†♥†አባ
ገሪማ ዘመደራ†♥†
(“ኦ ወልድዬ
ግሩም ገሪማ ገረምከኒ”)
የተሰዓቱ ቅዱሳን ሐዋርያዊ ተልእኮ መቅድም
ተሰዓቱ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አልአሜዳ
በነገሰ በአምስት ዓመት ነው። እንደመጡት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው በአክሱም ዐስራ ሁለት ዓመት ኖረዋል።
ተሰዓቱ ቅዱሳን በስም አባ አሌፍ፣ አባ አረጋዊ፣
አባ ጰንጠሌዎን፣ አባ ገሪማ፣ አባ ጵሕማ፣ አባ አፍጴ፣ አባ
ሊቃኖስ፣ አባ ይምዓታ፣ አባ ጉባ ይባላሉ። እኚ አባቶች ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ዝም ብሎ አልተቀመጡም፤ ለሥራቸው
በር ከፋች የሆነውን ቋንቋ፣ የሕዝቡን ባህል ጠንቅቀው ካወቁ በኋላ ላይ በአንድ አከባቢ ከመኖር ይልቅ መንፈስ ቅዱስ በመደባቸው
ቀጥታ ማስተማርን መርጠው መንፈሳዊ ዓላማቸውን ለማሳካት የአክሱምን ነገስታት እርዳታና ድጋፍ አልተለያቸውም ነበር። እኚው ተሰዓቱ
ቅዱሳን የመጡበት ሀገራት ሮም፣ እስያ፣ አንጾኪያ፣ ቁስጥንጥንያ፣ ቂሳርያ፣ ኪልቂያ ሲሆን በነበሩበት ጊዜያትም፡-
፩. ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን አጽንቶልናል።
፪. መጽሐፍትን ተርጉሞልናል።
፫. ስብከተ ወንጌልን አስፋፍተዋል።
፬. ብዙ ገዳማትን መስርተዋል።
፭. ሥርዓተ ምንኩስናን አደራጅተዋል።