Tuesday, January 31, 2012

ግሸን ደብረ ከርቤ

ጥቂት ቆይታ በግሸን ደብረ ከርቤ ከተቀደሰው ተራራ ግማደ መስቀሉ ከሚገኝበት በእግረ ሕሊና እንሂድ እስቲ +++++++++++++እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ረድኤትን ይክፈለን ++++++++++++


Thursday, January 19, 2012

የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነትና አማላጅነት

የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነትና አማላጅነት 
በዲ/ን ሕብረት የሽጥላ
 
እስራኤላውያን በባቢሎን ምርኮ ለበርካታ አመታት በተሰቃዩ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ስለ እነርሱ በግልጽ ቃል ምልጃ አቅርቧል፡፡ ይህም ምልጃው በዚህ መልኩ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቧል፡- ‹‹የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፦ አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ።›› (ዘካ1.12) መልአኩ ይህን ልመና ባቀረበ ጊዜ ‹‹እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው።›› ይላል፡፡ (ዘካ1.13)
ታሪኩን ልብ ብሎ ያነበበ ሰው ይህ ‹‹መልካምና የሚያጽናና ቃል›› ምን ይሆን? ማለቱ አይቀርም፡፡ መቼም ‹‹የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?›› ለሚለው የልመና ቃል ‹‹ምሬአቸዋለሁ ወይም እምራቸዋለሁ›› ከሚል ውጭ የሚያጽናና ቃል ሊኖር አይችልም፡፡ ይህም በግምት የቀረበ ሐሳብ ሳይሆን መልአኩ ለዘካርያስ ባስተላለፈው የመጨረሻ ቃል ይታወቃል፡፡ ‹‹ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ ቤቴ ይሠራባታል በኢየሩሳሌምም ላይ ገመድ ይዘረጋበታል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦ ደግሞም እንዲህ ስትል ስበክ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከተሞቼ ደግሞ በበጎ ነገር ይረካሉ እግዚአብሔርም ደግሞ ጽዮንን ያጽናናል፥ ኢየሩሳሌምንም ደግሞ ይመርጣል።›› ብለህ ስበክ ብሎ ልኮታል፡፡ (ዘካ1.16-17

Wednesday, January 18, 2012

ለጣቱ ቀለበት እሰሩለት ሉቃ.15፤22

ለጣቱ ቀለበት እሰሩለት ሉቃ.15፤22 
በመምህር ተስፋዬ ሞሲሳ
የጠፋው ልጅ  (ሉቃስ 15:11)
አባቴ ሆይ መጥቻለሁ
ይቅር በለኝ በድያለሁ
ይቅር ባይ ነህና የበደሉህን
ቂም እንዳቲዝብኝ በደሌን ቆጥረህ
ስለማይገባኝ ለመባል ልጅህ
ቁጠረኝ እንዳንዱ ከአገልጋዮችህ

አባቴ ሲቆጣኝ አልመለስ ብዬ
ስትመክረኝ እናቴ አልሰማሽም ብዬ
ከወንድሜ ጋራ ሀብቴን ተካፍዬ
ከሰው ሃገር ሄድኩኝ ከአባቴ ተለይቼ

የማይጎዳ መስሎኝ የሃጥያት መከራ
ኮብልዬ ነበረ ወደ ሃጥያት ተራ
አሁንግን ተመለስኩ ጥፋቴን አውቄ
የሰማይ አባት ሆይ ይቅር በለኝ

በአባቴ ቤት ሞልቶ ማርና ወለላ
በአባቴ ቤት ሞልቶ የቅኔው አዝመራ
ሄድኩኝና መንገድ በሰፊው ጎዳና
ናፍቆቱ በዛብኝ ያሬዳዊው ዜማ

እኔም ልብ ስገዛ ስመለስ ከቤቴ
ገና ከሩቅ አይቶኝ ይቅር ባይ አባቴ
ወደኔ ሮጦ አቀፈና ሳመኝ
በልቤ እየገረመኝ ወዲያው መታቀፌ
ትንሽ ሊወቅሰኝ ነው ብዬ ስጠባበቅ
መች እሱ ሊያስታውስ የትላንቱን ዛሬ
ደገመና አዘዘ አዲስ ልብስ ለእራሴ
ደግሞም ቀለበት ለጣቴ ; ጫማንም ለእግሬ

ይቅር ባይ ነህና የበደሉህን
ቂም እንዳቲዝብኝ በደሌን ቆጥረህ
ስለማይገባኝ ለመባል ልጅህ
ቁጠረኝ እንደ አንዱ ከአገልጋዮ