በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚመራ ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ ሰየመ፡፡ በዛሬው ዕለት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቃቤ መንበር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ፓትርያርክ እስኪመርጥ ድረስ ቤተ ክርስቲያንን በበላይነት የሚመሩ ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ ይሆናል::
አቡነ ህዝቅኤል ዛሬ ነሐሴ 14/04 በ9.00 ሰዓት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መሰረት ፓትርያርክ እስኪመረጥ ድረስም ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሲኖዶሱን በመሰብሰብም በሐላፊነት ይቆያሉ ውሳኔው ግን የተወሰነው ዛሬ ጠዋት መሆኑ ታውቋል::