Monday, February 27, 2012

ፆም አያስፈልግም?

ፆም  አያስፈልግም?
 ክርስቶስ ፆሞልኗልና አንፆም ?
ፆም በዛ ?
ፆም ማለት ምን ማለት ነው ?
ፆም የታዘዘበት ምክነያቱ ምንድን ነው ?
 ቀሲስ ከፍያለው  ጥላሁንቀሲስ ከፍያለው  ጥላሁን
ፆም የዳቢሎስ ድል መንሻ ነው ያድምጡት በጥቂቱ



ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል



"ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥
 እንዲህ ሲል። በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች። ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ። ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥ ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ ጌታም አለ። ዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን? ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፥0 እንዲህ ሲል ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ። እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጦማለሁ፥ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት አወጣለሁ አለ ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን። አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።" ሉቃ18:1-14
"ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም"  ማቴ. ፬፡፬

Friday, February 24, 2012

ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ

ከበለስ በታች  ሳለህ  አየሁህ ዮሐ. 1፡-44 በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ዮሐ.1:44-52 "በነገው ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊወጣ ወደደ፥ ፊልጶስንም አገኘና ተከተለኝ አለው  ፊልጶስም ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበረ ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ። ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው ናትናኤልም ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? አለው። ፊልጶስ። መጥተህ እይ አለው ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ። ተንኰል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው እነሆ አለ ናትናኤልም ከወዴት ታውቀኛለህ? አለው ኢየሱስም መልሶ። ፊልጶስ ሳይጠራህ፥ ከበለስ በታች ሳለህ፥ አየሁህ አለው ናትናኤልም መልሶ። መምህር ሆይ፥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ አለው ኢየሱስም መልሶ ከበለስ በታች አየሁህ ስላልሁህ አመንህን? ከዚህ የሚበልጥ ነገር ታያለህ አለው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ አለው።"

Tuesday, February 21, 2012

አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ አብሳዲ አረፉ።


በ1912 የተወለዱ አና በኢትዮጵያ እና በኤርትራ በክህነታቸው ቤተ ክርስቲያንን ያገለገሉት ብፁእነታቸው ዲቁናን  ከብፁዕ አቡነ ይስሃቅ እንዲሁም ቅስናን ከኤርትራው ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል  ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ረዳት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል እንዲሁም ከግብፅ ከፍሊስጤም እና ከሊባኖስ ያለውን የቤተ ክርስቲያን ፈተና በማቀለል ከፍተኛ አገልግሎትን ፈፅመዋል ብፁእነታቸው የዕብራየስጢኛ እና የአረቢኛ ቋንቋም ተምረዋል ፡፡
ላለፉት 60 ዓመታት በኢየሩሳሌም ገዳማት የኖሩትና በእግራቸው ከኢትዮጵያ ወደ ቅድስት አገር ጓዙት  ጥንታዊ ትውፊት ከፈፀሙት አበው መካከል የነበሩት ብፁዕነታቸው በሕመም እና በእርግና ምክንያት  በተወለዱ በ 92 ዓመታቸው የካቲት 10 ለሊት ባደረባቸው ሕመም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል የአባታችንን ነፍስ አምላክ በገነት ያሳርፍልን::

Tuesday, February 14, 2012

«ወዮልኝ፣»


መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው

የእግዚአብሔር ሰዎች «ወዮልኝ፤» እያሉ ራሳቸውን ገሥጸው ይኖራሉ። ጌዴዎን የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ ፊት ለፊት ስላየው ፥ ቃል በቃል ስላነጋገረው፡- «አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ ወዮልኝ፤ የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና፤» ብሎ ነበር። እግዚአብሔርም፡- «ሰላም ለአንተ ይሁን፥ አትፍራ፥ አትሞትም፤» ብሎታል። መሳ ፮፥፳፪። ነቢዩ ኤርምያስም፡- «በሆድ ሳልሠራ አውቄሃለሁ፥ ከማኀፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሐዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ፤» በተባለ ጊዜ፡- «ወዮ ጌታ እግዚአብሔር፥ እነሆ፥ብላቴና ነኝና እናገር ዘንድ አላውቅም፤» ብሏል። ኤር ፩፥፬። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ፦ «ወንጌልን ባልሰብክ ወዮልኝ፤ » ብሏል። ፩ኛ ቆሮ ፱፥፲፮።
          እነዚህ «ወዮልኝ፤» ማለታቸው ለእኛ አብነት ነው። ታላላቆቹ እንዲህ ካሉ ከእኛ ከታናናሾቹ የብዙ ብዙ ይጠበቃል። ዕለት ዕለት «ወዮልኝ፤» እያልን ደረታችንን ልንደቃ፥ እንባችንን ልናፈስስ ይገባል። ሥጋችንን ደስ ከማሰኘት በስተቀር እግዚአብሔርን ደስ አሰኝተን አናውቅምና። ሰውን ደስ ለማሰኘት በሰውም ዘንድ ለመወደድ (ለውዳሴ ከንቱ) እግዚአብሔርን እናሳዝናለንና። እንኳን መንፈሳዊ መሆን መምሰሉ እንኳ አቅቶናልና። ሃያ፥ሠላሳ ዓመት ቃለ እግዚአብሔር ዘር ተዘርቶብን፡- ሠላሳ፥ስድሳ፥መቶ ማፍራት የተሳነን ዘረ ቆርጥሞች ነንና። መቁረባችን ማቁረባችን ፥ መቀደሳችን ፥ ማስቀደሳችን፥ ማሳለማችን፥መሳለማችን፥ መናዘዛችን፥ማናዘዛችን፥ መዘመራችን፥ማዘመራችን፥ መስበካችን፥መሰበካችን ሁሉ ከንቱ ሆኖብናልና። ስለሆነም «እገሌ ሳይገባው ነው፤» የሚለውን ትተን፡- «እኔ ሳይገባኝ ነውና ወዮልኝ፤» እንበል። የእግዚአብሔር ሰዎች፡- «ወዮላችሁ፤» እስኪባሉ አይጠብቁምና።
«ወዮላችሁ፤»
          የዓለም ሰዎች፡- «ወዮላችሁ፤» እስኪባሉ ይጠብቃሉ፤ ተብለውም አይመለሱም፤ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቃሉን ትምህርት ሰምተው፥ የእጁን ተአምራት አይተው ያልተመለሱትን ጸሐፍት ፈሪሳውያንን በአንድ ምዕራፍ ላይ ብቻ ስምንት ጊዜ «ወዮላችሁ፤» ብሏቸዋል።

ትውፊት


ትውፊት   የሚለው ቃል አወፈየ /ሰጠ/ ከሚለው የግእዝ ቃል /ግስ/ የተገኘ ቃል ሲሆን የተሰጠ /የተቀበሉት/ የሚል ትርጉም አለው፡፡ ስለዚህ ሐዋርያዊ ትውፊት ማለት ከሐዋርያት ጀምሮ በቃል፣ በጽሑፍና በተግባር ሲፈጸም በመመልከት ሲወርድ ሲዋረድ ከእኛ ዘንድ የደረሰ የቤተ ክርሰቲያን ትምህርት እና ሥርዓት ማለት ነው፡፡  ሐዋርያትና ሌሎቹ የጌታችን ደቀመዛሙርት ወንጌልን መጀመሪያ ያስተምሩ የነበሩት በቃል ነበር፡፡ በኋላ ግን ትምህርቱ እንዳይጠፋ በማለት በጽሑፍ ጽፈውታል፡፡ ከጻፏቸውም ነገሮች አብዛኞቹ ባለን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ያልተጻፉ ብዙ ነገር እንዳሉና፣ ከጽሑፋቸውም ውጪ በቃልና በተግባር ያስተማሩት ብዙ ነገር እንዳለ ራሳቸው ጽፈዋል፡፡  «ጌታችን ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸው ነበር» /ዮሐ. 21.25/  «በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ» /2 ተሰ 2.15/ 

Sunday, February 12, 2012

ድርሳንና ገድል ጥያቄ

ጥያቄ ”በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ጊዜ ድርሳንና ገድል ሲባል እሰማለሁ፡፡ እኔም የድርሳንና የገድል ልዩነት ብዙ ጊዜ አይገባኝም፤ እባካችሁ የድርሳንና የገድልን አንድነትና ልዩነት አስረዱኝ”

ዲ/ን ኅሩይ ባየ

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ጊዜ ድርሳንና ገድል ሲባል እሰማለሁ፡፡ እኔም የድርሳንና የገድል ልዩነት ብዙ ጊዜ አይገባኝም፤ እባካችሁ የድርሳንና የገድልን አንድነትና ልዩነት አስረዱኝ”
ገብረ እግዚአብሔር
ከዲላ

ውድ ጠያቂያችን በእርግጥ እርስዎ እንዳሉት ድርሳንና ገድል በቤተ ክርስቲያን የማይነሡበት ጊዜ የለም፡፡ “የኑሮአቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው” ዕብ.13፥7 እንደተባለው በሃይማኖትና በምግባር ለመጠንከር ገድለ ቅዱሳንን የያዙ መጻሕፍትን እናነባለን፤ እንጸልይባቸዋለን፡፡ የቅዱሳን መላእክትንም ጠባቂነት፣ የሊቃውንትን ተግሣጽ ትርጓሜና ምክር የዕለተ ሰንበትን ክብር እና የኢየሱስ ክርስቶስን የቤዛነት ሥራ የሚናገሩ ድርሳናትን ሁል ጊዜ እናነባለን እናደርሳለን፡፡