✙በስመ ሥላሴ✙
✙†♥†ፈጣን ደመና†♥†✙
✙ነቢዩ
ኢሳይያስ በመንፈስ እግዚአብሔር እየተቃኘ ቅድስት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ዐማኑኤልን ይዛ ወደ ግብጽ የመሰደዷን ነገር ተገልጦለት፤
“እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፥ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።” ኢሳ. ፲፱፡፩ በማለት ከገነት የተሰደድነውን እኛን ወደ ቀደመ ርስታችን እንደመጣን ለማጠየቅና፣ ጠላታችን ዲያብሎስን ከሰዎች ልብ አውጥቶ
ለመስደድ፤ ክብር ይግባውና ወልደ እግዚአብሔር ልመናዋ ፈጥኖ በሚሰማላት “ደመና መፍጠኒት” በተባለች በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም
ጀርባ ታዝሎ ወደ ግብጽ የመሰደዱን ነገር አስቀድሞ ገልጾታል።
✙ይኸውም በቅዱስ
ወንጌል እንደተጻፈ ንጉሡ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ለዮሴፍ በሕልሙ ተገልጾለት “ተንሥእ
ወንሣእ ሕፃነ ወእሞ ወጉየይ ውስተ ብሔረ ግብጽ” (ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ”) ባለው ጊዜ ይኽ ኢሳያስ የተናገረው
ትንቢት ሊፈጸም ምልጃወዋ ፈጥነኖ በሚደርስላት “ደመና መፍጠኒት” በተባለች በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ጀርባ ታዝሎ
ወደ ግብጽ በሄደ ጊዜ የግብጽ ጣዖታት ሁሉ እይተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱ አድሮ ያስቱ የነበሩት አጋንንት ሁሉ ሸሽተዋል። በመሆኑም
እመቤታችን “ደመና መፍጠኒት” ወይም ደመና ኢሳያስ ተብላ ተጠርታለች።