ቅዱስ ነአኩቶለአብ ከአባቱ ከቅዱስ ገ/ማርያም ከእናቱ ከንግሥት መርኬዛ ለ1164 ዓ.ም ታህሣሥ 29 ቀን ተወለደ ነአኩቶለአብ ማለት የሰማይ አባታችን እናመሰግነው ማለት ነው፡፡ ልደቱም ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን እንዳበሰረው እሱም የተወለደው በብስራተ ገብርኤል ነው፡፡ ከ11 ነገስታት አንዱ ከ4ቱ ነገስታት(ቅዱስ የምርሐነ ክርስቶስ ቅዱስ ገብረማርያም ቅዱስ ላሊበላና ቅዱስ ነዓኩቶለአብ) ቅዱስ የሚባል ስም የተሰጠው ካህን ወንጉስ ቅዱስ ነአኩቶለአብ እስካሁን ድረስ በህይወት ያለ ለወደፊት በሀይማኖቱ እንደኤልያስና እንደሄኖክ ስለቅዱሳን አማላጅነት መስክሮ የሚሞት እስከ አሁን በብሄረ ህያዋን ያለ በንግስና 40 ዓመት የቆየ ስውር ጻድቅ ነው፡፡ እናትና አባቱ በህፃንነቱ ነበር የሞቱበት፡፡ ነገር ግን የቃልኪዳን አባት ቅዱስ ላሊበላ ከቤተ መንግስቱ ወስዶት በጥሩ ሁኔታ ስርዓተ መንግስቱን እየተመለከተ አደገ፡፡
Tuesday, August 28, 2012
ቅዱስ ነአኩቶለአብ
ቅዱስ ነአኩቶለአብ ከአባቱ ከቅዱስ ገ/ማርያም ከእናቱ ከንግሥት መርኬዛ ለ1164 ዓ.ም ታህሣሥ 29 ቀን ተወለደ ነአኩቶለአብ ማለት የሰማይ አባታችን እናመሰግነው ማለት ነው፡፡ ልደቱም ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን እንዳበሰረው እሱም የተወለደው በብስራተ ገብርኤል ነው፡፡ ከ11 ነገስታት አንዱ ከ4ቱ ነገስታት(ቅዱስ የምርሐነ ክርስቶስ ቅዱስ ገብረማርያም ቅዱስ ላሊበላና ቅዱስ ነዓኩቶለአብ) ቅዱስ የሚባል ስም የተሰጠው ካህን ወንጉስ ቅዱስ ነአኩቶለአብ እስካሁን ድረስ በህይወት ያለ ለወደፊት በሀይማኖቱ እንደኤልያስና እንደሄኖክ ስለቅዱሳን አማላጅነት መስክሮ የሚሞት እስከ አሁን በብሄረ ህያዋን ያለ በንግስና 40 ዓመት የቆየ ስውር ጻድቅ ነው፡፡ እናትና አባቱ በህፃንነቱ ነበር የሞቱበት፡፡ ነገር ግን የቃልኪዳን አባት ቅዱስ ላሊበላ ከቤተ መንግስቱ ወስዶት በጥሩ ሁኔታ ስርዓተ መንግስቱን እየተመለከተ አደገ፡፡
Friday, August 24, 2012
ኑዛዜ
በዲ/ን ሕብረት የሽጥላ
- ራስን ለካህን ማሳየት ይገባል::
- ኃጢአትን ለካህን መናገር አይገባም ለሚሉ::
ይህንን ልናስደምጣችሁ
የፈለግንው መናፍቃን እና ፕሮቴስታንት ተሓድሶዎች ኃጢአትን ለካህን
መናገር አያስፍልግም መጸሃፍ ቅዱሳዊ አይደለም ለሚሉ መልስ ስለሚያስፈልጋቸው ነው፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ከተወገዙት ተሐድሶዎች ውስጥ
አሸናፊ መኮንን አሁንም ይህንኑ እያለ እያሳተበት ስለሆነ እና ለሁላችንም ኃጢአትን ለካህን መናገር እንደሚገባን እንድንረዳ ስለሚያስፈልግ
ነው፡፡
ለዲ/ን ሕብረት የሽጥላ
ቃለህይወትን ያሰማልን አሜን::
የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደሪ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው
የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደሪ
ሊቀ ብርሃናት ተ/ማርያም መንገሻ ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 11/2004 ዓ.ም ሌሊት 6፡00 ሰዓት ላይ የፍልሰታን ሰአታት ለመቆም ወደ ቤተ ክርስቲያን በሚሄዱበት ሰአት እዚያው በቤተ ክረስስቲያኑ ቅጥር ግቢ ሁለት የደብሩ አገልጋዮች እንደደበደባቸውና በመሀልም የተመለከቱ ሰዎች በመጮሃቸው ምክነያት የደብሩ
ጠበቃዎች መሳሪያቸውን በመተኮሳቸው የተነሳ ፓሊስ ደርሶ ሊተርፉ እንደቻሉ እና ከደብሩ አስተዳዳሪ ጋር ጠብ ይኖራቸዋል ተባለው የተገመቱ
የታሰሩ ሲሆን ከትላንት በስቲያ ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሳቸው የታየ ሲሆን ከግድያ ሙከራው የሉበትም ተብለው የታሰሩ የነበሩትን
የደብሩ አገልጋዮችን በዋስ የፈታ ሲሆን በወንጀሉ እጃቸው አለበት ብሎ ያመነባቸውን በእስር እንዲቆዩ ሆኗል፡፡
ደብዳቢዎቹ ጳጳሱ ከሚገቡበት ጉድጓድ አንተም ተገባለህ
እያሉ እንደደበደቧቸው እና ሊገድሏቸው እንዳሰቡ ያገኘንው መረጃ ያስረዳል ፡፡
Thursday, August 23, 2012
የብጹዕ አባታችን አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነስርአታቸው ተፈፅሟል አጠር ያለ የህይወት ታሪካቸውንም ያድምጡት
የታላቁ
ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ እና ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቀ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ
ዘመንበረ ተክለሓይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዘዳንት እና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር
ፕሬዘዳንት ሥርአተ ቀብር የተፈፀመበት ቀን አንድ መሆኑ እንድምታው ምንድነው?
የአለቃ አያሌው ታምሩ የሥርአተ ቀብር የተፈፀመበት ቀን 17/12/1999 ዓ.ም ሐሙስ
ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቀ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሓይማኖት
የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዘዳንት እና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዘዳንት 17/12/2004
ሐሙስ
Wednesday, August 22, 2012
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ፓሮቴስታንታዊ መሪ አስተናገደች
"†♥†ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥"ኢሳ.60፡12
ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋህዶ ሃይማኖት መቼም የማይነጣጠሉ ነበር ዛሬ ዛሬ ግን ቤተ ክርስቲያናችን ተሰሚነቷ እየቀነስ አመራሩ አካል ጫና እያሳደረባት
እና ቤተ ክርስቲያኗ እንኳን ሲቃጠሉ ሀይ ባይ እያጣች መጥቶ ዛሬ ደግሞ ይህ አልበቃ ብሎ ኢትዮጵያ እና ኦርቶዶክስ ተፋተው
የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ መሪ ለማስተናገድ በቃች፡፡
መቼም ሁላችሁም እንደምትገምቱት
ሐይለማርያም ብሎ ፓሮቴስታንት አይኖርም አይደረግም ብላችሁ ተገምቱ ይሆናል ነገር ግን በደቡቡ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንሰራፍ
ያለው የፕሮቴስታንት እምነት ወደድንም ጠላንም አሁን መሪ የተባሉትን ጠቅላይ ሚንስቴር ሀይለ ማርያም ደሳለኝን ሳይቀር ሰለባ አድርጓቸዋል፡፡ ወላይታና አካባቢውም ቢሆን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን
ተኩረት ባለመስጠቷ ብዙዎቹ ካደጉባት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዋን
ባለመረዳት ኮብልለዋል፡፡ እግዚአብሔር ወደ እናት ቤታቸው እስኪመልስልን ልንፀልይ ይገባል
እኛ የምንሰራቸው የቤተ ክርስቲያናችን ስራዎች ግን በዝተዋል
፡፡
“ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ” እንዲሉ
በምንኩስና ከዓለም መለየት እና የምነኩስና ቆብ፡፡
ምንኩስናና
በምንኩስና ከዓለም መለየት
ምንኩስና ማለት አንድ ልብ አንድ
ሐሳብ ሆኖ እግዚአብሔርን በማገልገልና እሱን ብቻ በማሰብ ተወስኖ መላእክትን በመምሰል ከዓለማዊው ተድላ ደስታ መለየት ማለት
ነው እንጂ ሰው መሆንን ለመርሳት ወይም ለመተው አይደለም፡፡ ይህም ይታወቅ ዘንድ ሐዋርያ ጳውሎስ " ወበኅቤየስ ምውት
ዓለም ወአነሂ ምውት በኅበ ዓለም በኔ ዘንድ የሞተ ነው፡ እኔም በዓለም ዘንድ የሞትኩ ነኝ ብሏል፡፡ ገላ 6፡ ፡14
ሞት ማለትም መለየት ማለት ነው እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም፡ "አኮኑ
ወዳዕነ ሞትነ እምኃጢአት እፎ እንከንክል ሐይወ ባቲ" ከኃጢአት ፈጽመን ተለይተናል እንግዲህ በኃጢአት መኖር እንዴት
እንችላለን እንዳለ:: ሮሜ 6፡2
በምንኩስና ከዓለማዊ ግብር
መለየትም ፍጹም ለመሆን ነው እንጂ በዓለማዊ ግብር ሆኖ እግዚአብሔርን ማገልገል አይቻልም ማለት አይደለም በዓለማዊ ግብር ሆነው
የታዘዘውን ሕግ ፈጽመው ከጸደቁ ዓለማውያን እነ ኖኅ አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ሄኖክ ኢዮብን የመሳሰሉ አሉ ማቴ 22 ፡ 32፡፡
ያዕ፡5:11:ዕብ፡11፡ 5፡6፡፡
Monday, August 20, 2012
የጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ ሆኗል መግለጫውንም እንዲህ ሰማን
" ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።"ዮሐ.1:3
PM Meles Zenawi has died. The long lasting discussion of his whereabouts are rested now. Ethiopia lost two of its powerful leaders: the premier and the patriarch. It is amazing time. May God rest their souls. Amenዛሬ ማለዳ ነሐሴ 15,2004ዓ/ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ አድርጓል::
ይህንንም ተከትሎ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ Haile Mariam Desalegne named acting Prime Minister
Subscribe to:
Posts (Atom)