Tuesday, February 14, 2012

ትውፊት


ትውፊት   የሚለው ቃል አወፈየ /ሰጠ/ ከሚለው የግእዝ ቃል /ግስ/ የተገኘ ቃል ሲሆን የተሰጠ /የተቀበሉት/ የሚል ትርጉም አለው፡፡ ስለዚህ ሐዋርያዊ ትውፊት ማለት ከሐዋርያት ጀምሮ በቃል፣ በጽሑፍና በተግባር ሲፈጸም በመመልከት ሲወርድ ሲዋረድ ከእኛ ዘንድ የደረሰ የቤተ ክርሰቲያን ትምህርት እና ሥርዓት ማለት ነው፡፡  ሐዋርያትና ሌሎቹ የጌታችን ደቀመዛሙርት ወንጌልን መጀመሪያ ያስተምሩ የነበሩት በቃል ነበር፡፡ በኋላ ግን ትምህርቱ እንዳይጠፋ በማለት በጽሑፍ ጽፈውታል፡፡ ከጻፏቸውም ነገሮች አብዛኞቹ ባለን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ያልተጻፉ ብዙ ነገር እንዳሉና፣ ከጽሑፋቸውም ውጪ በቃልና በተግባር ያስተማሩት ብዙ ነገር እንዳለ ራሳቸው ጽፈዋል፡፡  «ጌታችን ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸው ነበር» /ዮሐ. 21.25/  «በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ» /2 ተሰ 2.15/ 

Sunday, February 12, 2012

ድርሳንና ገድል ጥያቄ

ጥያቄ ”በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ጊዜ ድርሳንና ገድል ሲባል እሰማለሁ፡፡ እኔም የድርሳንና የገድል ልዩነት ብዙ ጊዜ አይገባኝም፤ እባካችሁ የድርሳንና የገድልን አንድነትና ልዩነት አስረዱኝ”

ዲ/ን ኅሩይ ባየ

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ጊዜ ድርሳንና ገድል ሲባል እሰማለሁ፡፡ እኔም የድርሳንና የገድል ልዩነት ብዙ ጊዜ አይገባኝም፤ እባካችሁ የድርሳንና የገድልን አንድነትና ልዩነት አስረዱኝ”
ገብረ እግዚአብሔር
ከዲላ

ውድ ጠያቂያችን በእርግጥ እርስዎ እንዳሉት ድርሳንና ገድል በቤተ ክርስቲያን የማይነሡበት ጊዜ የለም፡፡ “የኑሮአቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው” ዕብ.13፥7 እንደተባለው በሃይማኖትና በምግባር ለመጠንከር ገድለ ቅዱሳንን የያዙ መጻሕፍትን እናነባለን፤ እንጸልይባቸዋለን፡፡ የቅዱሳን መላእክትንም ጠባቂነት፣ የሊቃውንትን ተግሣጽ ትርጓሜና ምክር የዕለተ ሰንበትን ክብር እና የኢየሱስ ክርስቶስን የቤዛነት ሥራ የሚናገሩ ድርሳናትን ሁል ጊዜ እናነባለን እናደርሳለን፡፡

Friday, February 10, 2012

ያኔ… /በቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ/!!

(በወንድማችን ገብረእግዚአብሔር)
ያኔ… /በቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ/!!
( በተመስጦ ሆነው ያንቡት)!
በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በደመናው ውስጥ የነበሩት ሦስቱ ደቀ መዛሙርት እንዴት የተባረኩ ናቸው?

Thursday, February 9, 2012

በአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ጭፍን ጥላቻ ቤተ ክርስቲያናችን ተቃጠለች


 በአጽራረ ቤተ ክርስቲያን  ጭፍን ጥላቻ ቤተ ክርስቲያናችን ተቃጠለች








በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚደርስው አደጋ ከእለት ወደ እለት አስከፊ እየ ሆነ መጥቶአል በቅርቡ በስልጤ የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን በሙስሊሙ የደረሰባት ቃጠሎ ከውስጣችን የማይጠፋ እና መቼም ቢሆን የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ የማያቕርጥ ቢሆንም ክርስቲያን እና ምስማር ሲምቱት ይጠብቃል ንውና  ይልቁንም ክቀድሞው አሁን ጠንክረን ቤተ ክርስቲያናችንን ልንጠብቅ ይገባል


ጆሮም የማይሰማው አይንም የማያየው መቼ የለመ ዛሬ ደግሞ ፕሮቲስታንቱ ቅሰጣቸውን አጠናክርው ቀጥልዋል::
በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት፣ በዲታ ወረዳ፣ ጋና ደሬ ቀበሌ፣ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 29 ቀን 2004 ዓ.ም. ከሌሊቱ በስድስት ሰዓት አካባቢ በእሳት ቤተ ክርስቲያናችን ተቃጠሎአል 

ካህናት እና ዲያቆናትእንደታሰሩ ነው

(በወንድማችን ነቢዩ ሰሎሞን)
የስልጢ ቅበት ማርያም አገልገይ ካህናት ዲያቆናት እና አስተዳዳሪ አሁንም እንደታሰሩ ነው ሙሉ ሪፖርቱ ደርሶናል
በክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ከሚደረግባቸውና እንደ አንድ ዜጋ እንኳን ከማይቆጠሩበት ቦታዎች መካከል ስልጢ ዋናውና ቀዳሚው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በእርግጥ በስልጢ ወረዳ ውስጥ 22 አብያተክርስቲያናት እና ከፍተና ቁጥር ያለው ምዕመን ቢኖርም እስከአሁን ድረስ ምዕመናን በነጻነት የእግዚአብሔርን ስም እንዳይጠሩ እና በነጻነት እንዳይንቀሳቀሱ ለኑሮዋቸውም ምንም ዓይነት ዋስትና የሌላቸው መሆኑ በጣም የሚያሳዝን እየሆነ መጥቷል፡፡

Wednesday, February 8, 2012

Monday, February 6, 2012

ውዳሴ ማርያም በንባብ

ውዳሴ ማርያም በንባብ 
ከሰኑይ  እስከ  ዘሰንበተ ክርስቲያን እንዲሁም  እንቀጸ ብርሃንን  ጨምሮ


ከቤተ መቅደስም አትለይም ነበር ሉቃ 2:37

ከቤተ መቅደስም አትለይም ነበር ሉቃ 2:37
በዲ/ን ህብረት የሽጥላ