በአብ ስም አምኜ አብን ወላዲ ብዬ፣ በወልድ ስም አምኜ ወልድን ተወላዲ ብዬ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምኜ መንፈስ ቅዱስን
ሰራጺ ብዬ በማመን ምንም እንኳን በስም በአካል በግብር ሦስት ቢሆኑም በመለኮት ዓለምን በመፍጠርና በማሳለፍ በህልውና በመፍረድ
አንድ አምላክ ብዬ በማመንና በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በመታመን ስለ ስለ ቅዱስ ላልይበላ ከብዙ በጥቂቱ ለመጻፍ እንዲህ
እንጀምራለን።
“…. ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ ኪያየ
ይጸንሑ ጻድቃን እስከ ሶበ ተዐስየኒ።” (“ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ።”) መዝ.፻፵፩፡፯ (141፡7)
ቅዱስ ላልይበላ /ከ1180-1207 ዓ.ም/
ቅዱስ ላሊበላ አባቱ ጃን ስዩም እናቱ ኪርወርና ይባላሉ። መጋተ ፳፱ ቀን ተፀንሶ ታህሳስ ፳፱ ቀን ተወለደ። በተወለደም ጊዜ በንብ ስለ ተከበበ እናቱ ማር የበላል ለማለት
"ላል ይበላል"
ብላለች። በአገውኛ ላል ማር ማለት ነው። ከዚህ የተነሳ ስሙ ላሊበላ ተባለ። ቅዱስ ላሊበላ የብሉያትንና የሐዲሳትን ትምህርት ትርጓሜ የተማረና ጠንቅቆ የሚያውቅ ነው። ትርጓሜ መጽሐፍትንና ሥርዓተ ቤተክርስቲያነን ተምሮ
ወደ ትውልድ ሀገሩ ወደ ሮሃ ሲመለስ ንጉሱ የአባቱ ልጅ ታላቅ ወንድሙ ሐርቤ (ገ/ማርያም) ተቀብሎ ሥርዓተ መንግስትን እያስተማረ
ከእርሱ ጋር አስቀመጠው።