Monday, November 5, 2012

ዓመታዊ እና ወርሃዊ መታሰቢያ በዓላት


በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።ኢሳ.56:5
ቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው። ምሳ 107 
እግዚአብሄር ለቅዱሳን በቸርነቱ ከሰጣቸው በረከት ለመሳተፍ መታሰቢያቸውን ማድረግ የግድ ነው እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።/ማቴ 1040-46/ ይላልና ይህም የተባለው በነብያት፣ በጻድቃንና  በሌሎችም ቅዱሳን ስም መታሰቢያ ማድረግ እንደሚገባ ለመግለጽ ነው።  
መታሰቢያ አንድ ሰው ለሀገሩ በስራው መልካም ስራ፡ ላበረከተው አስተዋፅኦ በጀግንነቱ ታይቶ በዚህች ኃላፊ ጠፊ ዓለም በስሙ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል ፣መንገድ ተሰርቶለት ሲዘከር ይኖራል ፡፡ እሱ ሕይወት ባይኖርም ስሙ ህያው ሆኖ ሲወሳ ይቆያል፡፡ ሰው ሁሉ እንዲያሲታውሰውም ይደረጋል፡፡ የእነዚህ አርበኝነት ምድራዊ ሃላፊ ጠፊ ነው። የቅዱሳን መታሰቢያ ስንለል ግን ፤ጻድቁን ለማስታወስ በቅዱሱ ስም የሚገነባውን ቤተክርስትያን የሚከበረውን በአል ነው። ምድራዊው መታሰቢያ  ለየት የሚያደርገው ምድራዊ መታሰቢያቸው ከሰው ሳይሆን ከሰማያዊ አምላክ ፈቃድ በመሆኑ ሥራው ነው። ምስጋናና ግርማ ነው፤ ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል። ለተአምራቱ መታሰቢያን አደረገ፤ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው።5 ለሚፈሩት ምግብን ሰጣቸው፤ ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል።መዝ.111:3

Thursday, November 1, 2012

ዜና ሕይወቱ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ

ልደቱ :- የወርቃማው ዘመን ወርቃማ ደራሲ፣ መናኝ፣ ጻድቅ፣ ሊቅ፣ የሕዝብ መምህር እና የሥነ ምሕንድስና ባለሙያ የሆነው አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተወለደው በ1357 ዓመተ ምሕረት በወሎ ክፍለ ሀገር በዛሬው ቦረና በጥንቱ ወለቃ ወረዳ ሸግላ በተባለ ቦታ ነው፡፡ አባቱ ሕዝበ ጽዮን እናቱ እምነ ጽዮን ይባላሉ፡፡ ስለ አባቱ ሕዝበ ጽዮን ሁለት የተለያዩ ታሪኮች ይተረካሉ፡፡ የሰኔ ድርሳነ ዑራኤል ምንባብ አባቱ በመጀመሪያ የትግራይ በማስከተል የሰግላ /ጋሥጫ/ አገር ገዢ እንደነበር ይወሳል፡፡ ገድሉ ደግሞ /ጠቢብ ወማእምረ መጻሕፍት ወአቡሁኒ መፍቀሬ እግዚአብሔር አምኁልቈ ካህናተ ደብተራ ዘውሳጤ ዓጸደ ቤተ ንጉሥ/ አባቱም የእግዚአብሔር ወዳጅና በቤተ መንግሥት በነበረችው ድንኳን /ሥዕል ቤት/ ከሚያገለግሉ ካህናት ወገን ነበረ ይላል፡፡ እንደ ገድሉ ገጸ ምንባብ ትርጉም ሕዝበ ጽዮን ከንጉሡ ሥዕል ቤት በቅዳሴ ወይም በማሕሌት ከሚያገለግሉ ካህናት አንዱ ነው፡፡ /. . . ወእሙኒ እም ሥዩማነ ወለቃ/ እናቱም ከወለቃ ሹማምንት ወገን ነች ይላታል፡፡ ይኸውም የጥንቱ ወለቃ /የዛሬው ደቡብ ወሎ፣ ቦረና ከላላ/ ከነበሩ መኳንንት ወገን መሆኗን ያመለክታል፡፡      የአባ ጊዮርጊስ ወላጆች ልጅ ሳይወልዱ ለረጅም ዓመታት ቆይተዋል፡፡ የልጅ ፍላጎታቸው እንዲሠምር ለሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተሳሉ፡፡ ስእለታቸውም ሥምሮ በመልአኩ ቀዱስ ዑራኤል አብሣሪነት ወንድ ልጅ ወለዱ፡፡ ልጃቸውን ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመማጸን ስለወለዱ ስሙን ጊዮርጊስ ብለው ጠሩት፡፡ ወላጆቹ የታላቁን ሰማዕት ስም ለልጃቸው ያወጡት ወደ ፊት በዓላውያን ነገሥታት ፊት ምስክር፣ አፅራረ አምነትን አሳፋሪ፣ ካህናትንና ምእመናት በየዘመናቱ ከሚነፍሱ የኑፋቄና የክህደት ነፋሳት በወንጌል ብርሃን ነፃ የሚያወጣ ሲሉ ይህን ስም እንዳወጡለት ድርሳነ ዑራኤል እንዲህ ይተርካል፡፡ ‹‹ዘይከውን መምህረ ኵሉ ዓለም ወበጸሎቱ ዘያድኅን አሞተ ሲኦል ፍቁረ ድንግል ማርያም ወላዲቱ ለአማኑኤል፡፡ ወመገሥጾሙ ለነገሥት፡፡ ወፀሮሙ ለዐላውያን ሃይማኖት በሰይፈ ቃሎሙ ለሐዋርያት ዘያጠፍኦሙ እም ብሔረ ኢትዮጵያ፤ ወለካህናተ ጽድቅ ዘይመርሆሙ እምጽልመተ ኑፋቄ መንገለ ብርሃን ቃለ ወንጌሉ ለክርስቶስ በትምህርተ ሕጎሙ ለሐዋርያት›› ይላል፡፡
ትምህርት :-አባ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ደረጃ መንፈሳዊ ትምህርቱን ከወላጅ አባቱ ሕዝበ ጽዮን እንደተማረ ይገመታል፡፡ አባቱ የመጀመሪያ ደረጃ ተምህርቱን ካስተማሩት በኋላ መዐርገ ዲቁና እንዲቀበል ማድረጋቸውን  ገድሉ ይነግረናል፡፡ ወሶበ ልህቀ ሕቀ ወሰዶ ኀበ ጳጳስ ወሴሞ ዲያቆነ፡፡ ባደገም ጊዜ ከጳጳስ ዘንድ ወሰደው ጳጳሱም በዲቁና አሾመው ይላል ገድሉ፡፡ ዲቁና መቀበሉን እንዲ መዓርገ ዲቁና የሰጡትን ጳጳስ ስም አይገልጽም፡፡ ዳሩ ግን መዓርገ ዲቁናን በ1341 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እስከ ዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ አካባቢ ከነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ መተርጉም እንደተቀበለ ይገመታል፡፡
መዓርገ ዲቁና ከተቀበለ በኋላ የአባ ጊዮርጊስ ወላጆች ለታላቅ ሐላፊነት የተመረጠውን ልጃቸውን በዘመኑ የታወቀ የነገረ ሃይማኖት ትምህርት ሊያስተምሩት ለሚችሉ መምህራን መስጠት እንዳለባቸው ወሰኑ፡፡ በወቅቱ ጥልቀት ያለው የነገረ ሃይማኖት ትምህርት ለመማር የሚመረጠው ትምህርት ቤት ሐይቅ እስጠፋኖስ ነበር፡፡ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ በዐፄ ዳዊት /1385 - 1395/ ዘመነ መንግሥት እንደገባ ገድሉ ይገልጣል፡፡ ሐይቅ እስጢፋኖስ የተለያየ ሊቃውንት የሚገኙት፣ በብዙ መጻሕፍት የተሞላውና ዙሪያውን በሐይቅ በመከበቡ የተማሪን ሐሳብ ለማሰባሰብ አመቺ የሆነ ቦታ ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስ በሐይቅ እስጢፋኖስ ትምህርት አልገባው ብሎ ለሰባት ዓመታት ተቀምጦ ነበር፡፡ የትምህርት ቤት ሕይወቱም ከቅዱስ ያሬድ ይመሳሰላል፡፡ ቀዱስ ያሬድ ትምህርት አልገባው ብሎ ሰባት ዓመት እንደተቸገው እንደዚሁ አባ ጊዮርጊስም አብረውት የሚማሩት ተማሪዎች ይህ ትምህርት የማይገባው ስለ ምንድን ነው? በእርሱ ኃጢአት ነው ወይስ በወላጆቹ? ብለው እስከ ሚጠይቁ ድረስ ትምህርት አልገባ ብሎት ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ የሐይቁ መምህር የነበረው ዐቃቤ ሰዓት ሠረቀ ብርሃን ለአባቱ ‹‹ልጅህ ትምህርት አይገባውምና የቤተ መንግሥት ነገር አስተምረው›› ብሎ መለሰው፡፡ አባቱ ሕዝበ ጽዮን ግን ‹‹ አንድ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ አልቀበልህም እዚያው ገዳሙን ያገልግል›› ብሎ እንደገና ላከው፡፡በዚህ ዓይነት መምህሩ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ መልሶ ወሰደውና በጥበብ እድ ሥራ ላይ ተመደበ፡፡ በጥበበ እድ ባከበተው ዕውቀትም እንደ ቅዱስ ላሊበላ ከዐለት ፈልፍሎ ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ ችሏል፡፡ ዛሬ ከዘመን ርዝማኔ የተነሣ ጥገና ባይደረግለትም አባ ጊዮርጊስ ፈልፍሎ ያሠራው ዋሻ ቅኔ ማኅሌት፣ ቅድስት እና መቅደስ ያለው ቤተ ክርስቲያን ብዙ የትሩፋት ሥራ በሠራበት በጋሥጫ ገዳም ይገኛል፡፡ የወለቃን ወንዝ ለመሻገር ያገለግል ዘንድ ከዓለት ፈልፍሎ የሠራው ድልድይም የሥነ ምሕንድስና ሙያው የታየበት አሻራ ነው፡፡አባ ጊዮርጊስ ዕውቀት ስለ ተሠወረው ሁል ጊዜ በሥዕለ ማርያም ሥር እየተንበረከከ ይጸልይ ነበር፡፡ የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም እህል በመፍጨት ያገለግል ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ይፈጭበት የነበረው የድንጋይ ወፍጮ አሁንም በገዳሙ ውስጥ ይገኛል፡፡ አንድ ቀን እመቤታችን ተገለጠችለትና አይዞህ ዕውቀት የተሠወረብህ ትምህርት ስለማይገባህ ሳይሆን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ እንዲገለጥ ነውና ታገሥ አለችው፡፡ ከዚያም ጽዋዐ ልቡና አጠጣችው፡፡ከዚህ በኋላ በሐይቅ እስጢፋኖስ ትምህርቱን በሚገባ ተምሮ አጠናቀቀ፡፡ በዕውቀቱም ቀድሞ የሚያውቁት ሁሉ ይደነቁበት ጀመር፡፡

Wednesday, October 31, 2012

የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጠናቀቀ

ዋና ዋና 
  • የአብነት ትምህርት ቤቶችን ገዳማትንና የካህናት ማሠልጠኛዎችን በበጀት አጠናክሮ በበለጠ እንዲሠሩ ለማድረግ የ10 ሚሊየን ብር በጀት እንዳጸደቀ አመልክቷል፡፡
  • እርቀ ሰላሙ በመጪው ህዳር ወር የሚቀጥል ይሆናል 
  • ቅዱስ ሲኖዶስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለአራት አህጉረ ስብከት እንዲከፈል ወስኗል
  • የአቡነ ጰውሎስ ንብረት በሙሉ ተሰብስቦ ወደ ሙዝየም እንዲገባ ሲኖዶስ ወስኗል
  • ዱስ ሲኖዶስ ለዕርቀ ሰላሙ ውይይት የወከላቸው ሦስት ብጹአን አባቶች ኀዳር 25 ቀን ወደ አሜሪካ አምርተው ውይይቱ ከኀዳር 26-30 ቀን 2005 ዓ.ም በዳላስ ቴክሳስ እንደሚካሄድ ታውቋል:: 
  • የሥርዐተ ምንኵስና አፈጻጸም በየገዳማቱ ሕግ መሠረት ጠብቆ “ልማት እንዲጠናከርባቸው” ይደረጋል::
  •  የካህናት ማሠልጠኛዎች በየክልሉ ይቋቋማሉ፤ በየቋንቋዎቹ የመጽሔቶችና ጋዜጦች ኅትመት ይጀመራል::
  •  
  • †♥† ነገረ ቅዱሳን †♥†


    †በስመ ሥላሴ†
    “ስምከ ሕያው ዘኢይመውት”/”ሰው የተመኘውን ከሰራ የሚጠብቀው ሞቱን ነው”  (አባ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳስ 1932-1982)
     ወበዛቲ ዕለት አዕረፈ አቡነ አላኒቆስ (ጥቅምት ፳፩) (በዚህ ቀን ትልቁ ጻድቅ አቡነ አላኒቆስ አረፈ)።  

    “ከቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር (የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።”) መዝ.፻፲፭/፻፲፮፡፲፭ (115/116፡15

    ሀገራቸው ሸዋ አንኮባር ሲሆን ወግዳ ወይም ምግዳ ይላቸዋል። አባታቸው አጼ ይኩኖ አምላክ እናታቸው ንግስት ኮከቢያ ይባላሉ። የንጉስ ልጅ ሲሆን መናኔ መንግስት ወብእሲት ናቸው። የተወለዱትም በ1238 ዓ.ም ነው። እንቁ ባህርይ የመል የቅዕል ስም አላቸው። ንጉሱ አባታቸው አግባና መንግስቴን ውረስ ሲላቸው እምቢ ብለው ወደ እመቤታችን ስዕል ሄደው ተደፍተው አለቀሱ። እመቤታችንም ክፍልህ ምናኔ ነው ስትላቸው የአባታቸው መንግስት እንደሚያል የእግዚአብሔር መንንግስት ብቻ ነው የማያልፈው ብለው ወደ ወሎ ሐይቅ ሄደው ተናደው ተወርውረው ከባህር ገቡ። በዚያን ጊዜ መላእክት መጥተው አወጡአቸውና አፅናነትው በዚህ ገዳም እንዲቀመጡ ከአበምኔቱ ጋር አገኛቸው። በዚህ ገዳም መንኩሰው ወደ አክሱም ገዳም ሄደው የታቦተ ሙሴ አጣኝ ሆኑ። ትልቁ ታሪካቸውም ጓደኛቸው ከእሳቸው ጋር አብረው የሚኖር መነኩሴ የሚያገለግላቸውም ነበርና በንሰሐ አባትነት የያዟት አንዲት ሴት ነበረች። በዚህ ጊዜ ከአሽከሯ አረገዘች፤ በኋላም በሏ መኮነኑ ከዘመቻ ሲመጣ ከምን አረገዝሽው ብሎ ቢጠይቃትና ቢገርፋት ሲጨንቃት ከንሰሐ አባቴ ነው ያረገዝኩት ብላ ንሰሐ አባቷን በሐሰት ወንጅላ ወስዳ ሰጠችው። ከዚህ በኋላ ያነን መነኩሴ እገድላለሁ ብሎ ወደ ገዳሙ ሄደ። አቡነ አላኒቆስም ይህንን ነገር ሰሙ።  ወደ እኔ ኑ ብለው ጠሩአቸው። ያም በሐሰት የተወነጀለው መነኩሴ ሄዶ ወደ አቡነ አላኒቆስ ተጠግቶ አለቀሰ። ሰገደ ጻድቁም እሷን አስጠርተው ሲጠይቋት ስታፍር አዎን አለች፤ በሐሰት በዚህም ጊዜ ከሱ ከሆነ ይወለድ ከሌላ ከሆነ ግን አይወለድ ብለው ገዘቷትረገሟት፤ በሆዷ ይዛ 22 ዓመት ጢም አውጥቶ ጥርስ አብቅሎ ተወለደ። ህፃኑ ሲወለድም “ወእመሰ እምዘመደ እስራኤል ክብርት እንተ ረስየተኒ ገብረ”  በሎ መሰከረባት። ከዚህ በኋላ ህፃኑንም  አባታችን አሳድገውት ስሙንም አባ ተወልደ መድህን ብለው አመንኩሰው በምናኔ እንዲኖር አድርገውታል። ግድልም አለው፤ ታቦትም አለው። በዕብላ ወረዳ አሉጌን ከተባለው ተራራ ላይ ገዳም አለው። እንግዲህ አባታችን ታሪካቸው እጅግ በጣም ብዙ ነው። ዛሬ ገዳማቸው የሚገኘው ትግራይ ማይበራዝዬ ነው። ይህን ሁሉ ተጋድሎ አድርገው አባታችን በክብር በዛሬዋ ቀን ዐርፈዋል።

    ዮሐንስ ሐጺር



    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን፡፡
    አባ ዮሐንስ ሐጺር ( ጥቅምት  አዕረፈ)

    “ከቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር (የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።”) መዝ.፻፲፭/፻፲፮፡፲፭ (115/116፡15

    እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን፡፡(እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር  ስደተኞችን ይጠብቃል፡፡)“ መዝ.፻፵፭፡፰ (145፡8)

        በዚህች ቀን አባ ዮሐንስ ሐጺር አረፈ።  ቁመቱ አጭር ስለሆነ ነው ዮሐንስ ሐጺር የተባለው። በ18 ዓመቱ በገዳመ አስቄጥስ መንኩሶ በተጋድሎኖረ ሲሆን ይህ አባትነጽሮተ ስሉስ ቅዱስ” የደረሰ አባት ነው።

        እዚህ ደረጃ የደረሱ አባቶች ቀና ቢሉ ሥላሴን ይመለከታሉ ዝቅ ቢሉ እንጦሮጦስን ያያሉ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን የገዳሙ አበምኔት ሊፈትነው ብሎ ደረቅ እንጨት ሰጠው ይህንን ተክለህ አለምልመህ ፍሬውን አምጣልኝ አለው።

        እርሱም እንጨቱን ተከለውና፤ 3 ዓመት ሙሉ ከሩቅ ቦታ ውሃ እየቀዳ አጠጣው።  3ኛው ዓመት ጸደቀ፤ ለመለመ፤ ትልቅ ዛፍም ሆነ፤ ፍሬም አፈራ፤ መነኮሳቱ ይህ የትእግስት ውጤት ነው ብለው ፍሬውን ቀምሰውለታል፡፡

        አንዲትአትናስያ” የምትባል ሴት ነበረች። መጀመሪያ ጻድቅ ነበረች በኋላ ላይ በዝሙት ወደቀች ዘማዊም ሆነች። የቀድሞ ቅድስናዋን የሚያውቁ መነኮሳት ሊመክሯት ቢመጡ ሳቀችባቸው። አሁን ማንን እንላክ ብለው አሰቡ ዮሐንስ ሐጺርን ላኩት። ተራ ሰው መስሎ ገባ፤ ለዝሙት የመጣ መስሏት ተቀበለችው። ተጫወት አለችው ዮሐንስ ሐጺር ማልቀስ ጀመረ ምን ያስለቅስሃል ትለዋለች።