Monday, October 22, 2012

አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?

" በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች  ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ  የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው ኢየሱስም። አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት እናቱም ለአገልጋዮቹ። የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው። አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። ኢየሱስም። ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው። አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም። አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ። ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው። ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ። " ዮሐ.2:1-11
አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ? ማለት ምን ማለት ነው ? በውኑ ይህ ስድብ ነውን ? ብዙዎች የዚህን ቃል ትርጉም ባለመረዳት ሲስቱ ይስተዋላል:: የቃሉን ትርጉም እና ምንነት ከማየታችን በፊት ስለእመቤታችን ድንግል ማርያም ከፍጥረት ሁሉ ልዩ ክብር እንዳላት ጥቂት እንበል:: እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማይጠረጠር መልኩ ከፍጥረት ሁሉ ልዩ ናት፡፡ በድንግልና ላይ እናትነት፣ በክብረ ድንግልና ላይ ክብረ ወሊድ፣ በድንጋሌ ሥጋ ላይ ድንጋሌ ነፍስና ድንጋሌ ኅሊና የተሰጠው ከእርሷ በቀር ማንም የለም፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፤ ከፍጥረት ወገን እንደ እመቤታችን እርሱን ለማወቅ የተቻለው ፍጥረት የለም፡፡ በሉቃስ ወንጌል ትርጓሜው ላይ እንደገለጸው ስለ አምላክ ፍጥረት ሊያውቀው የሚቻለው የመጨረሻው የእውቀት ደረጃ ላይ የደረሰችው እመቤታችን ብቻ ናት፡፡ እንደ እርሱ ትርጓሜ እመቤታችን ፍጡር ለፈጣሪው ክብር ሊጨምርለት እንደማይቻለው እያወቀች  ‹‹ተዐብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር››‹‹ነፍሴ እግዚአብሔርን ታከብረዋለች›› ያለችው ፍጡር ሊረዳው የሚቻለው የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሳ በዚያ መጠን ማመሰገኗን ስትገልጽልን ነዉ ይላል፡፡

Friday, October 19, 2012

ሳይቃጠል በቅጠል

(የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ) አንጋፋዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በብዙ ሚልዮን የሚቆጠር ተከታይ ምእመናን እንዳሏት ይታመናል፡፡ ይህች አንጋፋና ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ጥንተ ሥልጣኔ መሠረት ስትኾን ለኢትዮጵያ የቱሪስት መዲናነት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ እና መሠረት እንደኾነችም ማንም የሚስማማበት እውነት ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን የኢትዮጵያ ሕዝብ እምነቱን እንዲያከብር፣ ባህሉንና ቅርሱን እንዲከባከብ በሥነ ምግባር በግብረ ገብነት የታነጸ እንዲኾን ያበረከተችው አስተዋፅኦም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይማኖቱን ጠባቂነትና ባህሉን አክባሪነት በምስክርነት እንድትጠቀስ አድርጓታል፡፡ በዚህ መስክም ቤተ ክርስቲያኒቱ ከክርስትና እምነት ተከታዮች ውጭ የኾኑ ወገኖችንም በፍቅርና በክብካቤ በመያዝ ፍቅርን፣ አንድነትንና መቻቻልን በተግባር የሰበከች ስትኾን በውጤቱም ለኢትዮጵያ የእምነቶች መቻቻል ቁልፍ ሚና የተጫወተች አንጋፋና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን ነች፡፡

ብሔራዊት የኾነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ወንጌልን ለመላው ሕዝብ ከማዳረስ አንጻር በከተማ ያልተወሰነች፣ በየገጠሩ የሚገኙ ሕዝቦችን በስብከተ ወንጌል በመማረክ ተከታዮቿ ያደረገች በውጤቱም በመላ ሀገሪቱ ለመስፋፋት የቻለች ስትኾን በክርስትና እምነት ውስጥ ያሉ ወገኖችም በሰላም፣ በመፈቃቀርና በመቻቻል ከሌሎችም ወገኖች ጋራ መኖር እንዲችሉ ያስተማረች እናት ቤተ ክርስቲያን ነች፡፡

Thursday, October 18, 2012

†♥†አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ†♥†



“በስመ ሥላሴ”
እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን፡፡(እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር  ስደተኞችን ይጠብቃል፡፡)“ መዝ.፻፵፭፡፰ (145፡8)
አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ

ኢትዮጵያዊው አባት አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባቱ መልዓከ ምክሩ እናቱ ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለደበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ይባላል፡፡ በዚያች ሀገር እግዚአብሔርን የሚፈራ ስሙ መልዓከ ምክሩ የሚባል ደግ ሰው ባለቤቱም ወለተ ማርያም ሁለቱም ደጋጎች እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው በእግዚአብሔር ህግ ጸንተው የሚኖሩ መልካም ስራን በመስራት እንደ ዘካርያስና ኤልሳጴጥ እውነተኞች ነበሩ፡፡ሁለት ደጋጎች ልጆችም አሏቸው የተባረከ መልካም ፍሬን የሚያፈራ በመጾም በመጸለይ እግዚአብሔርን የሚያገለግል በጸሎቱ ሰውን የሚጠቅም በጻድቃንም ዘንድ የተመረጠ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ዘወትር ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ድንግል ማርያም ይለምኑ ነበር፡፡

†♥†"ቤተ ክርስቲያን" †♥†



"ቤተ ክርስቲያን"

ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ወገኖች፣ ለጸሎትና ለምስጋና ለስግደትና ለቁርባን የሚሰበሰቡበት ታቦትና መስቀል፣ ሥዕልና ንዋየ ቅዱሳን ያለበት የክርስቲያን ቤት ናት። ይችውም ባለሦስት ክፍል ሕንጻ ቤተክርስቲያን ስትሆን እኒህም ቅኔ ማህሌት፣ ቅድስት እና መቅደስ ናቸው።   
በክርስቶስ ያመነ ያመነች  ምእመን ምእመንት ሰውነት ቤተ ክርስቲያን (መቅደሰ እግዚአብሔር) ይባላሉ።  ጉባኤ ምዕመናን ቤተ ክርስቲያን። ቤተ ክርስቲያን ተተበብለሎ የተተረጎመው አቅሌሲያ የሚል የግሪክ ቃል ነው። “አቅሌሲያ” ማኀበር ወይም ጉባኤ ተብሎ ይተረጎማል።
“ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል...” ማቴ. ፳፩፡፲፫ (21፡13)
ስለ ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጽሐፍትና ቅዱሳን አባቶች በብዙ መንገድ ተርጉመውታል።
“ቤተ ክርስቲያን ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ የምታደርገን የልዑል እግዚአብሔር ደጅ ናት።” (መ/ዲዲስቅሊያ)   

Sunday, October 14, 2012

†♥† “እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን፡፡“ (እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፡፡)“”†♥† መዝ.፻፵፭፡፰ (145፡8)



በስመ ሥላሴ
 ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ (የጸድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል።)መዝ.111፡6
ቅድመ ዓለም ዘሀሎ አለም ከመፈጠሩ በፊት ለነበረ ለእግዚአብሔር አብ እና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ለለበሰ ለእግዚአብሔር ወልድ እንዲሁም ከእነሱ ባለመራቅ ለሚኖር  ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፡፡ ስለ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በማብዛት አይደለም በማሳነስ በማስረዘም አይደለም በማሳጠር እንድጽፍ ያነሳሳኝ እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ጌትነትና ውዳሴ ይገባዋል አሜን በእውነት፡፡
እንኳን ለጻድቁ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ  ዓመታዊ ክብረ በዓል፣ እንዲሁም ጴጥሮስጳውሎስ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡
እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን፡፡(እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር  ስደተኞችን ይጠብቃል፡፡)“ መዝ.፻፵፭፡፰ (145፡8)
አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሀጋራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ፡ ይባላሉ፡፡ ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች፡፡ በዚሁ መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ተጸንሰው ታህሳስ 29 ተወለዱ፡፡ ዓይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ተነስተው “ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽ ልመት ውስተ ብረሃን” ብለው በማመስገናቸው ኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን ይመስላሉ፡፡

Friday, October 12, 2012

♥†♥ቅድስ ነአኩቶ ለአብ (፩ሺ፪፻፩ ዓ.ም/1201 ዓ.ም/♥†♥

በስመ ሥላሴ

ስለ እመቤታችን፣ ስለሐዋርያት፣ ስለነገስታት፣ ስለጻድቃን፣ ስለሰማዕታት፣ ስለ ቅዱሳን መላእክት በአጠቃላይ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እንወቅ፣ እንመርምር፣ እንጠይቅ፣እንማማር ለዚህም እግዚአብሔር አምላክ እዝነ ልቦናችንን ይክፈትልን፤ ያዲስ ኪዳን ኪሩብ የጸጋ መፍሰሻ ምልዕተ ክብር ምልዕተ ውዳሴ የሆነች እመቤታችን ድንግል ማርያም ምስጢር ትግለጥልን አሜን!!!
እንኳን ለእመቤታችን በዓታ ለማርያም፣ነአኩቶ ለአብ፣ፋኑኤል መልአክ፣አቡነ ዜና ማርቆስ፣ እንዲሁም አባ ሊባኖስ ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ አሜን።
ቅዱሳን ጻድቃን መላ ዘመናቸውን  ከጣዕመ ዓለምና ከተድላ ዓለም ተለይቶ ቤት ልስራ ዘር ልዝራ ሳይሉ ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው አስገዝተው በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በምናኔ ጸንተው የኖሩ ናቸው።
አኗኗራቸው ድምጸ አራዊቱን ጸብዓ አጋንንቱን ግርማ ሌሊቱን ሳይሳቀቁ ደዋ ጥሰው፣ ደንጋይ ተንተርሰው፣ ጤዛ ልሰው ነው። ይህን ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ።” በማለት በዕብ.11፡37-38 የገለጸው።
ቅድስ ነአኩቶ ለአብ (፩ሺ፪፻፩ ዓ.ም/1201 ዓ.ም/

†♥†አቡነ ዜና ማርቆስ በ፲፫ኛ/13ኛው/ መቶ ክ/ዘማን)†♥†

በስመ ሥላሴ

እንኳን ለእመቤታችን በዓታ ለማርያም፣ ነአኩቶ ለአብ፣ፋኑኤል መልአክ፣አቡነ ዜና ማርቆስ፣ እንዲሁም አባ ሊባኖስ ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ
 አቡነ ዜና ማርቆስ  በ፲፫ኛ/13ኛው/ መቶ ክ/ዘማን)
ስለ እመቤታችን፣ ስለሐዋርያት፣ ስለነገስታት፣ ስለጻድቃን፣ ስለሰማዕታት፣ ስለ ቅዱሳን መላእክት በአጠቃላይ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እንወቅ፣ እንመርምር፣ እንጠይቅ፣እንማማር ለዚህም እግዚአብሔር አምላክ እዝነ ልቦናችንን ይክፈትልን፤ የአዲስ ኪዳን ኪሩብ የጸጋ መፍሰሻ ምልዕተ ክብር ምልዕተ ውዳሴ የሆነች እመቤታችን ድንግል ማርያም ምስጢር ትግለጥልን አሜን!!!
ቅዱሳን ጻድቃን መላ ዘመናቸውን  ከጣዕመ ዓለምና ከተድላ ዓለም ተለይቶ ቤት ልስራ ዘር ልዝራ ሳይሉ ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው አስገዝተው በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በምናኔ ጸንተው የኖሩ ናቸው።
ቅዱስ አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ ሀገራቸው ዞረሬ /ጽላልሽ/ ነው። አባታቸው ካህን ዮሃንስ የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት የአቡነ ጸጋዘአብ ወንድም ነው። እናታቸው ዲቦራ (ማርያም ዘመዳ ትባላለች። የአቡነ ቀዎስጦስ እህት ናት። በብስቃረ ማርቆስ ወንጌላዊ ህዳር ፳፬  /24/ ተወልዷል። አርባ ቀን ሲሞላው ሊያስጠምቋቸው ቤተ ክርስቲያን ወሰዷቸው። ጸሎተ ጥምቀቱ ደርሶ ከውሃ ውስጥ ሲከቷቸው ቆመው እሰግ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብለው 3 ጊዜ ሰግዶአል። ውሃው ፈላ አጥማቂው ቄስ  የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት የአቡነ ጸጋዘአብ ወንድም ካህኑ እንድርያስ ነበር። እድሜው 72 ዓመት ስለነበር በሕፃኑ ድርጊት ፈርቶ ወደ ቤተ መቅደስ ሮጠ። ቅዱስ ሩፋኤ ከፍርሃቱ አጽናንቶት ከማየ ጸሎቱ ራሱን እንዲቀባ ነግሮት በራ የነበረ ራሱ ጸጉር በቅሎለታል።አቡነ ዜና ማርቆስ 5 ዓመት ሲሞላቸው ወላጆቻቸው ለመምህር ሰጧቸው። በ 3 ዓመት ብሉይንና ሐዲስ አጥንተው በ8 ዓመታቸው ከቅዱስ ቄርሎስ ድቁና ተቀብለው ሲመጡ ሽፍቶች የእጃቸውን በትር ነእሳቸውም ወደ ጌታ ቢያመለክቱ በትራቸው እባብ ሆና ነድፋ ገድላቸዋለች።  30 ዓመት ሲሆናቸው ማርያም ክብራ ለምትባል ደግ ሴት አጋቧቸው። ልማደ መርዓዊ ወመርዓት (ሙሽራውና ሙሽራይቱ)  ያድርሱ ብለው መጋረጃ ሲጥሉባቸው  በሌሊት ወጥተው ሄዱ። መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ሀገረ ምሑር አድርሷቸውዋል። በዛም የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በመጥራታቸውና  ከንጉሱ (ሀገረ ገዢው) አብላኝ በማለታቸው የኔ አምላክ ማኮስ ነው ኢየሱስ የምትለው ማን ነው ቢላቸው አምላካችን ነው ቢሏቸው ወስዶ ቤተ ጣዖት ቢያሳያቸው ወስደው በእግር ረግጠው አሰጠሙት።  መስፍኑ ተቆጥቶ አሰራቸው። መልአኩም ከእስራታቸው ፈቷቸዋል። እንዲያበላቸው ዳግም ሀገረ ገዢውን ቢጠይቁት ተናዶ በጦር ሊወጋቸው ሲል ምድር አፏን ከፍታ ባሕር ሆና አሰጠመችው። እንዲህ እያሉ ብዙ ስለ ጌታ መስክረዋል።