ሁሌም ቢሆን ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲጣስ እያየን ዝም የሚል ልብ የለንም፡፡ በተለይ በመድረክ አገልግሎት ላይ
በመናያቸው ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲጣስ ማየተ ደግሞ በጣሙን የቆስላል፡፡ መቼም ሳይገባው የቤተ ክርስቲያን መድረክ
ላይ ለመውጣት የሚደፍር አለ ብለን አናስብም ትንሽም ቢሆን ምስጢራትን የተማረ እና የስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን
ያወቀ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ስርዓትማ ካየንው አንድ ሰው ወደ አገልግሎት ከመግባቱ
በፊት በፈሪሐ እግዚአብሔር ሊቀርብ ይገባዋል::“በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር ስታደርግ
ለአንተ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ ለዘላለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ የማዝዝህን እነዚህን ቃሎች ሁሉ ሰምተህ
ጠብቅ።” ዘዳ.12:28፤ እንደተባልንው ስንመላለስ እግዚአብሔርን በመፍራት የሚያዘንን
በመፈጸም መሆን ይኖርብናል::
እግዚአብሔርን የሚፈራ
ትውልድ ደግሞ ለእግዚአብሔር ቃል ይገዛል በእግዚአብሔርም የባረካል፡፡ በንስሃ ህይወቱም ሁል ጊዜ ተጠብቆ መኖርም
ይገባል “እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፥ ጠብቀውም ንስሐም ግባ” ራእ.3:3 ንስሃ የሚገባ
ሰው ደግሞ ህይወቱ በጸሎት የመሰረታል ሁል ጊዜም ይሰግዳል ይጾማልም ለአገልግሎቱም መቃናተ ፈቃደ እግዚአብሔርን
በመጠየቅ ይኖራልም፡፡ እነኝህ ያነሳናቸው በጣም ጥቂቱን ግዴታዎች ነው ይህቺን ትንሻን ህይወት የሌለው ክርስቲያን
አገልጋይ አይደለም ክርስቲያን ለመሆኑም ጥርጣሬ ውስጥ ይገባል፡፡