†♥†በስመ ሥላሴ†♥†
እንኳን ለእመቤታችን በዓታ ለማርያም፣
ነአኩቶ ለአብ፣ፋኑኤል መልአክ፣አቡነ ዜና ማርቆስ፣ እንዲሁም አባ ሊባኖስ ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ
አቡነ ዜና ማርቆስ በ፲፫ኛ/13ኛው/ መቶ ክ/ዘማን)
ስለ እመቤታችን፣ ስለሐዋርያት፣ ስለነገስታት፣
ስለጻድቃን፣ ስለሰማዕታት፣ ስለ ቅዱሳን መላእክት በአጠቃላይ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እንወቅ፣ እንመርምር፣ እንጠይቅ፣እንማማር ለዚህም
እግዚአብሔር አምላክ እዝነ ልቦናችንን ይክፈትልን፤ የአዲስ ኪዳን ኪሩብ የጸጋ መፍሰሻ ምልዕተ ክብር ምልዕተ ውዳሴ የሆነች እመቤታችን
ድንግል ማርያም ምስጢር ትግለጥልን አሜን!!!
†♥† ቅዱሳን
ጻድቃን መላ ዘመናቸውን ከጣዕመ ዓለምና ከተድላ ዓለም ተለይቶ
ቤት ልስራ ዘር ልዝራ ሳይሉ ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው አስገዝተው በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በምናኔ ጸንተው የኖሩ
ናቸው።
ቅዱስ
አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ ሀገራቸው
ዞረሬ /ጽላልሽ/ ነው። አባታቸው ካህን ዮሃንስ የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት የአቡነ ጸጋዘአብ ወንድም ነው። እናታቸው
ዲቦራ (ማርያም ዘመዳ ትባላለች። የአቡነ ቀዎስጦስ እህት ናት። በብስቃረ ማርቆስ ወንጌላዊ ህዳር ፳፬ /24/ ተወልዷል። አርባ ቀን ሲሞላው ሊያስጠምቋቸው ቤተ ክርስቲያን
ወሰዷቸው። ጸሎተ ጥምቀቱ ደርሶ ከውሃ ውስጥ ሲከቷቸው ቆመው እሰግ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብለው 3 ጊዜ ሰግዶአል።
ውሃው ፈላ አጥማቂው ቄስ የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት
የአቡነ ጸጋዘአብ ወንድም ካህኑ እንድርያስ ነበር። እድሜው 72 ዓመት ስለነበር በሕፃኑ ድርጊት ፈርቶ ወደ ቤተ መቅደስ ሮጠ። ቅዱስ
ሩፋኤ ከፍርሃቱ አጽናንቶት ከማየ ጸሎቱ ራሱን እንዲቀባ ነግሮት በራ የነበረ ራሱ ጸጉር በቅሎለታል።አቡነ ዜና ማርቆስ 5 ዓመት
ሲሞላቸው ወላጆቻቸው ለመምህር ሰጧቸው። በ 3 ዓመት ብሉይንና ሐዲስ አጥንተው በ8 ዓመታቸው ከቅዱስ ቄርሎስ ድቁና ተቀብለው ሲመጡ
ሽፍቶች የእጃቸውን በትር ነእሳቸውም ወደ ጌታ ቢያመለክቱ በትራቸው እባብ ሆና ነድፋ ገድላቸዋለች። 30 ዓመት ሲሆናቸው ማርያም ክብራ ለምትባል ደግ ሴት አጋቧቸው። ልማደ
መርዓዊ ወመርዓት (ሙሽራውና ሙሽራይቱ) ያድርሱ ብለው መጋረጃ
ሲጥሉባቸው በሌሊት ወጥተው ሄዱ። መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ሀገረ ምሑር
አድርሷቸውዋል። በዛም የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በመጥራታቸውና ከንጉሱ
(ሀገረ ገዢው) አብላኝ በማለታቸው የኔ አምላክ ማኮስ ነው ኢየሱስ የምትለው ማን ነው ቢላቸው አምላካችን ነው ቢሏቸው ወስዶ
ቤተ ጣዖት ቢያሳያቸው ወስደው በእግር ረግጠው አሰጠሙት። መስፍኑ
ተቆጥቶ አሰራቸው። መልአኩም ከእስራታቸው ፈቷቸዋል። እንዲያበላቸው ዳግም ሀገረ ገዢውን ቢጠይቁት ተናዶ በጦር ሊወጋቸው ሲል
ምድር አፏን ከፍታ ባሕር ሆና አሰጠመችው። እንዲህ እያሉ ብዙ ስለ ጌታ መስክረዋል።