Thursday, May 17, 2012

ማ/ቅዱሳን መንግሥት በዋልድባ አካባቢ ስለሚገነባው የስኳር ፕሮጄክት “መልካምነት” ባለመዘገቡ ተጠየቀ፤ መልስ እንዲሰጥ ይጠበቃል


አስከትሎም “ስለሆነም ማንኛውም ጋዜጠኛ በተለይም ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልሣን የሆነው የማኅበሩ ጋዜጣና መጽሔት መረጃ ከወሰደ በኋላ መግለጫውን አለማውጣቱ አግባብነት የሌለው ከመሆኑም በላይ የሚዲያ ሥነ ምግባርንም ያልተከተለ ስለሆነ” ጽሑፉ ያልወጣበትን ምክንያት ማኅበሩ በጽሑፍ ይገልጽ ዘንድ ከሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መታዘዙን ያብራራል።

የመምሪያው ደብዳቤ አክሎም “ጋዜጣዊ መግለጫውን በሚዲያ ለማውጣት ተስማምታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ከወሰናችሁ በኋላ ዘገባው የቀረበት ምክንያት በጽሑፍ ለማደራጃ መምሪያው” እንዲመለስ እንደሚጠብቅ ይገልጻል። ደብዳቤው በአድራሻ ለማኅበሩ ከተላከ በኋላ ደግሞ ለቤተ ክህነቱ የተለያዩ አካላትና በመንግሥትም በኩል “ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ለብሔራዊ ደኅንነት አገልግሎትና ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን” ግልባጭ ተደርጓል።

የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት. የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት፣ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ እና ሕግ አገልግሎት መምሪያ የቤተ ክርስቲያናችን አካላት ስለሆነ በቀጥታም ባይሆን ጉዳዩ ሊያገባቸው ይችላል። ከላይ ስማቸው የተዘረዘሩት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በምን አግባብ ነው ስለ አንድ ማኅበር፣ ያውም በአንድ መምሪያ ሥር ስላለ አካል ግልባጭ የሚደረግላቸው? መንግስታዊ መሥሪያ ቤቶቹ ከሚዲያ ጋር የተገናኙ እንኳን ቢሆኑ በግድምድሞሽ “ግንኙነት አላቸው” ይባል ይሆናል። ፌዴራል ጉዳዮች፣ ደኅንነት፣ ፖሊስ … መጠቀሳቸው ለምን ያስፈልጋል? እሰሩልን፣ ግደሉልን፣ ቀፍዱድልን ለማለት ካልሆነ።

Monday, May 14, 2012

አቡነ ጳውሎስ ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ጋራ ማበራቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ገለጹ

 (ምንጭ ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 5/2004 ዓ.ም፤ May 13/ 2012)፦



  • ቅዱስ ሲኖዶስ በቀጣይ ለሚኖረው አመራር የመላው ካህናትና ምእመናን ጸሎትና ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲደረግለት ተጠይቋል 
  • በአባ ጳውሎስ፣ አባ ፋኑኤልና ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ምክርና ኮሚሽን አድራጊነት የተጻፈው የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ርእሰ አንቀጽ እና ዘገባ በፈጠረው ቁጣ ሳቢያ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተቋረጠ 
  • ጋዜጣው በስብሰባ መካከል መሰራጨቱና ባተኮረበት ይዘት ብፁዓን አባቶችን ለማሸማቀቅ ተብሎ መዘጋጀቱን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተናግረዋል 
  • የጋዜጣው ርእሰ አንቀጽና ዘገባዎች አባ ጳውሎስ በስብሰባው እንዲያዙላቸው የሚፈልጓቸውን አጀንዳዎች ከአባ ጳውሎስ “የፓትርያርክነት ዐምባገነንነት” ፍላጎት አንጻር የማብራራት ግብዝነት የሚታይበት ነው
  • አባ ጳውሎስን ከፓትርያርክነት ማዕርጋቸው በሚያወርዷቸው የቃለ መሐላ ጥሰትና የታማኝነት መታጣት ጉዳዮች ዙሪያ ጠንካራ ውይይት ተጀምሯል
  • የአባ ጳውሎስ ግብረ በላዎች ትንት ማምሻውንና ዛሬ ቀን በአባቶች ማረፊያ ቤት እየተዘዋወሩ በማስፈራራት ጽናታቸውንና አንድነታቸውን ለማላላት እየሞከሩ ነው፤ እጅጋየሁ በየነ፣ ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁንና ለጊዜው ስማቸው ያልተጠቀሱ ግለሰቦች ይገኙባቸዋል
  • መደበኛ ስብሰባው ነገ ሰኞ ይቀጥላል
  ግንቦት 4 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀትር በፊት በነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ርእሰ መንበሩ አባ ጳውሎስ በምልአተ ጉባኤው ስምምነት የተደረሰባቸውን አጀንዳዎች ባለመቀበል ኾነ ብለው በያዙት ግትርነት የተነሣ ብዙኀኑ አባላት ከቀትር በኋላ ሌላ ሰብሳቢ መርጠው ውይይታቸውን ለመቀጠል ወስነው ነበር የተነሡት፡፡
በዚህ መሠረት የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ከቀትር በኋላ ስብሰባውን ለመቀጠል ወደ አዳራሹ ሲገቡ የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በየመቀመጫቸው አንጻር ተቀምጦ ያገኛሉ፤ ፓትርያርኩም በኮሚቴው የተዘጋጁትን አጀንዳዎች እንደሚቀበሉ መስለው ተላስልሰው በመቅረባቸው ምልአተ ጉባኤው በእርሳቸው ርእሰ መንበርነት እየተመራ በተ.ቁ (2) ላይ የተመለከተውን የቅዱስ ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤልን ሪፖርት አዳመጠ፤ እግረ መንገዳቸውንም ጋዜጣውን እንደ ዋዛ መመልከታቸውን አላቆሙም ነበር፡፡
ሪፖርቱ በንባብ ተሰምቶ ከተጠናቀቀ በኋላ ውይይት ከመጀመሩ በፊት ለሻሂ ዕረፍት የተነሡት አባቶች ግን ጋዜጣው በያዘው ‹ቁም ነገር› ላይ መመካከር ያዙ፤ ምክክሩም አቡነ ጳውሎስ ከስብሰባው ቀደም ብለው ከዋሽንግተን ወደ አገር ቤት ከመጡት አባ ፋኑኤል እና ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ጋራ በማበር የጋዜጣውን አዘጋጆች እና ጋዜጣው በሚዘጋጅበት መምሪያ ውስጥ በሓላፊነት የሚገኙ ሌሎች ግለሰቦችን በቅጥረኝነት በመጠቀም የሠሩት መኾኑን ይደርሱበታል፡፡
ከሻሂ ዕረፍት መልስ ጋዜጣው ምን እንደጻፈ፣ ስለምን እንደጻፈ ሊያውቅና ሲቆጣጠርም ይገባ የነበረው  የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ስለ ጋዜጣው ዝግጅት ምንም እንደማያውቁና ሌሎች አጀንዳዎች ወደ ኋላ ቀርተው ምልአተ ጉባኤው በዚሁ ጉዳይ እንዲነጋገር ይጠይቃሉ፡፡ ከዚህ በኋላ በቤቱ የነበረው ድባብ በፓትርያርኩ እና በአባ ፋኑኤል ላይ ባነጣጠረ የተግሣጽ መአት የተሞላ ነበር፡፡ አባ ጳውሎስም ይኹኑ አባ ፋኑኤል የሠሩትን ያውቃሉና አንገታቸውን አቀርቅረው ተግሣጻቸውን ከመቀበል ውጭ ትንፍሽ ያሉት ነገር አልነበረም፡፡
በተግሣጹ አባ ጳውሎስ ከተሐድሶ መናፍቃን ጋራ በግልጽ በማበር አባቶች በወቅታዊ ጉዳዮች በተቀረጹት አጀንዳዎች ዙሪያ ያላቸውን አንድነት እና የዓላማ ጽናት በመሸርሸር ለማሸማቀቅ (በግብር የሚመስሏቸው የመፍቀሬ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎጎች እንደሚያደርጉት) አስበው እንዲፈጸም በማዘዝ እጃቸው እንዳለበት ተነግሯቸዋል፤ አባ ፋኑኤልም “መወገዝ ያለብኽ ሕገ ወጡ አንተ ነኽ፤ በሌላው ሊቀ ጳጳስ ሀገረ ስብከት ገብተኽ ክህነት የምትሰጥ፤ አንተ ብሎ ክህነት ያዥ¡” በሚሉና ሌሎችም ኀይለ ቃላት የድርሻቸውን አግኝተዋል፡፡
በ56ኛ ዓመት ቁጥር 126፣ ሚያዝያ ግንቦት 2004 ዓ.ም ታትሞ በወጣው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ላይ ‹‹የአባቶች ገበና በሕገ ቤተ ክርስቲያን ሲጋለጥ›› በሚል ርእስ ስለ ሰፈረው ርእሰ አንቀጽ፣ ‹‹ቤተ ክርስቲያንንና መንጋዎቿን ከወቅታዊ አደጋ ለመታደግ ከግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚጠበቅ የህልውና ውሳኔ›› በሚል ርእስ ስለተዘጋጀው ሐተታ አስተያየታቸውን የተጠየቁት ዋና አዘጋጁ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ‹‹እኔ ማንንም አልፈራም፤ ጽሑፉ አያስጠይቀኝም እንጂ ብጠየቅበት አልፈራም፤ በይዘቱ አዲስ አይደለም፤ የተለያዩ ግለሰቦች በየራሳቸው አቀራረብ ሲጽፉት የቆዩት ነው፤ እኔ ለመጻፍ የሞከርኹት የቤተ ክርስቲያን ህልውና እየተነካ ነው ብዬ በማምንበት ስለ ጳጳሳት ንብረት ጉዳይ ነበር፤ አባ ጳውሎስ ግን በሲኖዶስ ስብሰባ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይሻሻል አሉ፤ እውነቱን ለመናገር  ጽሑፉ ከውጭ የመጣ እንጂ በዝግጅት ክፍሉ የተጻፈ አይደለም፤ በስሜ እየተነገደብኝ ነው፤›› ብለዋል፡፡
ዋና አዘጋጁ ጽሑፉ ከውጭ ተዘጋጅቶ እንደመጣ የተናገሩትን መነሻ በማድረግ አዘጋጁን አካል ለማወቅ በተደረገ ጥረት÷ ‹‹አባ ጳውሎስን ደግፋችኹ ከጻፋችኹ ማንም አይነካችኹ፤ ከተነካችኹም እኛ አለንላችኹ፤ ሁሉም ወንጀለኛ ነው›› በሚል የጥቅም ማበረታቻ የተቀበሉት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዋና ሓላፊ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ፣ በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ዋና ሓላፊነት ባለው ሥልጣን ቀናዒ ኦርቶዶክሳውያንን ከመድረክ እያገለለና በየአህጉረ ስብከቱ በመዞር ከፕሮቴንታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆችና አቀንቃኞች ጋራ ያለውን ግንኙነት እያጠናከረ የሚገኘው አእመረ አሸብር፣ እንደ ቀበሮዋ ዘለው ዘለው የሻቱትን ማዕርገ ጵጵስና ቢያጡት የተሾሙትን አባቶች በማሸማቀቅና አንገት በማስደፋት ለመሾም የቋመጡት አባ ሰረቀ፤ ለዚህም የገንዘብ ድጋፍ የሰጡት አባ ፋኑኤልና ዦቢራው ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን መኾናቸው እየተነገረ ነው፤ የአባ ጳውሎስ አይዟችኹ ባይነት (ቡራኬ) ሳይዘነጋ ማለት ነው፡፡ ይኹንና የዝግጅት ክፍሉም በጽሑፉ ላይ ማሻሻያ በማድረግና እንዲታተም በመፍቀድ፣ ምናልባትም የጥቅሙም ተካፋይ በመኾን መጠየቁ እንደማይቀር ግልጽ ነው፡፡

Tuesday, April 24, 2012

ብሂለ አበዉ


  • ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል    
  ቅዱስ አትናቴዎስ
  • ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል            
        ቅዱስ ሚናስ
  • በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና
        ታላቁ አባ መቃርስ
  • አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ሚስጥር ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት ያርቀዋል፡፡
   አረጋዊ መንፈሳዊ
  • ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ፡፡
  ማር ይስሐቅ
  • ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል     አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ጥበብ ይለየዋል፡፡                     
  አረጋዊ መንፈሳዊ
  •          ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ››    
  ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
  •          ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር›› 
  ቅዱስ ይስሀቅ ሶርያዊ
  •        ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም››
  ቅዱስ አርሳንዮስ
  •        ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል››              
        ቅዱስ እንድርያስ
  •          ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን››                           
  አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን
  •          ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው››  
  ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ

Monday, April 2, 2012

Monday, March 26, 2012

የለገዳዲ የቅ/ኪዳነ ምህረት ተአምር




የካቲት 16/2004 ዓ.ም  የቃል ኪዳኗ ታቦት ለእመቤታችን ቃል ኪዳን በተገባበት ቀን ለማክበር  ከህናት ወደ ዋሻው ገብተው ታቦቷን ተሸክመው ወደ  ድንኳን መጡ፡፡ እልልታው ቀለጠ ግማሹ በደስታ የለቅሳል ቀድሞ የፈረሰው የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን  ጋር የተጣለው ድንኳን ደረሱ ታቦት ተሸካሚው ካህን ምልክት አሳዩ ታቦትን መሸከም አልቻልኩም አቃጠለኝ ካህን ይቀየርልኝ አሉ፡፡ በሌላ ካህን ተቀየሩ ሕዝቡም እንዲረጋጋ ተነገረው፡፡ ወረብ ስብከት ወደፊት ለሚሰራው መቃኞ ቤተ ክርስቲያን እርዳታ ተሰበሰበ ስርዓት ቅዳሴ በድንኳን ውስጥ ተከነወነ፡፡ ከዚያም ታቦተ ቅድስት ኪዳነምህረትን ይዘው ከድንኳን ጉዞ ተጀመረ፡፡ ለወንጌል መስፋፋት ዘወትር የሚደክሙት ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉት የለገዳዲ ወጣቶች ቀይ ቲሸርት ለብሰው ቀይ ምንጣፍ የሚያነጥፉ ተቦቷን ወደ መጣችበት ዋሻ ለመመለስ ይዘምራሉ፡፡ ድንገት ድምፅ ተሰማ አልቅሱ ምዕመናን አልቅሱ እግዚአብሔር እንዲታረቀን አልቅሱ የሚል  በሞንታርቦ ድምጽ ተሰማ  ምዕመናን ሁሉ ተደናገጡ ታቦተ ኪዳነ ምህረትን የተሸከሙትን ሁለኛው ካህን እያለቀሱ ድምጽ አሰሙ፡፡ ተቃጠልኩ አንሱልኝ አልቻኩም እግዚኦ በሉ ብለው በወደቁበት ይጮኃሉ ግን ማን ታቦቷን ያንሳላቸው፡፡ እሳትን ማን ይደፍራል፡፡ ጩኽቱ ምህላው ለቅሶው እግዚኦታው ቀጠለ ግን ማንም ታቦቷን ማንሳት አልቻለም ሕዝበ ክርስቲያን እንደ ሻሽ ተነጥፈው አለቀሱ መነኮሳት እና ካህናት አነቡ በብዙ ለቅሶና እግዚኦታ ቆሞሱ አባታችን በወደቁበት ቦታ ሆነው ወደ ዋሻ አትመልሱኝ ክብሬ መገለጫው ደርሷል ወደ ድንኳን አስገቡኝ ብላለች ሲሉ በቀላሉ ብድግ አለችና ወደ ድንኳን ገባች፡፡ ሁለተኛው ታቦት ተሸካሚው ካህን ከወደቁበት ለማንሳት ተሞከረ እራሳቸውን ስተው በሕይወትና በሞት መካከል ሳሉ ወጣቶች ካህኑን ከካህን ጋር ይዘው ወደ ፀበሉ ሮጡ ታቦት ተሸካሚው ካህን ሲጠመቁ በእሳት የጋለ ብረት ምጣድ ውሃ ሲፈስበት የሚያወጣውን ድምጽ እና ጭስ እሰቸውም ላይ ታየ ከብዙ ሰዓታት ቆይተ በኋላ እራሳቸውን አወቁ፡፡ ካህናቱ የወደቁት ኃጢያተኛ ስለሆኑ ሳይሆን የቅድስት ኪዳነ ምህረት ዕለት ወደ ዋሻ አልገባም ብላ በተዓምቷ ቦታውን ስአስከበረች ነው፡፡ የወረዳው ምክር ቤት ፍልፍል ቤተክስቲያን ኃይማኖታዊ እና ታሪከዊ ቦታነቱን የታቦቷን ሃያልነት አምነው ተቀበሉ፡፡ ግን ቦታውን እስካሁን ለቤተክስቲያኗ አልሰጡም  ጠንካራው  የለገዳዲ ምዕመናን ግን በጥቂት ቀን ውስጥ መቃኞ ቤተክስቲያን ስርቶ አጠናቆ እሁድ መጋቢት 16/2004 ዓ.ም ፅላቷን ከድንኳን ወደ መቃኞ በሰላም ገብታለች ሕዝበ ክርስቲያኑም ከተለያየ ቦታ እየመጡ እየተፈወሱ ናቸው  በቀጣይ የተሸለ ቤተ ክርስቲያን ሰርቶ በቅርብ ማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው ሁላችንም የራሳችንን ድርሻ እንድንወጣ ይገባል መልክታችን ነው ፡፡
አምላክ ቤተክርስቲያናችንን ከጠላት ይጠብቅልን


Tuesday, March 20, 2012

የዋልድባ ጉዳይ አበቃለት ማለት ነው?

እንዴት ነው ነገሩ የዋልድባ ጉዳይ አበቃለት ማለት ነው? ትላንት መንግስት ስምምነት ላይ እንደተደረሰ እና ሌላ ሀሳብ ያለው ካለ ግን ብሎ  “ገዳማችን ይህን የሚደግፍ እንጂ የፀረ ሰላም ሀይሎች መሸሸጊያ አይደለም በዋልድባ ገዳም ስም የግል ጥቅማቸውን ለማራመድ የሚሯሯጡ ኃይሎችን እንቃወማለን” በማለት ፓለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ማድረጉ ምን ይሉታል እውን ወደ 18 አብያተ ክርስቲያናትን መንግስት እንዲያፈርስ መነኮሳቱ የሚፈቅዱ የመስለናልን? ይልቁንም ለመሰዋት እንደተዘጋጁ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ በ6/7/04  በቪኦዬ ሪዲዮ የቀረበውን እንስማ


Monday, March 19, 2012

የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዛሬም በደኑ ላይ የእሳት ቃጠሎው በንፋስ ሀይል በጣም እየተባባሰ ነው

የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዛሬም   በደኑ ላይየእሳት ቃጠሎው በንፋስ ሀይል በጣም እየተባባሰ ነው በአሁን ሰዓትም ከፍተኛ እርዳታ እንደሚፈልጉ ገልፀውልናል ቃጠሎው ትላንት ቅዳሜ 08/07/04 እንደጀመረ ለማወቅ ተችሎአል በአሞራ ገደል(የመላእክት ከተማ) አካባቢ መሆኑ እሳቱን ለማጥፋት ከባደ አድርጎታል
 

መንግሥት ከአካባቢው የውኃ ቦቴዎችን እና ወታደሮችን በማንቀሳቀስ ውኃውን ለማጥፋት ጥረት እያደረገ ቢሆንም እሳቱ ግን ወደ ገዳሙ በመጠጋት ላይ ነው፡፡
አሁን አማራጫችን አንድ ብቻ ነው፡፡ የዝቋላን ገዳም ከማጣታችን በፊት ያለንን ነገር ሁሉ ይዘን በተገኘው ትራንስፖርት ወደ ዝቋላ መትመም ብቻ፡፡ ወንበር ማርያም ድረስ የውኃ ቦቴዎቹ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ያለውን ባገኘነው ዕቃ ሁሉ ውኃውን ይዘን በመውጣት መረባረብ፡፡ ያለበለዚያ ግን የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ወደ ታሪክነት ይቀየራል፡፡
እነሆ ክርስትናችን የሚፈተንበት፣ ኢትዮጵያዊነታችንም የሚለካበት ጊዜ መጣ፣ በእሳት ተቃጥለው ያቆዩትን ገዳም ከእሳት ማዳን ካልቻልን እንግዲህ የኛ መኖር ትርጉሙ ምንድን ነው?