- መፈክራችን - “የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል” የሚል ነው።
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 11/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 20/2012)፦ በጥቂት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፍላጎት በመዘወር ላይ ያለው የ6ኛው
ፓትርያርክ ምርጫ
ተጠናክሮ በመቀጠል አሁን “አስመራጭ ኮሚቴ”
በማቋቋም ትልቅ
ርምጃ ተስፈንጥሯል። ለዕርቅና ለሰላም ወደ
አሜሪካ የላካቸውን ልዑካን መምጣት ሳይጠብቅ፣ ይዘው ለሚመጡት ምላሽ
ቦታ ሳይሰጥ አዲስ ፓትርያርክ ወደ
መምረጡ እየተጓዘ ነው።
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ በአገር ውስጥም፣ ከአገር ውጪም፣ በመላው ዓለም ያለው ኦርቶዶክሳዊ ድምጹን ማሰማት እንደሚፈልግ ይታወቃል። የአቅሙን የመፍትሔው አካል መሆን ይፈልጋል። ታዲያ
ምን ይሻላል? ከጥቃቅን የጽዋ ማኅበራት እስከ ግዙፎቹ፣ ከማኅበረ ካህናት እስከ ማኅበረ ምዕመናን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን
እንደሚገደን መናገር የሚገባን አሁን ነው። ስለዚህም ነው
ይህንን የመወያያ ርዕስ የከፈትነው። መፍትሔ የምትሏቸውን ሐሳቦች በማቅረብ፣ በየአካባቢያችሁና
በየአጥቢያችሁ በአካል በመሰባሰብና በመነጋገር ለእናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያላችሁ አለኝታነት እንድታሳዩ ይጠበቃል። እምነት በሥራ እንጂ በምን ይገለጻል? ለመነሻ እንዲሆን ይህንን እንጠቁም። እናንተም አክሉበት።
- መረጃውን ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን ማድረስ፣ (በስልክ የኤስ.ኤም.ኤስ መልእክቶች፣ በፌስቡክ፣ በትዊተር)፣
- በየአጥቢያችን ድምጻችንን ልናሰማ የምንችልበት ስብስብ መፍጠር፣
- ዜናውን ለመገናኛ ብዙኃን ማድረስ፣
- ብፁዓን አባቶችን በስልክም በአካልም በመቅረብ ስለ ጉዳዩ ማነጋገር፣ በውሳኔው እንደማንስማማ ማሳወቅ፣ (አስፈላጊ ነው ብለን በምናምነው ጊዜ ስልኮቻቸውን በይፋ ለማቅረብ እንገደዳለን)
- ጉዳያችን እና ዓላማችን “ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ” ሳይሆን የቤተ ክርስቲያናችን አባት የመምረጥ ጉዳይ መሆኑን ለሚመለከታቸው አካላት አለ ፍርሃትና ያለ ሥጋት መግለጽ፣
- ከመንግሥት አካላት የተደበቀ የመሥራት ፍላጎት እንደሌለን ከወዲሁ በተደጋጋሚ መግለጽ፣
- በአገር ውስጥ ያሉ ጋዜጦችና መጽሔቶች ለጉዳዩ ሽፋን እንዲሰጡት ማበረታታት፣
- የውጪ አገር ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎችም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ በሚል በዚሁ ሰበብ ኢሕአዴግን ለመተቸት ሳይሆን ጉዳዩን ለክርስቲያኑ ሕዝብ በማይጎረብት መልክ እንዲያቀርቡት ማገዝ፣
- ኦርቶዶክሳውያን ጡመራ መድረኮችም ዜናዎችን በትብብርና በኅብረት ለምእመኑ ማድረስ፣
ጨምሩበት!!!!