†♥† "ሐነጽዋ
ለቤተ
ክርስቲያን"
(ቤተ
ክርስቲያንን
ሰሯት)
“ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው።”
መዝ.፷፬/፷፭፡፭
†♥† “በኢሩቤል
ላይ የምትኖር የቀለያትንም (ጥልቅ ባሕርንም) ጥልቀት የምትመለከት ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ አቤቱ ምስጢርን ግለጽልን፤ ቃልህንም እንናገር፣
እናስተላልፍም ዘንድ ሁኔታዎችን ሁሉ አመቻችልን።”
†♥† ይህ ዕለት መስከረም ፲፮ (16) ቀን ብቻ ህንጸተ ቤተ ክርስቲያን ይባላል:: በዚህ ቀንም እንደ ሌሎቹ ቀናት ሁሉ አምልኮተ እግዚአብሔር በመዝሙር በቅዳሴ ይደገማል።
የመዝሙሩ
ርዕስ፡- "ሐነጽዋ
ለቤተ
ክርስቲያን"
(ቤተ
ክርስቲያንን
ሰሯት)
በቅዳሴ
ጊዜያትም ፩. በዲያቆኑ (ገባሬ ሰናዩ) 1ቆሮ.3፡1-18 ያለውን ፪. ዲያቆን (ንፍቁ ዲ.) ራዕ.21፡10 ፫ ረዳቱ ቄስ
(ንፍቁ ካ.) ሐዋ.7፡44-51 ያነባሉ።
†♥† ምስባክ፡- በገባሬ ሰናዩ (ዋናው) ዲያቆን የሚሰበከው ምስባክ
ደብረ
ጽዮን ዘአፍቀረ
ሐነጸ
መቅደሶ በአርያም
ወሰረራ
ውስተ ምድር ዘለዓለም
†♥† አማርኛ፡- የወደደውን የጽዮንን ተራራ።
መቅደሱን እንደ አርያም ሠራ፥
ለዘላለምም በምድር ውስጥ መሠረታት።
መዝ.77(78)፡69
†♥† ምስጢር (ትርጉም) ይህ ምስባክ ደ/ጽዮን (ቤተ መቅደስን፣ እመባታችንን፣
ምዕመንን) የወደደ እርሱ እንደወደደ መመስገኛ የምትሆን ቤተ መቅደስን በልዕልና ሰራት፤ እመቤታችንን ለማደሪያው ፈጠራት፤
ምዕመንንም በሞቱ በደሙ ቀድሶ ማደሪያው አደረጋት፤ በዚህ ዓለም (እመቤታችን በክብር ምዕመናን በሕይወት በክብር አጽንቶ ሰራት
የሚያሰኝ ትርጉም የያዘ ነው።
በዚህ
ዕለት የሚነበበው የወንጌል ክፍል (በዋናው ቄስ) ዮሐ.10፡22 እስከ ፍጻሜው ድረስ።