Tuesday, March 20, 2012

የዋልድባ ጉዳይ አበቃለት ማለት ነው?

እንዴት ነው ነገሩ የዋልድባ ጉዳይ አበቃለት ማለት ነው? ትላንት መንግስት ስምምነት ላይ እንደተደረሰ እና ሌላ ሀሳብ ያለው ካለ ግን ብሎ  “ገዳማችን ይህን የሚደግፍ እንጂ የፀረ ሰላም ሀይሎች መሸሸጊያ አይደለም በዋልድባ ገዳም ስም የግል ጥቅማቸውን ለማራመድ የሚሯሯጡ ኃይሎችን እንቃወማለን” በማለት ፓለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ማድረጉ ምን ይሉታል እውን ወደ 18 አብያተ ክርስቲያናትን መንግስት እንዲያፈርስ መነኮሳቱ የሚፈቅዱ የመስለናልን? ይልቁንም ለመሰዋት እንደተዘጋጁ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ በ6/7/04  በቪኦዬ ሪዲዮ የቀረበውን እንስማ


Monday, March 19, 2012

የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዛሬም በደኑ ላይ የእሳት ቃጠሎው በንፋስ ሀይል በጣም እየተባባሰ ነው

የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዛሬም   በደኑ ላይየእሳት ቃጠሎው በንፋስ ሀይል በጣም እየተባባሰ ነው በአሁን ሰዓትም ከፍተኛ እርዳታ እንደሚፈልጉ ገልፀውልናል ቃጠሎው ትላንት ቅዳሜ 08/07/04 እንደጀመረ ለማወቅ ተችሎአል በአሞራ ገደል(የመላእክት ከተማ) አካባቢ መሆኑ እሳቱን ለማጥፋት ከባደ አድርጎታል
 

መንግሥት ከአካባቢው የውኃ ቦቴዎችን እና ወታደሮችን በማንቀሳቀስ ውኃውን ለማጥፋት ጥረት እያደረገ ቢሆንም እሳቱ ግን ወደ ገዳሙ በመጠጋት ላይ ነው፡፡
አሁን አማራጫችን አንድ ብቻ ነው፡፡ የዝቋላን ገዳም ከማጣታችን በፊት ያለንን ነገር ሁሉ ይዘን በተገኘው ትራንስፖርት ወደ ዝቋላ መትመም ብቻ፡፡ ወንበር ማርያም ድረስ የውኃ ቦቴዎቹ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ያለውን ባገኘነው ዕቃ ሁሉ ውኃውን ይዘን በመውጣት መረባረብ፡፡ ያለበለዚያ ግን የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ወደ ታሪክነት ይቀየራል፡፡
እነሆ ክርስትናችን የሚፈተንበት፣ ኢትዮጵያዊነታችንም የሚለካበት ጊዜ መጣ፣ በእሳት ተቃጥለው ያቆዩትን ገዳም ከእሳት ማዳን ካልቻልን እንግዲህ የኛ መኖር ትርጉሙ ምንድን ነው?
 

Sunday, March 18, 2012

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሲኖዳ 3ኛ አረፉ

ደጉን መምህር አውነተኛውን አባት ታታሪዉን ወንጌላዊ ንጹውን መነኮስ አጣናቸው



የቤተ ክርስቲያኗ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትና የቅዱስ ማርቆስ መንበር 117ኛ ፓትርያርክ የቅዱስነታቸው ዕረፍት የታወቀው ትናንት መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ.ም. ነበር፡፡ በሰሜናዊ ግብፅ፣ አስዩት ውስጥ ሐምሌ 27 ቀን 1915 ዓ.ም ሲወለዱ ቅዱስነታቸው በካንሰር ሕመም ምክንያት በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል
 
ታላቅ አባት ቤተ ክርስቲያናችን አጣች አምላክ ነፍሳቸውን በገነት የሳርፍልን
 


Thursday, March 1, 2012

አገልግሎት


አገልግሎት  በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ኤር.48:10 የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚያደግ ርጉም ይሁን፥ ሰይፉንም ከደም የሚከለክል ርጉም ይሁን