†♥†አቡነ ዘርዓ ብሩክ†♥†
አቡነ ዘርዓ ብሩክ የጻድቁ አባታችን የዘርዓ ብሩክ አባት እና እናት የተባረኩ ከቅዱሳን ወገን የሚሆኑ ነበሩ የአባታቸው ስምም ቅዱስ ደመ ክርስቶስ ሲባል እናታቸው ደግሞ ቅድስት ማርያም ሞገሳ ትባላለች ጻድቁ አባታችን ገና በናታቸው ማህጸን እያሉ ነበር ብዙ ተአምራት የሚያደርጉት እግዚአብሄር መርጡአቸዋልና በሁአላም ከክርስቶስ ልደት በሁአላ በስምንተኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ ላይ በነሃሴ 27 ጻድቁ አባታችን ተወለዱ በ40ኛ ቀናቸውም ተጠምቀው በካህናት አፍ "ጸጋ ክርስቶስ" ተባሉ ከዛም ቤተሰቦቻቸው በጥሩ እድገት አሳደጉአቸው 7 አመትም በሞላቸው ግዜ በልጅነቴ የዚን አለም ክፋቱን እንዳላይ ብለው ቢጸልዩ አይናቸው ታውሩአል:ቤተሰቦቻቸውም የዚን አለም ትምህርት ሊያስተምሩአቸው አስተማሪ ጋር ቢወስዱአቸው ታመው ተመልሰዋል።