በቪሲዲ ከተደገፈ መረጃ ጋር
ፕሮቴስታንት እምነቱ ይህ ነው ሥርዓቱም ይህ ነው ለማለት አይቻለም ይልቁንም
በአብዛኛው የራሳቸው የሆነ ወጥ ሥርዓት የሌላቸው በመሆናቸው ማንነታቸውን በትርጉም በትክክል ለመግለጥ ሁልጊዜ አስቸጋሪ ሆኖ ይኖራል፡፡ በአብዛኛውም ግሎባላይዜሽን ባመጣው
አዳዲስ ኩነቶች እራሳቸውን በማመሳሰልና ጊዜውን በመምሰል የሚያክላቸው
እስካሁን አልተገኘም፡፡
ይሁን እንጂ “መቃወም” “ተቃውሞአዊ” ጠባይ የሚያይልባቸው መሆኑን ከአንዳንድ መረጃዎች መረዳት ይቻላል በየጊዜውም
የሚነሡት ሁሉ ከእነርሱ በፊት የነበረውን ትምህርት እየተቃወሙ በየጊዜው አዳዲስ ትምህርት እንዲያመጡና ክፍልፋያቸው (Denomination)
እንዲበዛ አድርገዋል፡፡
በዚህ ጊዜ ውስጥ
መሠረታዊና እውነተኛ ትምህርተ ሀይማኖት እንዲኖራቸው ከምክንያቶቻችን ይልቅ በመገለጥ ሃይማኖት አምነው ትምህረተ ሥላሴን እንዲቀበሉ ያደርጉ ሰዎችም እንደ ተነሱ
ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ በዓለም ላይ ከደረሱትም ጉዳት አንዱ የሰውን
ምግባር (moral) መለወጥና እንስሳዊና ሰይጣናዊ ማድረግ ነው፡፡
እስካሁንም በነበራቸው
አካሄድ “እግዚአብሔርን እናመሰግንበታለን”
የሚሉት “መዝሙራቸው” ዘመናዊ ዘፈን እንደሆነ የራሳቸው ሰው የተናገረውን እናነሳለን “ለእኛ
እንደ ኢትዮጵያ ክርስቲያኖች የሚያስፈልገን ሽብሸባ እንጂ ዳንስ ሊሆን
አይገባም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዓለም ከታወቀችበት ትውፊቶች የራሷ የሆነ አገራዊ ዝማሬ ያላት መሆኑ ነው፡፡ ይህም
ብዙዎቻችን የምንወደው ያሬዳዊ ዝማሬ ነው ያሬዳዊ ዝማሬ ለብዙዎቻችን የምንወደው ያሬዳዊ ዝማሬ ለብዙ የኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ የሚሰጠው
ምልክት ቀውስ ዳንስ ወይም ጭፈራ ሳይሆን አምልኮ ነው፡፡ ብዙዎቻችን የበገናን ስንትርትር ዜማ ስንሰማ ልባችን ይቀልጣል እንግዲያው
እግዚአብሔር በባህላችን ውስጥ ባስቀመጠው በዚህ መልካም ነገር ተጠቅመን ለማገልግልና ለማነጽ ብንሞክር መልካም ይመስለኛል፡፡ ቀናነት ካለን!” በማለት ብሶቱን አሰምቷል ዳንሳቸው እያደረሰ ያለውን ጉዳት ቀውስ ብሎ በመጥራት
ገልጦታል፡፡ ይህ ግርማዊ የተባለ ፀሐፊ የብልፅግና ወንጌል ብሎ በ1992
ባሳተመው መጸሐፍ ላይ የተገለጸ ሲሆን ዛሬ ላይ ደግሞ ሰሞኑን ባሳተሙት የመዝሙር ካሴቶች ቅዱስ ያሬድን ሊያስተዋውቁን እንዲህ ዳዳቸው፡፡ “ለቀባሪው
አረዱት” እንዲሉ:: ይህን ቪሲዲ ይመልከቱ