሁሉን ቻይ ታላቅ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ በቀንና በሌሊት የአንተን መኖር አስታውስና፣ አንተን ሁል ጊዜ በፊቴ አደርግህ ዘንድ ልቤን ምራልኝ፤ በኪሩቤል ላይ የምትኖር የቀለያትንም (ጥልቅ ባሕርንም) ጥልቀት የምትመለከት ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ፤ አቤቱ ምስጢርን ግለጽልኝ፤ ቃልህንም እናገር ዘንድ፣ ያለመሰልቸት ስለ አንተ እንድመሰክር አንተ አንደበት ሁነኝ አሜን።”
†♥† “በምድር
ላይ ኃጢአትን አሰረ፤ በሲዖል ሞትን አሸነፈ፣ በመስቀል ሳለ መርገምን ሻረ፣ በመቃብር ውስጥ ፈርሶ በስብሶ መቅረትን አስቀረ።
(ቅዱስ አትናቴዎስ) †♥†
“መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር” (መስቀል ከሁሉ ነገር በላይ ነው)” (ሊቃውንተ ቤ/ክ)
እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ከፈጠረበት
ጥበቡ በሚበልጥ ዓለምን ሁሉ ያዳነበት ከጥበብ ሁሉ በላይ የሆነ ጥበብ ይህ ቅዱስ መስቀል ነው!”
በቀደም በክፍል ፩ (አንድ) ጽሑፌ መስቀል በመጽሐፍ
ቅዱስ በሦስት ከፍዬ ማሳየቴ ይታወሳል፤ ይህም ፩. መከራ መስቀለ
ክርስቶስ
፪. መከራ መስቀለ ክርስቲያንና
፫. ዕፀ መስቀል
የመጀመሪያውን መስቀል ማለት መከራ መስቀለ ክርስቶስን
መሆኑን በቀደም በጻፍኩት ጽሑፌ በሰፊው የገለጽኩት ሲሆን፤ በክፍል
ሁለቱ (፪)ቱ ደግሞ የቀሩትን ማለትም፡- መስቀል ማለት “መከራ መስቀለ ክርስቲያንና”፣ “ዕፀ መስቀል” በሚሉት ትርጉሞች ላይ ዳግም
ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘን መለያየታችን ይታወሳል።
ክፍል
ሁለት
ደግሞ እነሆ እንደሚከተለው ቀርቧል። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ።
†♥† ፪. “መከራ
መስቀለ ክርስቲያን”፡- ማለት አንድ ክርስቲያን ወይም ሐዋርያ ስለ ክርስቶስ ስም፣ ስለ ወንጌል፣
ስለ ቤተክርስቲያን እድገት፣ ስለ ማህበረ ምዕመናን፣ የሚደርስበት መከራ፣ ስድብ፣ ሐሜት፣ መስቀል ይባላል። ጌታችን መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ሲናገር “መስቀሌን የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለኔ ሊሆን አይገባውም።” ማቴ.፲፡፴፰/10፡38/ በማለት የተናገረው
ለዚህ ነው። በተጨማሪም “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። አለ (ማቴ.፲፮፡፳፬/16፡24/፣
ማር.፰፡፴፬-፴፮/8፡34-36/ ጌታ መስቀሉን ተሸክሞ እንዳለ ቅዱሳን ሰዎች የሚቀበሉት የክርስቶስ ሳይሆን የራሳቸውን ነው። በመሆኑም
ቅዱስ ጴጥሮስ ቁልቁል መሰቀሉ፣ ቅዱስ ጳውሎስ በሰይፍ መመታት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ኢሳያስ በመጋዝ መተርተራቸው የቅዱሳን ሁሉ
ልዩ ልዩ ጸዋተወ መከራ መስቀል ይባላል።