Friday, August 24, 2012

የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደሪ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው


የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደሪ ሊቀ ብርሃናት ተ/ማርያም መንገሻ ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 11/2004 ዓ.ም ሌሊት 6፡00 ሰዓት ላይ  የፍልሰታን ሰአታት ለመቆም ወደ ቤተ ክርስቲያን  በሚሄዱበት ሰአት እዚያው በቤተ ክረስስቲያኑ ቅጥር ግቢ  ሁለት የደብሩ አገልጋዮች  እንደደበደባቸውና በመሀልም የተመለከቱ ሰዎች በመጮሃቸው ምክነያት የደብሩ ጠበቃዎች መሳሪያቸውን በመተኮሳቸው የተነሳ ፓሊስ ደርሶ ሊተርፉ እንደቻሉ እና ከደብሩ አስተዳዳሪ ጋር ጠብ ይኖራቸዋል ተባለው የተገመቱ የታሰሩ ሲሆን ከትላንት በስቲያ ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሳቸው የታየ ሲሆን ከግድያ ሙከራው የሉበትም ተብለው የታሰሩ የነበሩትን የደብሩ አገልጋዮችን በዋስ የፈታ ሲሆን በወንጀሉ እጃቸው አለበት ብሎ ያመነባቸውን በእስር እንዲቆዩ ሆኗል፡፡
ደብዳቢዎቹ ጳጳሱ ከሚገቡበት ጉድጓድ አንተም ተገባለህ እያሉ እንደደበደቧቸው እና ሊገድሏቸው እንዳሰቡ ያገኘንው መረጃ ያስረዳል ፡፡

Thursday, August 23, 2012

የብጹዕ አባታችን አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነስርአታቸው ተፈፅሟል አጠር ያለ የህይወት ታሪካቸውንም ያድምጡት

የታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ እና ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቀ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሓይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዘዳንት እና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዘዳንት ሥርአተ ቀብር የተፈፀመበት ቀን አንድ መሆኑ እንድምታው ምንድነው?

የአለቃ አያሌው ታምሩ የሥርአተ ቀብር የተፈፀመበት ቀን 17/12/1999 ዓ.ም ሐሙስ

ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቀ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሓይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዘዳንት እና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዘዳንት 17/12/2004 ሐሙስ

Wednesday, August 22, 2012

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ፓሮቴስታንታዊ መሪ አስተናገደች

"†♥†ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥"ኢሳ.60፡12
ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት መቼም የማይነጣጠሉ ነበር ዛሬ ዛሬ ግን ቤተ ክርስቲያናችን ተሰሚነቷ እየቀነስ አመራሩ አካል ጫና እያሳደረባት እና ቤተ ክርስቲያኗ እንኳን ሲቃጠሉ ሀይ ባይ እያጣች መጥቶ ዛሬ ደግሞ ይህ አልበቃ ብሎ ኢትዮጵያ እና ኦርቶዶክስ ተፋተው የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ መሪ ለማስተናገድ በቃች፡፡
መቼም ሁላችሁም እንደምትገምቱት ሐይለማርያም ብሎ ፓሮቴስታንት አይኖርም አይደረግም ብላችሁ ተገምቱ ይሆናል ነገር ግን በደቡቡ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንሰራፍ ያለው የፕሮቴስታንት እምነት ወደድንም ጠላንም አሁን መሪ የተባሉትን ጠቅላይ ሚንስቴር ሀይለ ማርያም ደሳለኝን ሳይቀር  ሰለባ አድርጓቸዋል፡፡ ወላይታና አካባቢውም ቢሆን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተኩረት ባለመስጠቷ ብዙዎቹ ካደጉባት ቤተ ክርስቲያን   አስተምህሮዋን ባለመረዳት ኮብልለዋል፡፡ እግዚአብሔር ወደ እናት ቤታቸው እስኪመልስልን ልንፀልይ ይገባል እኛ የምንሰራቸው የቤተ ክርስቲያናችን ስራዎች ግን በዝተዋል ፡፡
ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ  እንዲሉ

የብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነ ስርዓት ነሐሴ 16 ቀን 2004 ዓ.ም.ከ4.00 ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል

የብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቀ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሓይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዘዳንት እና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዘዳንት የቀብር ስነ ስርዓት ነሐሴ 16 ቀን 2004 ዓ.ም.ከ4.00 ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል ስርአቱ እስከ ነገ ከሰዓት ድረስ የሚቀጥል ይሆናል ከ4.00 ጀምሮም ከሆስፒታል ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በመደረስ በዚያም ጸሎት ሲደረግለት ቆይቷል፡፡

በምንኩስና ከዓለም መለየት እና የምነኩስና ቆብ፡፡

ምንኩስና በምንኩስና ከዓለም መለየት
ምንኩስና ማለት አንድ ልብ አንድ ሐሳብ ሆኖ እግዚአብሔርን በማገልገልና እሱን ብቻ በማሰብ ተወስኖ መላእክትን በመምሰል ከዓለማዊው ተድላ ደስታ መለየት ማለት ነው እንጂ ሰው መሆንን ለመርሳት ወይም ለመተው አይደለም፡፡ ይህም ይታወቅ ዘንድ ሐዋርያ ጳውሎስ " ወበኅቤየስ ምውት ዓለም ወአነሂ ምውት በኅበ ዓለም በኔ ዘንድ የሞተ ነው፡ እኔም በዓለም ዘንድ የሞትኩ ነኝ ብሏል፡፡ ገላ 6፡ ፡14
ሞት ማለትም መለየት ማለት ነው እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም፡ "አኮኑ ወዳዕነ ሞትነ እምኃጢአት እፎ እንከንክል ሐይወ ባቲ" ከኃጢአት ፈጽመን ተለይተናል እንግዲህ በኃጢአት መኖር እንዴት እንችላለን እንዳለ:: ሮሜ 6፡2
በምንኩስና ከዓለማዊ ግብር መለየትም ፍጹም ለመሆን ነው እንጂ በዓለማዊ ግብር ሆኖ እግዚአብሔርን ማገልገል አይቻልም ማለት አይደለም በዓለማዊ ግብር ሆነው የታዘዘውን ሕግ ፈጽመው ከጸደቁ ዓለማውያን እነ ኖኅ አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ሄኖክ ኢዮብን የመሳሰሉ አሉ ማቴ 22 ፡ 32፡፡ ያዕ፡5:11:ዕብ፡11፡ 5፡6፡፡

Monday, August 20, 2012

የጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ ሆኗል መግለጫውንም እንዲህ ሰማን

" ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።"ዮሐ.1:3
PM Meles Zenawi has died. The long lasting discussion of his whereabouts are rested now. Ethiopia lost two of its powerful leaders: the premier and the patriarch. It is amazing time. May God rest their souls. Amen
ዛሬ ማለዳ ነሐሴ 15,2004ዓ/ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ አድርጓል::

ይህንንም ተከትሎ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ Haile Mariam Desalegne named acting Prime Minister

ሰበር ዜና ቅዱስ ሲኖዶስ ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ መረጠ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚመራ  ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ  ሰየመ፡፡ በዛሬው ዕለት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ  ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቃቤ መንበር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ፓትርያርክ እስኪመርጥ ድረስ ቤተ ክርስቲያንን በበላይነት የሚመሩ ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ ይሆናል::
ቡነ ህዝቅኤል ዛሬ ነሐሴ 14/04 በ9.00 ሰዓት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መሰረት ፓትርያርክ እስኪመረጥ ድረስም ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሲኖዶሱን በመሰብሰብ በሐላፊነት ይቆያሉ ውሳኔው ግን የተወሰነው ዛሬ ጠዋት መሆኑ ታውቋል::

Sunday, August 19, 2012

የፓትርያርክ ምርጫ እና ተያያዥ ጉዳዮች

ቅዱስ ሲኖዶስ 1991 . ባወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ  ስለ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ምዕራፍ አራት ላይ ያሉትን አንቀፆች እንመ 
አንቀጽ 13
ስለ ቅዱስ ፓትርያርክ ምርጫ
  1. ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ ቀኖና በሚፈቅደው መሠረት ተመርጦ ይሾማል፡፡
  2. ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ፓትርያርክ ምርጫ በሚወስነው ቁጥር መሠረት አስመራጭ ኮሚቴ ይቋቋማል::
  3.   ለፓትርያርክነት የሚመረጡት ዕጩዎች ከሊቃነ ጳጳሳት ከጳጳሳትና ከኤጲስ ቆጶሳት መካከል ሲሆን ብዛታቸው ከሦስት ያላነሡ ከአምስት ያልበለጡ ይሆናል፡፡