(ደቂቀ ናቡቴ መስከረም 24,2005 ዓ.ም ከሐመር መፅሄት የተወሰደ(ዲ.ን
ያረጋል አበጋዝ)) ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን
ኃይለ ቃልን ከትርጓሜ
ትርጓሜን ከምሥጢር እንዲሁም
ደግሞ ምሥጢርን ከዜማ
ጋር አስተባብረውና አስማምተው
የሚደርሱ ሊቃውንት ባለቤት
ናት፡፡
በአምስተኛው መቶ ክፍለ
ዘመን የተነሳው ታላቁ ሊቅ
ቅዱስ ያሬድ አምሥቱን ጸዋትወ ዜማ
ሲደርስ በ14ኛው
መቶ ክፍለ ዘመን የተነሳው አባ ጊዮርጊስ
ደግሞ ሰዓታትን ደርሷል፡፡ በዚሁ
ዘመን አባ ጊዮርጊስ ጋር ጥልቅ
መንፈሳዊ ፍቅር የነበረው
አባ ጽጌ ድንግል ‹ማኅሌተ ጽጌ›
የተባለውን ድርሰት ደርሷል፡፡
ማኅሌተ ጽጌ ግጥማዊ
አካሄድ ያለው ድንቅ
ኢትዮጵያዊ ድርሰት ነው፡፡
ይህ ድርሰት በማንኛውም ጊዜ
የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ
ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ
የሚውለው ከመስከረም 26 እስከ
ኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል
ማርያም የስደት ዘመን
ነው፡፡ በዚህ ወቅት
በየሳምንቱ እሑድ ሌሊት
በሙሉ የእመቤታችንን ከልጇ ጋር
ወደ ግብፅ መሰደድና መንከራተት እያሰቡ
የሚደርስ ምሥጋናና ጸሎት
ነው፡፡
በሀገራችን የመስከረምና የጥቅምት
ወራት የአበባ ወራት (ዘመነ
ጽጌ) ናቸው፡፡ ይህም ወቅት
ተራሮች በአበባ የሚያጌጡበትና
ለዓይን ማራኪ የሚሆኑበት
ጊዜ ነው፡፡ በዚህም ዘመን
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ‹‹ስለ ልብስስ
ስለምን ትጨነቃላችሁ፡፡ የሜዳ
አበቦች እንዴት እንዲያድጉ
ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፡፡ አይደክሙም፣
አይፈትሉም፤ ነገር ግን
እላችኋለሁ፣ ሰሎሞንስ እንኳ
በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ
እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡ እግዚአብሔር፣ ዛሬ
ያለውን ነገም ወደ
እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር
እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፣
እናንተ እምነት የጐደላችሁ፣
እናንተንማ ይልቁን እንዴት፡፡
እንግዲህ ምን እንበላለን፣
ምንስ እንጠጣለን፣ ምንስ እንለብሳለን
ብላችሁ አትጨነቁ›› (ማቴ
5÷28-33) በማለት የተናገረውን ቃል
በማሰብ መጨነቅ የሚገባን
መንግሥተ ሰማያት ለመግባት
እንጂ በዚህ ዓለም ስላለው ነገር እንዳልሆነ
ተራሮችን በአበባ ያለበሰ
አምላክ በአርአያውና በአምሳሉ
የፈጠረንን እኛን ለኑሮ
የሚያስፈልገንን ምግብና ልብስ
እንደማይነሳን እያሰብን የምንዘክርበት
ወቅት ነው፡፡