Friday, November 9, 2012

እምሊባኖስ ትወፅእ መርዓት


 ኦ ድንግል አኮ በፍተወተ ደነስ ዘተጸነስኪ ፡፡ ድንግል ዘርዕ ዘይወጽእ እምስካበ ተዓዳዌ ሕግ ይከውን ለቅጥቃጤ ወለሙስና ባለው ፈቃድ የተፀነሽ አይደለሽም፡፡ አላ በሩካቤ ዘበህግ እምሐና ወኢያቄኒም ተወለድኪ ክቡር አውስቦ በኵለሄ ወለምስካቦሙኒ አልቦቱ ስዕበት ባለው ፈቃድ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ፡፡ አንድም እስመ ናሁ በኃጢአት ተፀነስኩ፡፡ ወበአመፃ ወለደተኒ እ...ምየ እንዲል፡፡ በልተው ጠጥተው በሚያደርጉት ፈቲው ጽነት የተፀነስሽ አይደለም፡፡ ብዝኁ ወተባዝኁ ባለው ፈቃድ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ፡፡ ታሪክ የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ቴክታ በጥሪቃ ይባላሉ፤ ይህ ቀራቸው የማይባሉ ባለጸጎች ነበሩ ፤ ብእላቸውም የወርቅ ፤ የብር የፈረስ ፤ የበቅሎ የሴት የባርያ የወንድ ባርያ ነው፡፡ ከወርቁ ብዛት የተነሳ እንደ አምባር እንደ ቀለበት እያሠሩ ከበሬው ከላሙ ቀንድ ያደርጉት ነበር፡፡ ይህን ያህል አቅርንተ ወርቅ ይህን ያህል አቅርንተ ብሩር ተብሎ ይቆጠር ነበር እንጂ የቀረው አይቆጠርም ነበር፡፡ ከእለታት ባንዳቸው ከቤተ መዛግብት ገብቶ የገንዘቡን ብዛት አይቶ ቴክታ እኔ መካን’ አንቺ መካን ይህ ሁሉ ገንዘብ ለማን ይሆናል አላት እግዚአብሔር እንጂ ከኔ ባሰጥህ ወይ ከሌላ ይሰጥህ ይሆናል ፤ አግብተህ አትወልድምን አለችው ይህስ እንዳላደርገው አምላከ እስራኤል ያውቃል አላት፤ በዚህ ጊዜ አዘኑ ወዲያው ራእይ አይተዋል ፤ ነጭ እንቦሳ ከበረታቸው ስትወጣ ፤ እንቦሳቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ስድስት ስትደርስ ፤ ስድስተኛዪቱ ጨረቃን ጨረቃ ፀሐይን ስትወልድ አይተው በሃገራቸው መፈክረ ሕልም አለና ሂደው ነገሩት ፤ ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ ፤ ጨረቃይቱ ከፍጡራን፡፡ በላይ የምትሆን ልጅ ትወልዳላችሁ የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም አንደ ነቢይ አንደ ንጉሥ ያለ ይሆናል አላቸው ጊዜ ይተርጉመው ብለውት ሄዱ፡፡ ከዚህ በኋላ ፀነሰች ፤ ወለደች ስሟን ሄኤሜን ዴርዴን ዴርዴ ቶናን ቶና ሲካርን ሲካር ሄርሜላን፤ ሄርሜላ ሐናን ወለደች፡፡ ሐና አካለ መተን ስታደርስ ከቤተ ይሁዳ ለተወለደ ኢያቄም ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት ፤ ምክነት ወርዶ እንደ አያቶችዋ ሁናለች ብዕሉ ግን በመጠን ሁኑዋል፡፡ ከጎረቤትዋ በዝሙት የምትኖር አንዲት ሴት ነበረች ሐና ዛሬ ቤተ ክርስቲያን እስማለሁ ብዬ ነበር፤ ነገር ግን የምለብሰው ልብስ የለኝም አለቻት፤ እርሱዋም ልብስማ የኔ ካንድ ሁለት ሦስት ልብስ ያለልሽ አይደለም የንን ለብሰሽ አትሄጅም አለቻት፡፡
ያንቺ ልብስ የተሰበሰበ በዐስበ ደነስ በዐስበ ዝሙት ነው፡፡ እግዚአብሔር ንጹሐ ባሕርይ ነው ንጹሕ ነገር ይወዳል ይህን ለብሼ ብለምነው ምን ይሰማኛል ብየ ነዋ አለቻት ሐና እኔ በምን ምክንያት ልጅ ነሳት እያልሁ ሳዝንልሽ እኖር ነበር ለካ አንደ ደንጊያ አድርቆ ያስቀረሽ ይህ ክፋትሽ ነው አለቻት ፤ በዚህ አዝናለች፡፡ አንድም ሁለቱ ሁሉ መሥዋዕት እናቀርባለን ብለው ከቤተ መቅደስ ሄዱ፤ ሊቀ ካህናቱ ሮቤል ይባል ነበር ወይትዌከፍ መሥዋእቶሙ ለመካናት እንጀ ይላል፤ እናንተማ ብዙኁ ወተባዝኁ ብሎ ለአዳም የነገረውን ያስቀረባችሁ ርጉማን አይደላችሁምን ቢጠላችሁ አልነበረምን መሥዋዕታችሁን አልቀበልም ብሏቸው በዚህ እያዘኑ ተመልሰዋል፡፡ አንድም ከአዕሩግ እስራኤል የተወለዱ ሰዎች የሚመገቡት ተረፈ መሥዋእት ነበር ያነን ነስቷቸው እያዘኑ ሲመለሱ ከዛፍ ስር ተቀምጠው አርጋብ ከልጆቻቸው ጋራ ሲጫወቱ ዕፅዋት አብበው አፍርተው አይታ አርጋብን በባሕርያቸው እንዲራቡ ዕፅዋትን አንዲያብቡ እንዲያፈሩ የምታደርግ የኔ ተፈትሮዬ ከደንጊያ ይሆን ልጅ የነሳኸኝ ብላ አዘነች ከቤታቸው ሂደው ወንድ ልጅ ብንወልድ ወጥቶ ወርዶ አርሶ ቆፍሮ ርዳን አንልም ፤ ለቤተ እግዚአብሔር አንጣፊ ፤ ጋራጅ ሁኖ ይኖራል ሴት ብንወልድ ዕንጨት ሰብራ ውኃ ቀድታ ትርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር በሶበ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ትኑር ብለው ብፅአት ገብተዋል የሐምሌ አመ ፴ ዕለት እሷ ለሱ ፀምር ሲያስታጥቁህ መቋምያህ አፍ አፍርታ ፍጥረት ሁሉ ሲመገብ አየሁ ብላ እሱ ለሷዋ ጸዓዳ ርግብ ሰባቱን ሰማያት ሰንጥቃ መጥታ በራስሽ ላይ ስታርፍ በቀኝ ጆሮሽ ገብታ በማሕጸንሽ ስታድር አየሁ ብሎ ያዩትን ሕልም ተጨዋውተዋል፡፡ በሀገራቸው መፈክረ ሕልም አለና ሂደው ነገሩት ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ አላቸው ፤ አንተስ አልፈታኸውም ጊዜ ይፍታው በወለው ተመልሰዋል፡፡ በነሐሴ ሰባት ቀን መልአክ መጥቶ ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ ብሏቸው በብስራተ መልአክ በፈቃደ አምላክ እመቤታችን ተፀነሰች፡፡ በተፀነሰችም ጊዜ ብዙ ተአምራት ተደርጓል፤ በርሴባ የምትባል አክስት ነበረቻት አንድ ዐይና ነች ፤ ሐና እግዚአብሄር በረድኤት ጎበኘሽ መሰለኝ ጡትሽ ጠቁሯል ከንፈርሽ አሯል ብላ ማኅፀኑዋን ዳሳ ዐይኑዋን ብታሸው በርቶላታል፣ ይህን አብነት አድርገው ሕሙማን ሁሉ ማኅፀኑዋን እየዳሰሱ የሚፈወሱ ሆነዋነዋል፡፡
ዳግመኛምሳምናስ የሚባል ያጎትዋ ልጅ ነበር ሞተ፤ ትወደው ስለነበርና ያለጋውን ሸንኮር ይዛ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት ተነስቶ ሰላም ለኪ ኦ እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ ብሎ ከበፈክረ ሕልም የቀረውን ተርጉሞታል፡፡ ከዚህ በኋላ አይሁድ ለምቀንነት አያርፉምና ቀድሞ ከነዚህ ወገን የሚሆኑ ዳዊት ሰሎሞን አርባ አርባ ዘመን እንደ ሰም አቅልጠው አንደ ገል ቀጥቅጠው ገዙን፡፡ ደግሞ ከዚህች የተወለደ እንደምን ያደርገን ይሆን ብለው በጠላትነት ተነሱባቸው፤ መልአክ ኢያቄምን አድባረ ሊባኖስ ይዘሃት ሂድ ብሎት አድባረ ሊባኖስ ሄዳ ወልዳታለች፡ እም ሊባኖስ ትወፅእ መርዓት ያሰኘው ቅሉ ይህ ነው፡፡ ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልሕቂ ከመ ዐዋልደ ዕብራውያን እለያገዝፉ ክሣዶን፡፡ አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተመቅደስ ነበርኪ፡፡ ይቆየን ! (ቅዳሴ ማርያም)
 “እምሊባኖስ ትወፅእ መርዓት … ሙሽራ /እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም/ ከሊባኖስ ትወጣለች” በማለት ጠቢቡ የተናገረው ቃለ ትንቢት ነው፡፡ /መኃ.4፥8/
ፈጣሪያችን ልዑል እግዚአብሔር ለተዋሕዶ ከመረጣት ከዓለመ አንስት ተለይታ በንጽሕና በቅድስና አጊጣ የመመኪያችን ዘውድ ከሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ረድኤት ይክፈለን፡፡ አሜን፡፡

4 comments:

  1. Amen , Kale Hiwot Yasemalen

    ReplyDelete
    Replies
    1. አሜን! ምልጃዋ ይጠብቀን፡ ለመጪው ዓምትም በሰላም አድርሶን ከረድኤትዋ ለመሳተፍ ያብቃን።

      Delete
  2. ቃለ ሕይወት ያሰማልን!!

    ReplyDelete
  3. Best bets for soccer today - Sports Toto
    Today, we're going to tell you 더킹카지노 슬롯 a 토토 사이트 모음 few key to checking into soccer betting apps. of the 메리트 카지노 쿠폰 most popular soccer betting options and which ones 우리카지노 will

    ReplyDelete