Tuesday, October 23, 2012

†♥†አቡነ ዘርዓ ብሩክ†♥†



አቡነ ዘርዓ ብሩክ
አቡነ ዘርዓ ብሩክ የጻድቁ አባታችን የዘርዓ ብሩክ አባት እና እናት የተባረኩ ከቅዱሳን ወገን የሚሆኑ ነበሩ የአባታቸው ስምም ቅዱስ ደመ ክርስቶስ ሲባል እናታቸው ደግሞ ቅድስት ማርያም ሞገሳ ትባላለች ጻድቁ አባታችን ገና በናታቸው ማህጸን እያሉ ነበር ብዙ ተአምራት የሚያደርጉት እግዚአብሄር መርጡአቸዋልና በሁአላም ከክርስቶስ ልደት በሁአላ በስምንተኛው መቶ /ዘመን መጨረሻ ላይ በነሃሴ 27 ጻድቁ አባታችን ተወለዱ 40 ቀናቸውም ተጠምቀው በካህናት አፍ "ጸጋ ክርስቶስ" ተባሉ ከዛም ቤተሰቦቻቸው በጥሩ እድገት አሳደጉአቸው 7 አመትም በሞላቸው ግዜ በልጅነቴ የዚን አለም ክፋቱን እንዳላይ ብለው ቢጸልዩ አይናቸው ታውሩአል:ቤተሰቦቻቸውም የዚን አለም ትምህርት ሊያስተምሩአቸው አስተማሪ ጋር ቢወስዱአቸው ታመው ተመልሰዋል።

Monday, October 22, 2012

†♥†አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ†♥†


በአብ ስም አምኜ አብን ወላዲ ብዬ፣ በወልድ ስም አምኜ ወልድን ተወላዲ ብዬ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምኜ መንፈስ ቅዱስን ሰራጺ ብዬ በማመን ምንም እንኳን በስም በአካል በግብር ሦስት ቢሆኑም በመለኮት ዓለምን በመፍጠርና በማሳለፍ በህልውና በመፍረድ አንድ አምላክ ብዬ በማመንና በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በመታመን ስለ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ከብዙ በጥቂቱ ለመጻፍ እንዲህ እንጀምራለን።
“…. ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ ኪያየ ይጸንሑ  ጻድቃን እስከ ሶበ ተዐስየኒ።” (“ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ።”) መዝ.፻፵፩፡፯ (141፡7)
አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
ትውልዳቸው ከዘርዐ ጌዴዎን ገበዘ አክሱም ነው። አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው አመተማርያም ይባላሉ። ለመምህር ሰጥቷቸው ሲማሩ አድገው ኋላ ወላጆቻቸው በሞት ሲለዩአቸው ደብረበን ኮል ስገብተው ስርዓተ ምንኩስናን ከአበው እያጠኑ ለትልቁም ለትንሸሹም በትህትና እየታዘዙ ውሃ እየቀዱ እንጨት እየሰበሩ በትኀርምትና በጸለሎት ይኖሩ ነበር። ሰይጣን በውዳሴ ከንቱ ጾር ቢመጣባቸው ከማኀበረ መነኮሳቱ ተለይተው በተባሕትዎ ለመኖር ሽተው ወጥተው ሲሄዱ ተከዜ ደረሱ። ወንዙ ሞልቶ የማያሻግራቸው ቢሆን ውሃውን በትምህርተ መስቀል ባርከው በአንድ እጃቸው መጽሐፍ በአንድ እጃቸው መብራት እንደያዙ ገብተው መብራቱ ሳይጠፋ መጽሐፉም ሳይበላሽ ተሻግረዋል። ዋልዲባ ሲደርሱ ጌታ እዚህ ተቀመጥ  ስላላቸው ገዳም ገድመው ሥርዓተ ምንኩስናን እያስተማሩ ተቀመጡ።

ቅዱስ ላልይበላ



በአብ ስም አምኜ አብን ወላዲ ብዬ፣ በወልድ ስም አምኜ ወልድን ተወላዲ ብዬ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምኜ መንፈስ ቅዱስን ሰራጺ ብዬ በማመን ምንም እንኳን በስም በአካል በግብር ሦስት ቢሆኑም በመለኮት ዓለምን በመፍጠርና በማሳለፍ በህልውና በመፍረድ አንድ አምላክ ብዬ በማመንና በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በመታመን ስለ ስለ ቅዱስ ላልይበላ ከብዙ በጥቂቱ ለመጻፍ እንዲህ እንጀምራለን።

“…. ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ ኪያየ ይጸንሑ  ጻድቃን እስከ ሶበ ተዐስየኒ።” (“ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ።”) መዝ.፻፵፩፡፯ (141፡7)

ቅዱስ ላልይበላ /ከ1180­-1207 ዓ.ም/
ቅዱስ ላሊበላ አባቱ ጃን ስዩም እናቱ ኪርወርና ይባላሉ። መጋተ ፳፱ ቀን ተፀንሶ ታህሳስ ፳፱ ቀን ተወለደ። በተወለደም ጊዜ በንብ ስለ ተከበበ እናቱ ማር የበላል ለማለት "ላል ይበላል" ብላለች። በአገውኛ ላል ማር ማለት ነው። ከዚህ የተነሳ ስሙ ላሊበላ ተባለ። ቅዱስ ላሊበላ የብሉያትንና የሐዲሳትን ትምህርት ትርጓሜ የተማረና ጠንቅቆ የሚያውቅ ነው። ትርጓሜ መጽሐፍትንና ሥርዓተ ቤተክርስቲያነን ተምሮ ወደ ትውልድ ሀገሩ ወደ ሮሃ ሲመለስ ንጉሱ የአባቱ ልጅ ታላቅ ወንድሙ ሐርቤ (ገ/ማርያም) ተቀብሎ ሥርዓተ መንግስትን እያስተማረ ከእርሱ ጋር አስቀመጠው።

አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?

" በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች  ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ  የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው ኢየሱስም። አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት እናቱም ለአገልጋዮቹ። የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው። አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። ኢየሱስም። ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው። አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም። አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ። ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው። ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ። " ዮሐ.2:1-11
አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ? ማለት ምን ማለት ነው ? በውኑ ይህ ስድብ ነውን ? ብዙዎች የዚህን ቃል ትርጉም ባለመረዳት ሲስቱ ይስተዋላል:: የቃሉን ትርጉም እና ምንነት ከማየታችን በፊት ስለእመቤታችን ድንግል ማርያም ከፍጥረት ሁሉ ልዩ ክብር እንዳላት ጥቂት እንበል:: እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማይጠረጠር መልኩ ከፍጥረት ሁሉ ልዩ ናት፡፡ በድንግልና ላይ እናትነት፣ በክብረ ድንግልና ላይ ክብረ ወሊድ፣ በድንጋሌ ሥጋ ላይ ድንጋሌ ነፍስና ድንጋሌ ኅሊና የተሰጠው ከእርሷ በቀር ማንም የለም፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፤ ከፍጥረት ወገን እንደ እመቤታችን እርሱን ለማወቅ የተቻለው ፍጥረት የለም፡፡ በሉቃስ ወንጌል ትርጓሜው ላይ እንደገለጸው ስለ አምላክ ፍጥረት ሊያውቀው የሚቻለው የመጨረሻው የእውቀት ደረጃ ላይ የደረሰችው እመቤታችን ብቻ ናት፡፡ እንደ እርሱ ትርጓሜ እመቤታችን ፍጡር ለፈጣሪው ክብር ሊጨምርለት እንደማይቻለው እያወቀች  ‹‹ተዐብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር››‹‹ነፍሴ እግዚአብሔርን ታከብረዋለች›› ያለችው ፍጡር ሊረዳው የሚቻለው የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሳ በዚያ መጠን ማመሰገኗን ስትገልጽልን ነዉ ይላል፡፡

Friday, October 19, 2012

ሳይቃጠል በቅጠል

(የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ) አንጋፋዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በብዙ ሚልዮን የሚቆጠር ተከታይ ምእመናን እንዳሏት ይታመናል፡፡ ይህች አንጋፋና ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ጥንተ ሥልጣኔ መሠረት ስትኾን ለኢትዮጵያ የቱሪስት መዲናነት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ እና መሠረት እንደኾነችም ማንም የሚስማማበት እውነት ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን የኢትዮጵያ ሕዝብ እምነቱን እንዲያከብር፣ ባህሉንና ቅርሱን እንዲከባከብ በሥነ ምግባር በግብረ ገብነት የታነጸ እንዲኾን ያበረከተችው አስተዋፅኦም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይማኖቱን ጠባቂነትና ባህሉን አክባሪነት በምስክርነት እንድትጠቀስ አድርጓታል፡፡ በዚህ መስክም ቤተ ክርስቲያኒቱ ከክርስትና እምነት ተከታዮች ውጭ የኾኑ ወገኖችንም በፍቅርና በክብካቤ በመያዝ ፍቅርን፣ አንድነትንና መቻቻልን በተግባር የሰበከች ስትኾን በውጤቱም ለኢትዮጵያ የእምነቶች መቻቻል ቁልፍ ሚና የተጫወተች አንጋፋና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን ነች፡፡

ብሔራዊት የኾነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ወንጌልን ለመላው ሕዝብ ከማዳረስ አንጻር በከተማ ያልተወሰነች፣ በየገጠሩ የሚገኙ ሕዝቦችን በስብከተ ወንጌል በመማረክ ተከታዮቿ ያደረገች በውጤቱም በመላ ሀገሪቱ ለመስፋፋት የቻለች ስትኾን በክርስትና እምነት ውስጥ ያሉ ወገኖችም በሰላም፣ በመፈቃቀርና በመቻቻል ከሌሎችም ወገኖች ጋራ መኖር እንዲችሉ ያስተማረች እናት ቤተ ክርስቲያን ነች፡፡

Thursday, October 18, 2012

†♥†አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ†♥†



“በስመ ሥላሴ”
እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን፡፡(እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር  ስደተኞችን ይጠብቃል፡፡)“ መዝ.፻፵፭፡፰ (145፡8)
አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ

ኢትዮጵያዊው አባት አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባቱ መልዓከ ምክሩ እናቱ ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለደበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ይባላል፡፡ በዚያች ሀገር እግዚአብሔርን የሚፈራ ስሙ መልዓከ ምክሩ የሚባል ደግ ሰው ባለቤቱም ወለተ ማርያም ሁለቱም ደጋጎች እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው በእግዚአብሔር ህግ ጸንተው የሚኖሩ መልካም ስራን በመስራት እንደ ዘካርያስና ኤልሳጴጥ እውነተኞች ነበሩ፡፡ሁለት ደጋጎች ልጆችም አሏቸው የተባረከ መልካም ፍሬን የሚያፈራ በመጾም በመጸለይ እግዚአብሔርን የሚያገለግል በጸሎቱ ሰውን የሚጠቅም በጻድቃንም ዘንድ የተመረጠ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ዘወትር ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ድንግል ማርያም ይለምኑ ነበር፡፡