- የስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫና መሰል ጉዳዮች በጥቅምቱ ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ይወሰናል::
- ቅዱስ ሲኖዶስ ከፓትርያርክ ምረጫ ጋር
በተያያዘ ለቤተ ክርስቲያኗ ወሳኝ ጉዳዮችን እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል፡፡
(ደቂቀ
ናቡቴ መስከረም 12/2005) ኢትዮጵያ ታላላቅ ቅዱሳንን ያፈራችበትን ወርቃማ
ዘመንን ለመድገም ከአሁን የተሻለ ታላቅ አጋጣሚ ይመጣል ተብሎ መቼም የሚጠብቅ አይሆንም፡፡ ፈር ያጡት ሰርዓቶቻችን
መስመር የሚይዙበት ፣ ምንም ስርዓት ያልተሰራላቸው ጉዳዮች አዲስ ስርዓት ተዘርግቶላቸው የወደፊት መጭውን እድል
የምትወስንበት ፣ እንደ ግመል ያበጡትን ከፍተኛ ችግሮቻችንን የሚወገዱበት ፣ የምንፈታበት ጊዜ ከዚህ የተለየ አጋጣሚ
ምቹ ሊመጣ? የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ወርቃማዎቹ ጊዜያት ዛሬ ላለነው ትውልድ ሲናፈቁን የሚኖሩ ቢሆንም እንዲህ
ያሉ ትውልድን የምንፈጥረው እጅ ለእጅ ተያይዘን ተከባብረን በአንዲት ቤተክርስቲያን ያለሰለሰ ጥረት ስናደርግ ፣
ስርዓቶቿን ስናስጠብቅና ስንጠብቅ ፣ ማንም እንዳሻው ሲፈነጭ አይቶ ዝም እየተባለ የሚታይበትን ጊዜ ሲከስም መሆነ ግልጽ
ነው፡፡
በዚህ አጋጣሚ ይህ ጊዜ ካለፈን እና መሠረታዊ ችግሮቻችንን ሳናስተካክል የነበረው ስርዓት አለብኝነት
ይቀጥል ብለን ዝም ካልን ግን ምን አልባትም ለቤተክርክስቲያናችን ጥቁር አሻራ አስቀምጠን እንዳልፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ
ማድረግ ይኖርብናል፡፡ በተለይ ደግሞ የዘረኝነትና የፍቅረ ነዋይ ችግሮች መጥራት ካልቻሉ አደጋው የከፋ ይሆናል፡፡
የውስጥ ችግሮቻችን ምንም ብዙ ቢሆኑም ትኩረት ወስድን እያንዳንዱ ስርዓት እንዲስተካከል ካደረግን በአንድ ሀሳብና በአንድ ልብ ሆነን ከውጪ ጠላቶቻችን የሚመጣብንን የሰማዕትነት ጊዜያት እየናፈቅን ብሩህ ዘመንን እያየን በቃለ እግዚአብሔር የታነጸ ታላቅ ዜጋ ፣ ትውልድ የምንፈጥርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡: በዚህ ረገድም የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን አርአያነት ለእኛም ይህ ተስፋ ይሆናል፡፡