በስመ አብ
ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡
አሜን፡፡
ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ ያደረሱን “ፍቅረ መድኅን” የተሰኙ ተርጓሚ(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ
ሲኖዳ 3ኛ የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን
113ኛ አበ አበው (ፓትርያርክ) እንደ ጻፉት) ሲሆኑ እኛም ጽሁፉ የያዘውን ቁመ ነገር ለእናነተም ልናካፍላችሁ ወደድን ተርጓሚውን አምላክ በእድሜ በፀጋ ይጠብቅልን፡፡ መልካም
ንባብ፡፡
ውርስ ትርጉም - በፍቅረ መድኅን
የእንግሊዝኛው ርእስ- The Virtue of
Humility
እመቤታችን እና ንግሥታችን
የምትኾን፤ የቅድስተ ቅዱሳን ወላዲተ አምላክ
ድንግል ማርያምን በዓል ምክንያት አድርገው
የመንፈሳውያን ዓርማ፤ የአጋንንት መውጊያ
ስለኾነችው ስለ “ትኅትና” ቅዱሰነታቸው አቡነ
ሲኖዳ ካስተማሩት
የእመቤታችን የቅድስት
ድንግል ማርያምን በዓል ምክንያት አድርገን
ከታደለቻቸው ጸጋዎቿ አንዱ ስለኾነው ጸጋዋ
እንነጋገራለን፡፡ይኸውም ትኅትና ነው፡፡
በመንፈሳዊ ሕይወት ትኅትና ቀዳሚው
ጸጋ ነው፡፡ትኅትና በመንፈሳዊ ሕይወት ግንባር
ቀደም በመኾን ጸጋን እና ተሰጥዖን ይጠብቃል፡፡በትኅትና
ያልታጀበ ወይንም ከትኅትና ጋር ያልኾነ ጸጋ
ኹሉ በግብዝነት የተነሣ በሰይጣን ሊነጠቅ፤
በኩራት በመመካት እና ራስን በማድነቅ የተነሣ
ሊጠፋ ይችላል፡፡
ወዳጄ: እግዚአብሔር ማንኛውንም ዓይነት
ስጦታ ቢሰጥህ ከስጦታው ጋር ትኅትናን
ጨምሮ እንዲሰጥህ ካልኾነ ግን ካንተ እንዲወስድልህ
ጸልይ፡፡ በተሰጠህ ስጦታ የተነሣ በመመካት
እንዳትጠፋ፡፡