ከባለፉት
ሁለት ክፍሎች የቀጠለ
(ደቂቀ
ናቡቴ መስከረም 14/2005)ቅዱስ ያሬድ ቀደምት የዜማ ምልክት ደራሲ መሆኑንም ጭምር ቤተ ክርስቲያን ለአለም የምታሳውቅበት ጊዜ ቢኖር ይህ 1500ኛ መታሰቢያ አመት ይመስለኛል ለዚህ የተቀደሰ ተግባር
ደግሞ እያንዳንዳችን ከዛሬ ጀምረን በየአጥቢያችን ታላላቅ በአላትን ተንተርሰን የሚዘከርበትን ሁኔታዎችን መፍጠር ይገባል ከመስቀል
በዓል አከባበር ቢጀምር ባዮች ነን፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ የዘመናት ዑደት ስፍር ቀምር የራሷን ዜማ ያደላደለች
አፍሪካዊት እመቤት ናት ብንል ጽልመት ሊጋርደው የማይችለው ገሀድ ነው፡፡
የቅዱስ ያሬድ የዜማ ድርሰቶች
የቅዱስ ያሬድ የዜማ ድርስቶች በአምስት ይከፈላሉ እነዚህም ድርሰቶች አምስት ፅዋትወ ዜማ በመባል ይጠራሉ ፡፡ እነርሱም ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ ዝማሬ፣ መጽስዕትና ምዕራፍ ይባላሉ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍት ላይ የቅዱስ ያሬድ ድርስቶችን በዜማ ይተበhል ደረጃ ልዩነት እና አንድነት ያላቸውን በመከፋፈል አራት ይላሉ አነርሱም ድጓ ፣ ቅዳሴ ፣ ዝማሬ እና መዋስዕት ይላሉ ይህን የሚሉት ድጓ ፣ጾመ ድጓ እና ምዕራፍ አንድ አይነት የዜማ ይትበሀል ስላላቸው እንደ አንድ ስለሚቆጥሯቸው በድጓ ውስጥ ስለሚያጠቃልሏቸው በመሆኑ አምስት ከሚሉት ጋር የሚጋጭ አይሆንም፡፡
·
ድጓ፡- ከጽሕፈቱና ከምልክቱ ብዛትና ክሳት የተነሳ ረቂቅ እስተግብዕ /ስብስብ/ ይባላል፡፡ ምክንያቱም የዓመቱን በዓላትና የሳምንቱ መዝሙራት ተሰብስበው ስለሚገኙ ነው፡፡ ድጓ ስብስብ ሙሾ፣ ቁዘማ መዝሙር፣ ሐዲስ፣ ፍፁም ማለት ነው ድጓ የቤተ ክርስቲያን ዜማ መድብል ሲሆን በውስጡ አራት ክፍሎች አሉ እነርሱም፡-
1. ድጓ
ዮሐንስ
- ስለ መጥምቁ ዮሐንስ የሚናገር ሲሆን፣ የዮሐንስን መንገድ ጠራጊነት የሐዲስ ኪዳንን መሸጋገርያነት አንስቶ የዘመረበት ነው የሚዘመርበትም ወቅት ከመስከረም 1
እሰከ ኅዳር 30
2. ድጓ
አስተምሕሮ
- ጌታችን ያሰተማረውን ትምህርት ያደረገውን ተዐምራት
የሚያነሳ ነው ማቴ.5፡2፣
ማር1፡ 39 የሚዘመርበት ወቅትም ከታህሳስ 1 እስከ መጋቢት 30፡፡
3.ድጓ
ጾም
- የድጓው ሦስተኛ ክፍል በዓቢይ ጾም የሚባል ነዉ፡፡
4. ድጓ
ፋሲካ
- የጌታችንን ለዓለም ቤዛ ወይንም ፋሲካ ሽግግር ራሱን መስጠቱን ያነሳል የዕርገትን የጰራቅሊጦስንና የክረምትን ነገር ያነሳል የሚዘመርበት ወቀትም ከሚያዝያ/ከትንሳኤ/ እሰከ ጳጉሜን መጨረሻ፡፡