Wednesday, February 22, 2012
Tuesday, February 21, 2012
አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ አብሳዲ አረፉ።
በ1912 የተወለዱት አና በኢትዮጵያ እና በኤርትራ
በክህነታቸው ቤተ ክርስቲያንን ያገለገሉት ብፁእነታቸው ዲቁናን ከብፁዕ አቡነ ይስሃቅ እንዲሁም ቅስናን ከኤርትራው ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ረዳት ሊቀ ጳጳስ በመሆን
ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል እንዲሁም ከግብፅ ከፍሊስጤም እና ከሊባኖስ ያለውን የቤተ ክርስቲያን ፈተና በማቀለል ከፍተኛ አገልግሎትን
ፈፅመዋል ብፁእነታቸው የዕብራየስጢኛ እና የአረቢኛ ቋንቋም ተምረዋል ፡፡
ላለፉት 60 ዓመታት
በኢየሩሳሌም ገዳማት የኖሩትና በእግራቸው ከኢትዮጵያ ወደ ቅድስት አገር የሚጓዙትና ጥንታዊ
ትውፊት ከፈፀሙት አበው መካከል የነበሩት ብፁዕነታቸው በሕመም እና በእርግና ምክንያት በተወለዱ
በ 92 ዓመታቸው የካቲት 10 ለሊት ባደረባቸው ሕመም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል የአባታችንን ነፍስ አምላክ በገነት ያሳርፍልን::
Tuesday, February 14, 2012
«ወዮልኝ፣»
መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው
የእግዚአብሔር ሰዎች «ወዮልኝ፤» እያሉ ራሳቸውን ገሥጸው ይኖራሉ። ጌዴዎን የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ ፊት ለፊት ስላየው ፥ ቃል በቃል ስላነጋገረው፡- «አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ ወዮልኝ፤ የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና፤» ብሎ ነበር። እግዚአብሔርም፡- «ሰላም ለአንተ ይሁን፥ አትፍራ፥ አትሞትም፤» ብሎታል። መሳ ፮፥፳፪። ነቢዩ ኤርምያስም፡- «በሆድ ሳልሠራ አውቄሃለሁ፥ ከማኀፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሐዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ፤» በተባለ ጊዜ፡- «ወዮ ጌታ እግዚአብሔር፥ እነሆ፥ብላቴና ነኝና እናገር ዘንድ አላውቅም፤» ብሏል። ኤር ፩፥፬። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ፦ «ወንጌልን ባልሰብክ ወዮልኝ፤ » ብሏል። ፩ኛ ቆሮ ፱፥፲፮።
እነዚህ «ወዮልኝ፤» ማለታቸው ለእኛ አብነት ነው። ታላላቆቹ እንዲህ ካሉ ከእኛ ከታናናሾቹ የብዙ ብዙ ይጠበቃል። ዕለት ዕለት
«ወዮልኝ፤» እያልን ደረታችንን ልንደቃ፥ እንባችንን ልናፈስስ ይገባል። ሥጋችንን ደስ ከማሰኘት በስተቀር እግዚአብሔርን ደስ
አሰኝተን አናውቅምና። ሰውን ደስ ለማሰኘት በሰውም ዘንድ ለመወደድ (ለውዳሴ ከንቱ) እግዚአብሔርን እናሳዝናለንና። እንኳን
መንፈሳዊ መሆን መምሰሉ እንኳ አቅቶናልና። ሃያ፥ሠላሳ ዓመት ቃለ እግዚአብሔር ዘር ተዘርቶብን፡- ሠላሳ፥ስድሳ፥መቶ ማፍራት
የተሳነን ዘረ ቆርጥሞች ነንና። መቁረባችን ማቁረባችን ፥ መቀደሳችን ፥ ማስቀደሳችን፥ ማሳለማችን፥መሳለማችን፥
መናዘዛችን፥ማናዘዛችን፥ መዘመራችን፥ማዘመራችን፥ መስበካችን፥መሰበካችን ሁሉ ከንቱ ሆኖብናልና። ስለሆነም «እገሌ ሳይገባው
ነው፤» የሚለውን ትተን፡- «እኔ ሳይገባኝ ነውና ወዮልኝ፤» እንበል። የእግዚአብሔር ሰዎች፡- «ወዮላችሁ፤» እስኪባሉ
አይጠብቁምና።
«ወዮላችሁ፤»
የዓለም ሰዎች፡- «ወዮላችሁ፤» እስኪባሉ ይጠብቃሉ፤ ተብለውም አይመለሱም፤ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
የቃሉን ትምህርት ሰምተው፥ የእጁን ተአምራት አይተው ያልተመለሱትን ጸሐፍት ፈሪሳውያንን በአንድ ምዕራፍ ላይ ብቻ ስምንት ጊዜ
«ወዮላችሁ፤» ብሏቸዋል።
ትውፊት
ትውፊት የሚለው ቃል አወፈየ /ሰጠ/ ከሚለው የግእዝ ቃል /ግስ/ የተገኘ ቃል ሲሆን የተሰጠ /የተቀበሉት/
የሚል ትርጉም አለው፡፡ ስለዚህ ሐዋርያዊ ትውፊት ማለት ከሐዋርያት
ጀምሮ በቃል፣ በጽሑፍና በተግባር
ሲፈጸም በመመልከት
ሲወርድ ሲዋረድ ከእኛ ዘንድ የደረሰ የቤተ ክርሰቲያን ትምህርት
እና ሥርዓት ማለት ነው፡፡ ሐዋርያትና
ሌሎቹ የጌታችን
ደቀመዛሙርት ወንጌልን
መጀመሪያ ያስተምሩ
የነበሩት በቃል ነበር፡፡ በኋላ ግን ትምህርቱ
እንዳይጠፋ በማለት በጽሑፍ ጽፈውታል፡፡
ከጻፏቸውም ነገሮች አብዛኞቹ ባለን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ይሁን እንጂ ያልተጻፉ ብዙ ነገር እንዳሉና፣
ከጽሑፋቸውም ውጪ በቃልና በተግባር
ያስተማሩት ብዙ ነገር እንዳለ ራሳቸው ጽፈዋል፡፡ «ጌታችን ኢየሱስም ያደረገው
ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት
ዓለም ራሱ ባልበቃቸው ነበር» /ዮሐ. 21.25/
«በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን
ወግ ያዙ» /2ኛ ተሰ
2.15/
Sunday, February 12, 2012
ድርሳንና ገድል ጥያቄ
ጥያቄ ”በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ጊዜ ድርሳንና ገድል ሲባል እሰማለሁ፡፡ እኔም የድርሳንና የገድል ልዩነት ብዙ ጊዜ አይገባኝም፤ እባካችሁ የድርሳንና የገድልን አንድነትና ልዩነት አስረዱኝ”
ዲ/ን ኅሩይ ባየ
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ጊዜ ድርሳንና ገድል ሲባል እሰማለሁ፡፡ እኔም የድርሳንና የገድል ልዩነት ብዙ ጊዜ አይገባኝም፤ እባካችሁ የድርሳንና የገድልን አንድነትና ልዩነት አስረዱኝ”
ገብረ እግዚአብሔር
ከዲላ
ውድ ጠያቂያችን በእርግጥ እርስዎ እንዳሉት ድርሳንና ገድል በቤተ ክርስቲያን የማይነሡበት ጊዜ የለም፡፡
“የኑሮአቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው” ዕብ.13፥7 እንደተባለው በሃይማኖትና በምግባር ለመጠንከር
ገድለ ቅዱሳንን የያዙ መጻሕፍትን እናነባለን፤ እንጸልይባቸዋለን፡፡ የቅዱሳን መላእክትንም ጠባቂነት፣ የሊቃውንትን
ተግሣጽ ትርጓሜና ምክር የዕለተ ሰንበትን ክብር እና የኢየሱስ ክርስቶስን የቤዛነት ሥራ የሚናገሩ ድርሳናትን ሁል
ጊዜ እናነባለን እናደርሳለን፡፡
Friday, February 10, 2012
ያኔ… /በቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ/!!
(በወንድማችን ገብረእግዚአብሔር)
ያኔ… /በቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ/!!
( በተመስጦ ሆነው ያንቡት)!
በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በደመናው ውስጥ የነበሩት ሦስቱ ደቀ መዛሙርት እንዴት የተባረኩ ናቸው?
Thursday, February 9, 2012
በአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ጭፍን ጥላቻ ቤተ ክርስቲያናችን ተቃጠለች
በአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ጭፍን ጥላቻ ቤተ ክርስቲያናችን ተቃጠለች |
ጆሮም የማይሰማው አይንም የማያየው መቼ የለመ ዛሬ ደግሞ ፕሮቲስታንቱ ቅሰጣቸውን አጠናክርው ቀጥልዋል::
በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት፣ በዲታ ወረዳ፣ ጋና ደሬ ቀበሌ፣ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 29 ቀን 2004 ዓ.ም. ከሌሊቱ በስድስት ሰዓት አካባቢ በእሳት ቤተ ክርስቲያናችን ተቃጠሎአል
ካህናት እና ዲያቆናትእንደታሰሩ ነው
(በወንድማችን ነቢዩ ሰሎሞን)
የስልጢ ቅበት ማርያም አገልገይ ካህናት ዲያቆናት እና አስተዳዳሪ አሁንም እንደታሰሩ ነው ሙሉ ሪፖርቱ ደርሶናል
በክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ከሚደረግባቸውና እንደ አንድ ዜጋ እንኳን ከማይቆጠሩበት ቦታዎች መካከል ስልጢ
ዋናውና ቀዳሚው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በእርግጥ በስልጢ ወረዳ ውስጥ 22 አብያተክርስቲያናት እና ከፍተና ቁጥር
ያለው ምዕመን ቢኖርም እስከአሁን ድረስ ምዕመናን በነጻነት የእግዚአብሔርን ስም እንዳይጠሩ እና በነጻነት
እንዳይንቀሳቀሱ ለኑሮዋቸውም ምንም ዓይነት ዋስትና የሌላቸው መሆኑ በጣም የሚያሳዝን እየሆነ መጥቷል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)