†♥†በሰመአብ ወወልድ
ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን†♥†
†♥†እንኳን ለአባታችን ለጻድቁ
አቡነ ተክለ ሃይማኖት የበዓላቸው መታሰቢያ በሰላም
አደረሰን።†♥†
“ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል እውነት እላችኋለሁ ማንም
ከእነዚህ ከታናናሾቹ
ለአንዱ ቀዝቃዛ
ጽዋ ውኃ
ብቻ በደቀ
መዝሙር ስም
የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው
አይጠፋበትም። "
የማቴዎስ ወንጌል ፲፡፵-፵፪ (10፥40-42)
†♥† ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ†♥†
የጸድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል መዝ.111፡1-6 ምሳሌ 10፡7 ማቴ. 10፡40-42
ቅድመ ዓለም ዘሀሎ አለም ከመፈጠሩ በፊት ለነበረ ለእግዚአብሔር
አብ እና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ለለበሰ ለእግዚአብሔር ወልድ እንዲሁም ከእነሱ ባለመራቅ ለሚኖር ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፡፡ የአባቴ የጻድቁ አቡነ
ተክለ ሃይማኖት ነገር እና መልክአ በማብዛት አይደለም በማሳነስ በማስረዘም አይደለም በማሳጠር እንድጽፍ ያነሳሳኝ ክብርና
ምስጋና ጌትነትና ውዳሴ ይገባዋል አሜን በእውነት፡፡
†♥†አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ክልል ከአባታቸው ከካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት እግዚእ ኃረያ መጋቢት ፳፬ ቀን ተፀንሰው፤ በ፲፩፻፺፯ ዓ.ም ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስት ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ ወርደው «አሐዱ አብ ቅዱስ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ» ብለው ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ትርጓሜውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ ተክለ ሃይማኖት ማለት ደግሞ ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡